Scripture Stories
ነቢዩ ኤልያስ


“ነቢዩ ኤልያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ኤልያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

1 ነገሥት 16–18

ነቢዩ ኤልያስ

የእናት እምነት እና የጌታ ተአምራት

ምስል
ኤልያስ ከንጉስ አክዓብ እና ከንግስት ኤልዛቤል ጋር ሲነጋገር

የእስራኤል መንግስት ምንም ዝናብ አልነበራትም፣ እናም ውሀም እያለቀ ነበር። ንጉስ አክዓብ እና ንግስት ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት አይወዱም ነበር። አንዳንድ ነቢያትን እንኳን እንዲገደሉ አድርገዋል። ንጉሱ እና ንግስቲቱ ዝናብ እንዲዘንብ ወደ ጣዖት ጸለዩ። ነበር ግን ነቢዩ ኤልያስ ጌታ ለአመታት ዝናብ እንደማይልክ ነገራቸው።

1 ነገሥት 16፥29–3317፥118፥13

ምስል
ኤልያስ ከወታደሮች ተደብቆ

ንጉሱ እና ንግስቲቱ በኤልያስ ላይ ተቆጡ። ህይወቱ አደጋ ላይ ስለነበረ ጌታ ኤልያስን እንዲደበቅ አስጠነቀቀው።

1 ነገሥት 17፥2–3

ምስል
ኤልያስ በጅረት ማፋሰሻ አጠገብ ተንበርክኮ

ጌታ ኤልያስን ወደ ጅረት መራው እንዲሁም ምግብ እንዲያመጡለት ወፎችን ላከ። ዝናብ ባለመኖሩ ጅረቱ ደርቆ ነበር እናም ኤልያስ ውሀ አልነበረውም።

1 ነገሥት 17፥4–7

ምስል
ኤልያስ ከሴት ጋር ሲነጋገር

ጌታ ኤልያስን በሩቅ ከተማ ወደምትገኝ አንዲት ሴት መራው። ኤልያስም ውሀ እና እንጀራ ጠየቃት። ነገር ግን ለራሷ እና ለወንድ ልጇ ብቁ የሚሆን የአንድ ቀን ምግብ ብቻ ነበር ያላት።

1 ነገሥት 17፥8–12

ምስል
ኤልያስ ከአንዲት ሴት ጋር ሲነጋገር

የመጨረሻዋ ትንሽ ምግብ እንደነበረ ኤልያስ አወቀ። ብትመግበው ጌታ ዝናቡ እስኪመጣ ድረስ ለቤተሰቧ ምግብ እንደሚያቀርብ ቃል ገባላት።

1 ነገሥት 17፥13–14

ምስል
ኤልያስ፣ ሴት፣ እና ልጅ ሲመገቡ

ሴትየዋ ለኤልያስ እንጀራ ጋገረች። ከዚያም ዘይቷ እና ዱቄቷ ተባዙ። ለኤልያስም ለቤተሰቧም ለብዙ ቀናት በቂ የሆነ ምግብ ነበራት።

1 ነገሥት 17፥15–16

ምስል
ለሞተ ልጅ የምታለቅስ ሴት

አንድ ቀን የሴቲቱ ልጅ ታመመ እና ሞተ። ጌታ ለምን ይህ እንዲደርስባት እንደፈቀደ ኤልያስን ጠየቀችው።

1 ነገሥት 17፥17–20

ምስል
አንዲት ሴት ልጅን እያቀፈች

ኤልያስ ክህነት ነበረው። ልጇን ባረከው እንዲሁም ወደ ህይወት እንዲመልሰው ጌታን ጠየቀው። ልጁም እንደገና ተነፈሰ፣ እናም ሴቲቱም ኤልያስ የጌታ ነቢይ እንደሆነ አወቀች።

1 ነገሥት 17፥21–24

አትም