Scripture Stories
የግብፅ መቅሰፍቶች


“የግብፅ መቅሰፍቶች፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“የግብፅ መቅሰፍቶች፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘጸአት 4–5፤ 7–12

የግብፅ መቅሰፍቶች

ፈርዖን ከጌታ በተቃራኒ ያደረጋቸው ምርጫዎች

ምስል
ሙሴ እና አሮን ከፈርዖን ጋር ሲነጋገሩ

ሙሴ እግዚአብሔርን አመነ እናም ወደ ግብፅ ተመለሰ። ሙሴ እና ወንድሙ አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እስራኤላውያንን ነፃ እንዲለቅና ከግብፅ እንዲወጡ ጠየቁት። ፈርዖን ተቆጥቶ ነበር እናም እምቢ አለ። እንዲያውም እስራኤላውያን የበለጠ እንዲሠሩ አስገደዳቸው።

ዘጸአት 4፥10–165፥1–18

ምስል
ወንዝ ወደ ደም ሲለወጥ

ፈርዖን ጌታን ባለመስማቱ፣ ግብፃውያን በአስከፊ መቅሰፍቶች ተረገሙ። በመጀመሪያ፣ በግብፅ ያለው ውሃ ሁሉ ወደ ደም ተቀየረ። ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲለቅ ፈርዖንን እንደገና ጠየቀው፣ ፈርዖን ግን አይሆንም አለ።

ዘጸአት 7፥14–25

ምስል
እንቁራሪቶች በግብፃውያን ላይ እየዘለሉ

በመቀጠልም፣ ጌታ እንቁራሪቶችን ወደ ግብፅ ላከ። እነርሱም በሁሉም ቦታ ነበሩ። ፈርዖንም እንቁራሪቶቹ ከሄዱ እስራኤላውያንን እለቃለሁ አለ። ጌታ እንቁራሪቶቹ እንዲሄዱ አደረገ፣ ፈርዖን ግን እስራኤላውያንን አልለቀቀም። ከዚያም ጌታ ቅማል እና ዝንቦችን ላከ።

ዘጸአት 8፥1–32

ምስል
ግብፃውያን እና የሞቱ እንስሳት

በመቀጠልም፣ ሁሉም የግብፃውያን እርሻ እንስሳት ሞቱ፣ ነገር ግን ከእስራኤላውያን እንስሳት መካከል አንዳቸውም አልሞቱም። ከዚያ ግብፃውያን በሰውነቶቻቸው ላይ የሚያሰቃዩ ቁስሎች መጡባቸው።

ዘጸአት 9፥3–12

ምስል
በረዶ እና የእሳት አውሎ ነፋስ ግብፅን ሲያጠፉ

ታላቅ አውሎ ንፋስ ከበረዶ እና ከእሳት ጋር ወደ ግብፅ መጣ። ይህም አስከፊ ውድመት አስከተለ።

ዘጸአት 9፥22–35

ምስል
አንበጣዎች ሰብሎችን ሲበሉ

ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቀቀም። ከዚያም ጌታ አንበጣዎችን ላከ፣ እናም እነሱ የሰዎችን ምግብ በሙሉ በሉ።

ዘጸአት 10፥12–20

ምስል
ፈርዖን

ከዚያም ለሦስት ቀናት ጨለማ ሆነ። በብዙዎቹ መቅሰፍቶች ወቅት፣ ፈርዖን መቅሰፍቱ የሚቆም ከሆነ እስራኤላውያንን ለመልቀቅ ቃል ገብቶ ነበረ፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ ጊዜ ቃሉን ያጥፍ ነበር።

ዘፀአት 10፥21–23፣ 27

ምስል
ሙሴ እና ቤተሰብ

ከዘጠኝ የተለያዩ መቅሰፍቶች በኋላ፣ ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቀቀም። ጌታ ለሙሴ ሌላ አስከፊ መቅሰፍት እንደሚመጣ ነገረው። ነፃነታቸውን እየጠበቁ ሳሉ፣ ጌታ እስራኤላውያን መርቶና ጠብቆ ነበር።

ዘጸአት 11፥4–712፥1–13

አትም