“ሐና፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ሐና፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ሐና
ለታማኝ ሴት የጌታ መልስ
በየዓመቱ፣ ሐና እና ባለቤቷ የጌታ ቤት ወደሆነው ወደ ቤተመቅደስ ይጓዙ ነበር። ሐና ልጆች አልነበሯትም፣ ስለሆነም በጣም አዘነች። ወንድ ልጅ ይኖራት ዘንድም ፆመች እና ፀለይች። ሐና ወንድ ልጅ ቢኖራት ልጇ ሲያድግ እርሱን እንደሚያገለግል ለጌታ ቃል ገባች።
ዔሊ የሚባል አንድ ካህን ሐና ስታለቅስ አያት። ጌታ ፀሎቷን እንደሚመልስላት ነገራት። ሐና በእግዚአብሔር ታመነች እንዲሁም ተስፋ አደረገች።
በዚያም አመት ሐና ወንድ ልጅ ወለደች። ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው።
ሐና ለጌታ ቃል የገባችውን አከበረች። ሳሙኤል ዕድሜው በደረሰ ጊዜ በጌታ ቤት ውስጥ እንዲያገለግል ወሰደችው። እርሱ ከካህኑ ዔሊ ጋር አገለገለ። ሐና ሳሙኤልን መጎብኘቷን ቀጠለች። ለእርሱ የሰፋችለትን ልብሶች አመጣችለት። እግዚአብሔር ሐናን በአምስት ተጨማሪ ልጆች ባረካት።