በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ጌታ ኤልያስን ሲያነጋግር


“ጌታ ኤልያስን ሲያነጋግር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ጌታ ኤልያስን ሲያነጋግር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

1 ነገሥት 19

ጌታ ኤልያስን ሲያነጋግር

የጌታን ድምፅ ማድመጥ

አክዓብ ከኤልዛቤል ጋር ሲነጋገር፣ ከበስተጀርባ እሳት

የበዓልን ካህናት ጌታ ድል እንዳደረገ ንጉሥ አክዓብ ለንግስት ኤልዛቤል ነገራት። ኤልዛቤል ተናደደች እናም ነቢዩን ኤልያስን እገድላለሁ አለች።

1 ነገሥት 19፥1–2

ኤልያስ ዋሻ እያገኘ

ኤልያስ ደህንነቱን ለመጠበቅ ከእስራኤል ምድር ወጣ። በጉዞው እየፆመ ለ40 ቀናት እና 40 ሌሊት ተጓዘ። ከዚያም ወደ ሲና ተራራ መጣ እና የሚደበቅበት ዋሻ አገኘ። ጌታ ኤልያስን ሊያናግረው ወደ ተራራው ጫፍ እንዲሄድ ነገረው።

1 ነገስት 19፥3፣ 8–11

ኤልያስ ንፋስን፣ የመሬት መንቀጥቀጥን እና እሳትን እየተመለከተ

ኃይለኛ ነፋስ መጣ እና በዋሻው ዙሪያ ያሉትን ድንጋዮች ሰባበራቸው። ከዚያም በኋላ የመሬት መንቀጥቀጥ ምድሩን አናወጠ። ከዚያም በኋላ እሳት ተነሳ። ኤልያስ የንፋሱን፣ የመሬት መንቀጥቀጡን እና የእሳቱን ከፍተኛ ድምፅ ሰማ። ነገር ግን የጌታ ድምፅ በጎሉት ድምጾች ውስጥ አልነበረም።

1 ነግሥት 19፥11–12

ጌታ ኤልያስን ሲያናግር

ከዚያም ኤልያስ ጸጥ ያለ፣ ትንሽ ድምፅ ሰማ። ጌታ እንደነበረ አውቆ ነበር። በዚያ ምን እያደረገ እንደነበር ጌታ ኤልያስን ጠየቀ።

1 ነገሥት 19፥12–13

ኤልያስ ጌታን እያናገረ

ራሱን ለመጠበቅ እንደተደበቀ ኤልያስ ተናገረ። ነቢያቱ ሁሉ ተገድለው ነበር፤ ህዝቡም ጌታን ንቀውት ነበር።

1 ነገሥት 19፥14

ኤልያስ ኤልሳዕን እያገኘ

ጌታ ኤልያስን አጽናናው እና አሁንም ጌታን የሚያመልኩ ብዙ እስራኤላውያን እንዳሉ ነገረው። ጌታም ኤልያስ ወደ ቤቱ እንዲመለስ እና ሌላ ነቢይ እንዲያዘጋጅለት ጠየቀው። የዚህ አዲስ ነቢይ ስም ኤልሳዕ ነበር።

1 ነገሥት 19፥15–18