“ዳንኤል እና የአንበሶች ጕድጓድ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ዳንኤል እና የአንበሶች ጕድጓድ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዳንኤል 6
ዳንኤል እና የአንበሶች ጕድጓድ
የአንድ ሰው ለመጸለይ ያለው ድፍረት
ዳርዮስ የባቢሎን ገዢ ሆነ እርሱም ዳንኤልን ይወድ ነበር እናም በግዛቱ ሁሉ እርሱን መሪ ለማድረግ ፈለገ። የንጉሱ አንዳንድ ጥበበኛ ሰዎች ቀንተው ነበር።
ጥበበኛ ሰዎች ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር እንደሚጸልይ ያውቁ ነበር፣ ስለዚህ ንጉሱ አዲስ ህግ እንዲያውጅ አታለሉት። ማንም ለእግዚአብሔር የሚጸልይ ሰው ወደ አንበሳ ጉድጓግ ይጣላል።
ዳንኤል ይህም ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ መረጠ። የንጉሱ ጥበበኛ ሰዎችም ዳንኤል ሲጸልይ አዩት እናም ዳንኤል ህጉን እንደጣሰ ለንጉሱ ነገሩት። ንጉሱ ጥበበኛ ሰዎቹ እንዳታለሉት ተገነዘበ። ዳንኤልን የሚያድንበት መንገድ ለማግኘት ሞከረ፣ ነገር ግን ንጉሱ የራሱን ህግ መከተል ነበረበት።
ዳንኤልም በአንበሶች ጕድጓድ ተጣለ። ዳንኤል እንዲጠበቅ እየጾመ፣ ንጉሱ ለሊቱን በሙሉ ሳያንቀላፋ አደረ።
በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሣ፥ ፈጥኖም ወደ አንበሶቹ ጕድጓድ ሄደ። ዳንኤል አሁንም በህይወት እንዳለ ለማየትም ጠራው። ዳንኤልም መለሰለት! እግዚአብሔር የአንበሶችን አፍ ለመዝጋት መልአክን እንደላከ ለንጉሱ ነገረው። አንበሶቹ እርሱን አልጎዱትም።
ንጉሱ ዳንኤል ደህና በመሆኑ ተደስቶ ነበር። ያታለሉትን እነዚያን ጥበበኛ ሰዎች ቀጣ፣ እናም ህጉንም ሰረዘ። መንግስቱንም ስለእግዚአብሔር ሀይል እና መልካምነት አስተማረ።