በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ህጻኑ ሙሴ


“ህጻኑ ሙሴ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ህጻኑ ሙሴ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፀአት 1–2

ህጻኑ ሙሴ

የወደፊቱን የእስራኤል መሪ መጠበቅ

ፈርዖን መንግስትን እየተመለከተ

የያዕቆብ ቤተሰብ በግብፅ ውስጥ ታላቅ ህዝብ ሆኑ እስራኤላውያን በሚባል ስም ይታወቁ ነበር። የግብፅ ንጉስ ፈርዖንም አንድ ቀን እስራኤላውያን በጣም ይባዛሉ እና ግብፅን ይወርሳሉ ብሎ ፈርቶ ነበር፣ ስለዚህ እስራኤላውያንን ባሪያዎቹ አደረገ።

ዘጸአት 1፥7–14

ወታደሮች ወንዝ ሲመለከቱ

ከዚያም ፈርዖን አዲስ የሚወለዱ የእስራኤል ወንድ ልጆች እንዲገደሉ አዘዘ። የእስራኤላውያን ቤተሰቦችም በጣም ፈርተው ነበር።

ዘጸአት 1፥15–22

ዮካብድ፣ ማሪያም፣ እና ህጻኑ ሙሴ በወንዝ ውስጥ

ዮካብድ የምትባል አንድ እስራኤላዊት እናት አዲስ የተወለደውን ወንድ ልጇን የምታድንበትን መንገድ አሰበች። ህጻን ልጇን በቅርጫት ውስጥ አስገብታ ቅርጫቱን በአባይ ወንዝ ዳርቻ ባለው ረዥም ሣር ውስጥ ደበቀችው። የህጻኑ እህት ማሪያም የእርሱን ደህንነት ለመጠበቅ ትከታተለው ነበር።

ዘጸአት 2፥1–4

የፈርዖን ሴት ልጅ ህጻኑን ሙሴ ይዛ

በወንዙ ውስጥ እየታጠበ ሳለች፣ የፈርዖን ሴት ልጅ ቅርጫቱን አገኘችው። አቅመ ቢስ የሆነው የእስራኤላውያን ህፃን ልጅ እያለቀሰ አየች እና እንደራሷ ልጅ ልታሳድገው ፈለገች። ማሪያም ወደ ፈርዖን ሴት ልጅ መጥታ ሕፃኑን የምትንከባከብ አንዲት እስራኤላዊት ሴት ማምጣት ትችል እንደሆነ ጠየቀች።

ዘጸአት 2፥5–6

የፈርዖን ሴት ልጅ፣ ዮካብድ፣ ማሪያም፣ እና ህጻኑ ሙሴ

ማሪያም እናቷን ዮካብድን ወደ ፈርዖን ሴት ልጅ አመጣች። ህጻኑን ትንከባከበው ዘንድ የፈርዖን ሴት ልጅ ለዮካብድ ለመክፈል ተስማማች።

ኦሪት ዘጸአት 2፥8–9

የፈርዖን ሴት ልጅ፣ ዮካብድ፣ እና ሙሴ

እስራኤላዊው ህጻን ልጅ አደገ። የፈርዖን ሴት ልጅ እንደ እራሷ ልጅ አሳደገችው። እሷም ሙሴ ብላ ጠራችው።

ዘፀአት 2፥10፡