“ኢዮብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2021 (እ.አ.አ)]
“ኢዮብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ኢዮብ 1–3፤ 19፤ 38–42
ኢዮብ
የጌታን ፍቅር ማመን
ኢዮብ ጌታን የሚወድና ትእዛዛቱን የሚያከብር መልካም ሰው ነበር። እርሱና ባለቤቱ 10 ልጆች ነበሯቸው እንዲሁም ብዙ የእንስሳት መንጋዎች እና ታላቅ ሀብት ነበረው።
ጌታ የኢዮብ እምነት እንዲፈተን ፈቀደ። ኢዮብ ከባድ ነገሮች አጋጠሙት።
አንድ ቀን ብዙዎቹ የኢዮብ እንስሳት ተሰረቁ። በኋላም እሳት የኢዮብን መላ ንብረቶች አቃጥሎ አገልጋዮቹን ሁሉ እንዲሁም ሌሎች እንስሳቶቹን ሁሉ ገደለ። ከዚያም አውሎ ንፋስ የኢዮብን ልጅ ቤት አፈረሰ። ልጆቹም በውስጡ ነበሩ እናም ሁሉም ሞቱ። ኢዮብ እና ባለቤቱ ከጤንነታቸው በስተቀር ምንም አልነበራቸውም።
ኢዮብ እና ባለቤቱ አዝነው ነበር። ልጆቻቸውንም ሳይቀር ሁሉንም አጥተው ነበር። ነገር ግን ኢዮብ አሁንም በጌታ ላይ እምነት ነበረው። ስለሆነው ነገር ጌታን አልወቀሰም።
ከዚያም ኢዮብ በጣም ታመመ። ሰውነቱን የሚያም ቁስል ሸፈነው። ኢዮብ እና ባለቤቱ እነዚህ ሁሉ መጥፎ ነገሮች ለምን እየተከሰቱ እንደሆነ ለማወቅ ጓጉ።
ጌታ ኢዮብን አናገረው እናም ምድርን፣ ከዋክብትን፣ እና ህይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ አሳየው። ጌታም ኢዮብን አስፈላጊ ትምህርት አስተማረው። ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት የሰማይ አባትን ልጆች ስለልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲማሩ እና እርሱን እንዲከተሉት ለመርዳት ነበር።
ኢዮብ ንስሀ ገባ በመጠራጠሩም ጌታን ይቅርታ ጠየቀ። በጌታ ለመታመን ቃል ገባ። ጌታ ኢዮብ እንደሚወደው አወቀ። ኢዮብን ፈወሰው እንዲሁም ተጨማሪ ልጆችን በመስጠትና አስቀድሞ ከነበረው በሁለት እጥፍ ሀብት በመስጠት ባረከው።