Scripture Stories
ያዕቆብ እና ቤተሰቡ


“ያዕቆብ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ያዕቆብ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 27–33

ያዕቆብ እና ቤተሰቡ

ጌታ ቃል ኪዳኖቹን እንዴት እንደሚጠብቅ

ምስል
ያዕቆብ ከአህያ ጋር ሲራመድ

ያዕቆብ ከተቆጣው ወንድሙ ዔሳው ለማምለጥ ቤቱን ለቆ ሄደ። የያዕቆብ አባትም ጌታን የምታፈቅር እና ትእዛዛቱን የምታከብር ሴት እንዲያገኝና እንዲያገባ ባረከው።

ዘፍጥረት 27፥42–4628፥1–5

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ለያዕቆብ ሲገለጥ

ያዕቆብ በጉዞ ላይ እያለ፣ ጌታ በራዕይ ጎበኘው። ሁልጊዜ ከያዕቆብ ጋር እንደሚሆንም ቃል ገባለት። ያዕቆብ ከተቀበለው ሁሉ አስራቱን ለጌታ ለመስጠት ቃል ገባ።

ዘፍጥረት 28፥10–16፣ 20–22

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ከያዕቆብ ጋር ሲነጋገር

ጌታም ያዕቆብ ብዙ ልጆች እንደሚወልድ ቃል ገባለት። በያዕቆብ ልጆች በኩል፣ የምድር ቤተሰቦች አዳኙን በማወቅ ይባረካሉ። በኋለኛው ቀናትም የያዕቆብ ቤተሰብ የእስራኤል ቤት ተብለው ይታወቃሉ።

ዘፍጥረት 28፧3–4፣ 141 ኔፊ 10፥14

ምስል
ያዕቆብ እና ራሔል

ያዕቆብ ወደ ሐራን ምድር ተጓዘ። በዚያም ራሔል የምትባል አንዲት ጻድቅ ሴትን አፈቀረ።

ዘፍጥረት 27፥4329፥9–20

ምስል
ያዕቆብ በሜዳ ላይ እየሰራ

ያዕቆብም ላባን ራሔልን እንዲያገባ ከፈቀደለት፣ ለአባቷ ላባን ለሰባት ዓመት ለመሥራት ተስማማ። ላባንም ተስማማ። ያዕቆብ ለሰባት አመት ሰራ።

ዘፍጥረት 29፥21–27

ምስል
ያዕቆብ፣ ራሔል፣ እና ልያ

ላባን ግን የመጀመሪያዋ ልጁ ልያ በመጀመሪያ እንድታገባ ፈለገ። በሠርጉ ወቅት ላባን ያዕቆብን በማታለል በምትኩ ልያን እንዲያገባ አደረገ። ነገር ግን ያዕቆብ ራሔልን ያፈቅር ነበር። እርሷንም ማግባት ከቻለ ሌላ ሰባት ዓመት እንደሚሠራ ቃል ገባ። ላባንም ተስማማ፣ እናም የያዕቆብ ቤተሰብ ማደግ ጀመረ።

ዘፍጥረት 29፥28–3530፥3–13፣ 17–24ያዕቆብ 2፥27–30

ምስል
ያዕቆብ ከቤተሰቡ ጋር ሲጓዝ

ላባንም ያዕቆብን በትክክል አልከፈለውም። ነገር ግን ጌታ ያዕቆብን በብዙ እንስሳት ባረከው እናም ወደ ቤት እንዲመለስ ነገረው።

ዘፍጥረት 30፥31፣ 4331፥1–7፣ 17–18

ምስል
ያዕቆብ

ወደ ቤቱ በመጓዝ ላይ እያለም፣ ያዕቆብ ወንድሙ ዔሳውና 400 ሰዎች ሊገናኙት እንደመጡ ተረዳ።

ዘፍጥረት 32፥3–6

ምስል
ያዕቆብ ቤተሰቡን ሲደብቅ

ያዕቆብም ዔሳው በእርሱ ላይ አሁንም ተቆጥቶ ሳይሆን እንዳልቀረ አሰበ። ያዕቆብ ለቤተሰቡ ደህንነት ፈራ፣ ስለዚህ ወደ ደህና ቦታ ወሰዳቸው እናም ጸለየ።

ዘፍጥረት 32፥7–24

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ከያዕቆብ ጋር ሲነጋገር

ያዕቆብ ለሊቱን ሙሉ እንዲሁም እስከ ጠዋት ድረስ ጸለየ። ጌታ ያዕቆብን ጎበኘና ባረከው። እርሱም የብዙዎች ታላቅ መሪ እንደሚሆንም ጌታ ነገረው። ጌታም የያዕቆብን ስም ወደ እስራኤል ለወጠው።

ዘፍጥረት 32፥24–30

ምስል
ኤሳው ከያዕቆብ ጋር ሲገናኝ

ወዲያውኑም ዔሳው እና ሰዎቹ ያዕቆብን እና ቤተሰቡን አገኙ። ዔሳው በያዕቆብ ላይ አልተቆጣም ነበር። ከያዕቆብ ጋር ለመገናኘት ሮጠ እናም አቀፈው። እርሱን ለማየት እና ከቤተሰቡ ጋር ለመገናኘትም በጣም ተደስቶ ነበር። ያዕቆብም ዔሳውን እንደገና በማየቱ ተደስቶ ነበር።

ዘፍጥረት 33፥1–7

ምስል
ያዕቆብ እና ዔሳው ቤተሰብን ሲመለከቱ

ጌታ ለያዕቆብ የገባቸውን ቃል ኪዳኖች በህይወቱ ሙሉ ጠበቀ። ያዕቆብ ከቤተሰቡ ጋር ወደ አገሩ ደረሰ በዚያም ሰፈረ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ፣ ያዕቆብ እስራኤል ተብሎ ተጠራ፣ እናም ቤተሰቦቹም እስራኤላውያን ተባሉ። ትእዛዛትን ማክበሩን እና ጌታን ማምለኩን ቀጠለ።

ዘፍጥረት 33፥17–20

አትም