“ንጉስ ኢዮስያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ንጉስ ኢዮስያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ንጉሥ ኢዮስያስ
የጌታን ትእዛዛት የመጠበቅ ተልዕኮ
ኢዮስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ በተሾመ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበር። ጌታን የሚወድ ጥሩ ንጉሥ ነበር። ጌታን እንዲታዘዙና ጣዖታትን ማምለክ እንዲያቆሙ ህዝቡን እስራኤላውያንን ለመርዳት ፈለገ። ዕድሜው ሲገፋ፣ እርሱና ህዝቡ ቤተመቅደሱን ማደስ እና እንደገና ውብ ማድረግ ጀመሩ።
ህዝቡ በቤተመቅደሱ ላይ ሲሠሩ፣ የካህናቱ አለቃ ኬልቅያስ የህጉን መጽሐፍ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን የያዘውን ጥቅልል አገኘ።
አንድ አገልጋይ መጽሐፉን ለኢዮስያስ አነበበለት። ኢዮስያስ ቃላቱን ሰማ እናም ሕዝቡ ጌታን ባለመታዘዙ ምክንያት አዘነ። ማዘኑን ለማሳየት ልብሱን ቀደደ።
ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጌታን እንዲጠይቅ ለኪልቅያስ ነገረው። ኬልቅያስና የንጉሱ አገልጋዮች ሕልዳናን ጎበኙ። እርሷ ነቢይት ይሄውም በጌታ የተነሳሳች ታማኝ መሪ ነበረች። እርሷም ህዝቡ እንዲታዘዙ እየረዳ ስለነበር ጌታ በኢዮስያስ ተደስቷል አለች። ንጉስ ኢዮስያስ በሰላም እንደሚኖር ጌታ ቃል ገባ።
ንጉሥ ኢዮስያስ ህዝቡ ለጌታ የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች እንዲጠብቁ ፈለገ። ጌታ ከረጅም ጊዜ በፊት እስራኤላውያንን እንዴት ከግብፅ ነፃ እንዳወጣቸው ለማስታወስ እንዲረዳቸው ፋሲካን እንዲያከብሩ ጠየቃቸው።