Scripture Stories
የአዳም እና የሔዋን ቤተሰብ


“የአዳም እና የሔዋን ቤተሰብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“የአዳም እና የሔዋን ቤተሰብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 4ሙሴ 5–6

የአዳም እና የሔዋን ቤተሰብ

ጌታን ለመከተል መምረጥ

ምስል
የአዳም እና ሔዋን ቤተሰብ

አዳምና ሔዋን ከኤድን ገነት ከወጡ በኋላ የሰማይ አባት በምድር ላይ ለእነርሱ ስላለው ዕቅድ መማራቸውን ቀጠሉ። ብዙ ልጆች ነበሯቸው እናም ስለጌታ የሚያውቁትን ሁሉ አስተማሯቸው። አንዳንዶቹ የአዳም እና ሔዋን ልጆች ጌታን ለመታዘዝ መረጡ። ነገር ግን ጥቂቶቹ አለመታዘዝን መረጡ።

ሙሴ 5፥1–126፥15

ምስል
አዳም እና ሔዋን ከልጆች ጋር፣ አዳም ቅዱሳት መጻህፍትን እየጻፈ

የአዳም እና ሔዋን ቤተሰብ የመታሰቢያ መጽሐፍን ጻፉ። የቤተሰባቸውን ታሪክ በመጽሐፉ ላይ ጻፉ፡፡ ጌታ እንዴት እንደረዳቸውም ጻፉ።

ሙሴ 6፥5–6

ምስል
ቃየን እና አቤል

ቃየን እና አቤል የአዳም እና ሔዋን ሁለት ወንድ ልጆች ነበሩ። አቤል ጌታን ይወድ ነበር እናም እርሱን ለመታዘዝ መረጠ። ቃየን ለጌታ አልታዘዘም፡፡ እሱ ማመጽን መረጠ።

ዘፍጥረት 4፥1–16

ምስል
ሰው ወደ ከተማ እየተመለከተ

የአዳም እና ሔዋን ቤተሰብ መብዛታቸውን ቀጠሉ። ብዙ ተጨማሪ ልጆች ተወለዱ። ሁሉም የመምረጥ ነጻነት ነበራቸው። ከጊዜ በኋላ አንዳንድ ሰዎች በጌታ ትእዛዛት ላይ አመፁ። ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡ እንዲያስተምሯቸው ጌታ ነብያትን ላከ።

ዘፍጥረት 4፥25–26ሙሴ 5፥136፥23

አትም