በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ወጣቱ ዳዊት


“ወጣቱ ዳዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ወጣቱ ዳዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

1 ሳሙኤል 16

ወጣቱ ዳዊት

እረኛ ልጅ ንጉስ እንዲሆን ተጠራ

ሳሙኤል እየተጓዘ

አዲስ ንጉስ እንዲያገኝ ጌታ ነቢዩ ሳሙኤልን ላከው። በወቅቱ ንጉሥ የነበረው ሳኦል ጌታን መከተል አቁሞ ነበር። ሳሙኤል ወደ ቤተልሔም ተጉዞ እሴይ የተባለን ሰው እንዲያገኝ ጌታ ነገረው። አዲሱ ንጉስ ከእሴይ ወንድ ልጆች አንዱ ይሆናል።

1 ሳሙኤል 16፥1–5

ሳሙኤል እና የእሴይ ልጆች

የእሴይ ታላላቅ ወንድ ልጆች ረጃጅም እና ጠንካሮች ነበሩ። ነገር ግን በሚያያቸው ሁኔታ መሰረት እንዳይፈርድ ጌታ ለሳሙኤል ነገረው።

1 ሳሙኤል 16፥6–10

ሳሙኤል ከእሴይ ጋር ሲነጋገር

ሳሙኤል ሌሎች ወንዶች ልጆች እንዳሉት እሴይን ጠየቀው። እሴይም ትንሹ ልጁ ዳዊት በጎቹን እየጠበቀ እንደነበር ነገረው። ዳዊት ወደ ሳሙኤል እንዲመጣ ተደረገ።

1 ሳሙኤል 16፥11

ሳሙኤል እና እሴይ እረኛውን ልጅ ዳዊትን እየተመለከቱ

ዳዊት ከወንድሞቹ ያነሰ እና እረኛ ልጅ ነበር። ነገር ግን ጌታ ስለዳዊት ቁመና ግድ አልነበረውም። የዳዊት ልብ በእምነት የተሞላ እንደነበር ጌታ ያውቅ ነበር። ዳዊት ንጉስ እንደሚሆን ለሳሙኤል ነገረው። ሳሙኤል ዳዊትን ባረከው ዳዊት ንጉስ እንዲሆን የጌታ መንፈስ አዘጋጀው።

1 ሳሙኤል 16፥12–13