“ሙሴ እና የነሀሱ እባብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ሙሴ እና የነሀሱ እባብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ሙሴ እና የነሀሱ እባብ
በጌታ ላይ እምነት ማሳደርን መማር
እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሲጓዙ ብዙ ጊዜ ጌታን ይረሱ እና ያጉረመርሙ ነበር። ትሁት እንዲሆኑ እና እርሱን እንዲያስታውሱ ለመርዳት ጌታ እባቦችን ላከ። እባቦቹ ህዝቡን ነደፉ፤ እናም ብዙዎቹ ሰዎች ሞቱ።
ብዙም ሳይቆይ ህዝቡ ንስሃ ገባ። ጌታ እባቦቹ እንዲሄዱ እንዲያደርግ እንዲጸልይ ሙሴን ጠየቁት። ጌታ እባቦቹን እንዲሄዱ አላደረገም። ነገር ግን ከተነደፉ ህዝቡ የሚድኑበትን መንገድ አዘጋጀ።
ጌታ ሙሴን ከናስ እባብ እንዲሠራና በበትር ላይ እንዲሰቅለው ነገረው። ሕዝቡ ተነድፈው በነበረ ጊዜ እና የናሱን እባብ በመለከቱ ጊዜ ጌታ አዳናቸው። ጌታም እስራኤላዊያን ትሁት እንዲሆኑ እና በእርሱ እንዲታመኑ ረዳቸው።