Scripture Stories
ዳንኤል እና ጓደኞቹ


“ዳንኤል እና ጓደኞቹ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ዳንኤል እና ጓደኞቹ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዳንኤል 1

ዳንኤል እና ጓደኞቹ

የንጉሱን ምግብ ለመብላት አሻፈረኝ ማለት

ምስል
ወንድ ልጆች በወታደሮች ሲወሰዱ

የባቢሎን መንግስት ኢየሩሳሌምን ድል አደረገች። ከሁሉም በላይ ብልህ እና ጠንካራ የሆኑ ጥቂት ወጣት ወንዶችን በኢየሩሳሌም ካሉት ቤተሰቦቻቸው ወሰዷቸው እና ንጉሱን እንዲያገለግሉ ወደ ባቢሎን አመጧቸው።

ዳንኤል 1፥1–4

ምስል
ወጣት ወንዶች በንጉሱ ቤተ መንግስት

ዳንኤል እና ጓደኞቹ ከእነዚህ ወጣት ወንዶች መካከል ጥቂቶቹ ነበሩ። በንጉሱ ቤተ መንግስት ውስጥ እንዲያገለግሉ እና የእርሱ ጠቢባን ሰዎች እንዲሆኑ ተመርጠው ነበር።

ዳንኤል 1፥4–6

ምስል
ምግብ እና የወይን ጠጅ

ንጉሱ ለዳኒኤል እና ጓደኞቹ ምግብ እና የወይን ጠጅ ሰጣቸው። ነገር ግን እነርሱ የንጉሱን ምግብ አይበሉም ወይም የወይን ጠጁን አይጠጡም። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚቃወም ነበር።

ዳንኤል 1፥5–8

ምስል
ወጣት ወንዶች ሲበሉ

ይህም የንጉሱን አገልጋይ ለህይወቱ እንዲፈራ አደረገው። እርሱም ዳንኤልን እና ጓደኞቹን ይንከባከብ ነበር፣ እናም የንጉሱን ምግብ ለመብላት አሻፈረኝ ካሉ ከሌሎቹ ወጣት ወንዶች በላይ ደካማ ይሆናሉ ብሎ ፈርቶ ነበር። ከዚያም ንጉሱ ተናዶ አገልጋዩን ይገድለዋል።

ዳንኤል 1፥9–10

ምስል
ዳንኤል አንድን አገልጋይ እያነጋገረ

ነገር ግን ዳንኤል በእግዚአብሔር ታመነ እናም የእርሱን ትእዛዛት ለማክበር ፈለገ። ዳንኤል አገልጋዩን ውሀ እና ጥራጥሬዎችን ለ10 ቀን እንዲሰጣቸው እና ከዚያም የእነርሱን ጤንነት ከሌሎች ወጣት ወንዶች ጤንነት ጋር እንዲያመዛዝን ጠየቀው። አገልጋዩም ተስማማ።

ዳንኤል 1፥11–14

ምስል
ዳንኤል እና ጓደኞቹ ሲያጠኑ

ከ10 ቀናት በኋላ ዳንኤል እና ጓደኞቹ ከሁሉም ሌሎች ወጣት ወንዶች በላይ ጤናማ ነበሩ። ዳንኤል እና ጓደኞቹ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ተከተሉ፣ እናም እግዚአብሔር እነርሱን በንጉሱ ቤተ መንግስት ውስጥ እጅግ በጣም ጥበበኛ ሰዎች አደረጋቸው።

ዳንኤል 1፥15–20

አትም