Scripture Stories
ንግስት አስቴር


“ንግስት አስቴር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ንግስት አስቴር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

አስቴር 2–5፤ 7–9

ንግስት አስቴር

በአደጋ ጊዜ ደፋር

ምስል
አስቴር በንጉሱ ቤተመንግስት ውስጥ

አንዳንድ እስራኤላውያን አይሁድ ተብለው ይጠሩ ነበር። አስቴር በፋርስ የምትኖር አይሁዳዊት ነበረች። ወላጆቿ ስለሞቱ የአጎቷ ልጅ መርዶክዮስ ተንከባከባት። በመንግሥቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች ወጣት ሴቶች ጋር ወደ ንጉሱ ቤተመንግሥት ተጋበዘች። ንጉሱ አዲስ ንግሥት ፈለገ እናም አስቴርን መረጠ።

አስቴር 2፥2–7፤ 16–17

ምስል
ሰዎች ለሐማን ሲሰግዱ

ንጉሱ ታላቅ ስልጣን የኖረው ሐማን የተባለ አገልጋይ ነበረው። ሐማንም ንጉሱ ምድሪቱን ሲገዛ ይረዳው ነበር። ንጉሱ ሁሉም ሰው ለሐማን እንዲሰድግ ያደርግ ነበር።

አስቴር 3፥1–2

ምስል
መርዶክዮስ እና ሐማን

መርዶክዮስ ግን ለሐማን አይሰግድም። መርዶክዮስ የሚሰግደው ለጌታ ብቻ ነበር። ይህም ሐማንን አናደደው። መርዶክዮስን እና አይሁዶችን በሙሉ ለመቅጣት ፈለገ።

ዘጸአት 20፥5አስቴር 3፥5–6፣ 8

ምስል
ወታደር ለሰዎች ማስታወቂያ ሲናገር

ሐማን አይሁዶች የንጉሱን ህግጋት እንዳልተከተሉ ለንጉሱ ነገረው። ንጉሱም ሐማን አዲስ ህግ እንዲያረቅ ፈቀደለት፤ አንድ ቀን ሁሉም አይሁዳውያን ይገደላሉ።

አስቴር 3፥8–11፣ 13

ምስል
መርዶክዮስ ከአስቴር ጋር ሲነጋገር

መርዶክዮስም አስቴርን ከንጉሱ ጋር እንድትነጋገር ጠየቃት። ንጉሱ የሐማንን ህግ መቀየር እና አይሁዳውያንን ማዳን ይችላል። ነገር ግን አስቴር ፈርታ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ንጉሱ ያለግብዣ እርሱን ለማነጋገር የሚመጡትን ይገድል ነበር።

አስቴር 4፥5–11

ምስል
አስቴር ሰዎችን ስትመለከት

መርዶክዮስ አስቴርን ስለሚገደሉት አይሁድ እንድታስብ ጠየቃት። መርዶክዮስም ጌታ አይሁዳውያንን ለማዳን አስቴርን በንጉሱ ቤተመንግሥት ውስጥ አስቀምጦም ሊሆን ይችላል አለ።

አስቴር 4፥13–14

ምስል
አስቴር እየጸለየች

ለመገደል የሚዳርጋት ቢሆንም እንኳ፣ አስቴር ከንጉሱ ጋር መነጋገር እንዳለባት አወቀች። አስቴር መላ አይሁዳውያን እና አገልጋዮቿ ከእርሷ ጋር እንዲጾሙ ጠየቀች።

አስቴር 4፥15–16

ምስል
አስቴር በሮችን ስትመለከት

አስቴር ለሦስት ቀናት ከጾመች በኋላ እራሷን አዘጋጀችና ንጉሱን ለመጠየቅ ሄደች።

አስቴር 5፥1

ምስል
አስቴር በንጉሱ ፊት እየሰገደች

ወደ ንጉሱ በቀረበች ጊዜም በትረ መንግስቱን ዘረጋ። ይህም ንጉሱ እርሷን በማየቱ ተደስቷል እናም አይገድላትም ማለት ነበር። ምን እንደፈለገች ጠየቃት። አስቴርም ህዝቦቿ በአደጋ ላይ እንዳሉ ለንጉሱ ነገረችው። በሐማን ህግ መሰረት፣ በመንግስቱ ውስጥ ያሉት እርሷ እና መላ አይሁዶች ይገደላሉ።

አስቴር 5፥2–37፥4–6

ምስል
ወታደር ለሰዎች ማስታወቂያ እየሰጠ

ንጉሱ በሐማን ተቆጣ እናም አስገደለው። ንጉሱም አይሁዶችን የሚጠብቅ አዲስ ህግ አወጣ። አሁን ማንም ሊጎዳቸው ቢሞክር ራሳቸውን እንዲከላከሉ ተፈቅዶላቸዋል ነበር።

አስቴር 7፥9–108፤10–11

ምስል
አስቴር

አስቴር በጌታ ላይ በነበራት እምነት እና ከንጉሱ ጋር ለመነጋገር በመድፈሯ ህዝቧን አዳነች። በሞት እና በሀዘን ምትክ ድግስ ነበር። አይሁዶችም ተደሰቱ።

አስቴር 8፥16–179፥18–32

አትም