“ነቢዩ ኢያሱ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ነቢዩ ኢያሱ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘዳግም 10፤ 31፤ 34፤ ኢያሱ 1፤ 3–6፤ 10–11፤ 21፤ 24
ነቢዩ ኢያሱ
ወደቃል ኪዳኑ ምድር ከመገባቱ በፊት የመጨረሻው ፈተና
ነቢዩ ሙሴ ወደሰማይ ከተወሰደ በኋላ ጌታ ኢያሱን አዲሱ ነቢይ እንዲሆን ጠራው። እስራኤላውያን በዮርዳኖስ ወንዝ አቅራቢያ በሰፈሩበት ጊዜ፣ ጌታ ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር የሚሄዱበት ጊዜ እንደደረሰ ተናገረ።
ዘዳግም 34፥1–9፤ ኢያሱ 1፥1–4፤ አልማ 45፥19
የቃል ኪዳኑ ምድር በከነዓን ነበር፤ ነገር ግን ክፉ ሰዎች እዚያ ይኖሩ ነበር። ጌታ ኢያሱን ብርታት እንዲኖረው እና እንዲጸና ነገረው። በጌታ እርዳታ እስራኤላውያን የከነዓንን ምድር ማሸነፍ ይችላሉ።
ኢያሱ ሰራዊት ሰበሰበ። ጌታ የአሥርቱ ትእዛዛትን የድንጋይ ጽላቶች እና ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲሸከሙ ነገራቸው። ካህናቱ እነዚህን ቅዱስ ዕቃዎች የቃል ኪዳን ታቦት በተባለ ሳጥን ውስጥ ተሸከሙ። ከዚያም ሠራዊቱ የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ተዘጋጀ። ወንዙ ጥልቅ ነበር እንዲሁም በፍጥነት ይሄድ ነበር።
ዘዳግም 10፥5፤ 31፥25–26፤ ኢያሱ 1፥10–11፤ 3፥1–11
ጌታ ወንዙን እንዲሻገሩ እንደሚረዳቸው ኢያሱ ለእስራኤላውያን ቃል ገባላቸው።
ኢያሱ 12 ካህናት የቃል ኪዳኑን ታቦት እንዲሸከሙ እና ወደውሀው እንዲገቡ ጠየቃቸው። ካህናቱ ወንዙ ውስጥ እንደገቡ ውሀው ተከፈለ።
እስራኤላውያን ወንዙን በደረቅ መሬት ተሻገሩ። ኢያሱ ከደረቁ ወንዝ 12 ድንጋዮችን እንዲወስዱ እስራኤላውያንን ጠየቃቸው። በዚያን ቀን የነበረውን የጌታ ተአምር ለእስራኤላውያን ለማስታወስ ድንጋዮቹን ቆለላቸው።
ኢያሱ የእስራኤላውያንን ሰራዊት ወደ ከነዓን ምድር መራ። ኢያሪኮ ወደምትባል ከተማ ደረሱ። ከተማዋ በጣም ጠንካራ ነበረች እንዲሁም ረዥም ግንቦች ነበሯት። ጌታ ኢያሪኮን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል ለኢያሱ ነገረው። እስራኤላውያን ለስድስት ቀናት ያህል በየቀኑ ኢያሪኮን መዞር አለባቸው አለ። ኢያሱ ጌታን ታዘዘ።
ኢያሱ የቃል ኪዳኑን ታቦት በእስራኤላውያን ፊት እንዲሸከሙ ለካህናቱ ነገራቸው። በየቀኑም ሠራዊቱ በኢያሪኮ ዙሪያ ዞረ እንዲሁም ሰባት ካህናት ቀንደ መለከታቸውን ነፉ። ሌሎቹ እስራኤላውያን ሁሉ ዝም አሉ።
በሰባተኛው ቀን ሠራዊቱ በኢያሪኮ ዙሪያ ሰባት ጊዜ ዞሩ። ካህናቱ ቀንደ መለከታቸውን ሲነፉ ኢያሱ እስራኤላውያን እንዲጮኹ ነገራቸው። በድንገት የኢያሪኮ ግንብ ወደቀ፣ እናም የኢያሱ ሠራዊት ከተማይቱን ወሰደ።
ጌታ ቃል እንደገባው እስራኤላውያንን ረዳቸው። የኢያሱ ሠራዊት የከነዓንን ምድር መውረሱን ቀጠለ፤ እናም እስራኤላውያን እዚያ መኖር ጀመሩ። ኢያሱም የጌታን ተአምራት እና ቃል ኪዳኖች አስታወሳቸው። እርሱም እስራኤላዊያን ጌታን ለማገልገል እንዲመርጡ ጠየቃቸው።