“አብርሐም እና ሣራ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2021 (እ.አ.አ)]
“አብርሐም እና ሣራ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፍጥረት 11–15፤ 17፤ አብርሐም 1–2
አብርሐም እና ሣራ
የሰውን ልጅ ቤተሰብ ለመባረክ የተሰጠ የተስፋ ቃል
አብርሐም በዑር ከተማ ውስጥ ይኖር ነበር። በዚያም ክፉ ካህናት ለጣዖቶታቸው ሊሰዉት ፈለጉ። አብርሐም ጸለየ እናም ጌታ አዳነው።
ከዚያም ጌታ አብርሐምን እና ባለቤቱን ሣራን ከዑር እንዲወጡ እና ወደ ሩቅ አገር እንዲጓዙ አዘዛቸው። በጉዞአቸውም እንደሚባርካቸው የተስፋ ቃል ሰጣቸው።
አብርሐም እና ሣራ ጌታን አመኑ እናም ከዑር ወጥተው ሄዱ። ነገር ግን ልጆች ለመውለድ ስላልቻሉ አዝነው ነበር። ጌታም አፅናናቸው። ልጅ እንደሚወልዱም የተስፋ ቃል ሰጣቸው።
ዘፍጥረት 11፥30–31፤ 15፥1–6፤ 17፥2–16፤ አብርሐም 2፥6–9
አብርሐም ስለእርሱ ይበልጥ ለማወቅ ወደ ጌታ ጸለየ። ጌታ አብርሐምን ጎበኘው እና ራሱንም ያህዌ ብሎ ጠራ። ያህዌ ከአብርሐም ጋር ቃል ኪዳን ገባ። አብርሐም ክህነት እንደሚኖረውም የተስፋ ቃል ሰጠው። በአብርሐም ቤተሰብ በኩል የምድር ቤተሰቦች በሙሉ እንደሚባረኩም ቃል ገባለት።
አብርሐም እና ሣራ በሚጓዙበትም ጊዜ ምግብ አስፈልጓቸው ነበር። ከነዓን ተብሎ በሚጠራ አገር ውስጥ ለመኖር ሞከሩ። በዚያም ምንም ምግብ አልነበረም፤ ስለዚህ ወደ ግብፅ መሄድ ነበረባቸው። ነገር ግን በግብፅ ውስጥ መኖር ለእነርሱ አደገኛ ነበር።
አብርሐም እና ሣራ ከግብፅ ወጡ እናም በከነዓን ለመኖር ተመለሱ። ከግብፅም ምግብ እና እንስሳትን ይዘው መጡ። ከነዓንም ጌታ ለእነርሱ ቃል የገባላቸው ምድር ክፍል ነበር።
ጌታ አብርሐም ክህነት እንደሚቀበል ቃል የገባለትንም አከበረ። አንድ ቀን አብርሐም እና ሣራ መልከ ጼዴቅ ተብሎ ከሚጠራ ጻድቅ ንጉስ ጋር ተገናኙ። አብርሐምም ለእርሱ አስራት ከፈለ።
አብርሐም ከመልከ ጼዴቅ ክህነትን ተቀበለ። ይህም ነቢያቱ አዳም እና ኖኅ ተቀብለውት የነበረው አንድ አይነት ክህነት ነበር።
የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፥36–40፤ አብርሐም 1፥2–4፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥14
አብርሐም እና ሣራ በከነዓን ደስተኛ ነበሩ፤ ነገር ግን ልጅ ስላልነበራቸው አሁንም ይጨነቁ ነበር። አንድ ቀን ቤተሰባቸው እንደሚበዛ እና መላውን ምድር እንደሚባርክ ጌታ የሰጣቸውን የተስፋ ቃል መታመን ይገባቸዋል።