“የምድር አፈጣጠር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“የምድር አፈጣጠር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፍጥረት 1–2፤ ሙሴ 1–3፤ አብርሐም 3–5
የምድር አፈጣጠር
ለሰማይ አባት ልጆች የሚያምር ቤት
የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር በሰማይ የደህንነትን ዕቅድ አቀረበ። ሁላችንም በደስታ ጮኸን! ስጋዊ አካልን ለመቀበል ወደ ምድር መምጣት እንችል ነበር። በምድር ላይ ሳለን፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተልን እንማራለን። ጌታ የእግዚአብሔርን መመሪያዎች በመከተል ምድርን ፈጠረ።
ዘፍጥረት 1፥1፤ ኢዮብ 38፥4–7፤ ሙሴ 1፥32–33፤ 2፥1፤ አብርሐም 3፥22–27
በመጀመሪያው ቀን፣ ጌታ ብርሀንን ከጭለማ ለየ። ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፣ ጨለማውንም ሌሊት አለው።
ዘፍጥረት 1፥3–5፤ ሙሴ 2፥3–5፤ አብርሐም 4፥1–5
በሁለተኛው ቀን፣ ውሃዎቹን በሰማይ ባሉ ደመናዎች እና በምድር ላይ ባሉ ውቅያኖሶች መካከል ከፈላቸው።
ዘፍጥረት 1፥6–8፤ ሙሴ 2፥6–8፤ አብርሐም 4፥6–8
በሶስተኛው ቀን፣ ጌታ ታላቅ ውቅያኖሶችን እና ደረቅ ምድርን ፈጠረ። ውሀዎቹን ባህር እና ደረቁን መሬት ምድርብሎ ጠራቸው። ምድርንም በአበቦች፣ በፍሬዎች፣ በዕጽዋት፣ እና በዛፎች አሳመረ።
ዘፍጥረት 1፥9–13፤ ሙሴ 2፥9–13፤ አብርሐም 4፥9–13
በአራተኛው ቀን፣ በቀን እንዲበራ ፀሐይን ፈጠረ። ከዚያም ጨረቃን እና ከዋክብትን በሌሊት እንዲበሩ ፈጠረ።
ዘፍጥረት 1፥14–19፤ ሙሴ 2፥14–19፤ አብርሐም 4፥14–19
በአምስተኛው ቀን፣ ጌታ በባህር ውስጥ ያሉትን ዓሦች እና በሰማይ ያሉትን ወፎች ፈጠረ። ፍጥረታትን እንዲባዙ ባረካቸው እንዲሁም ዓሦቹ ባህሩን እንዲሞሉ ባረካቸው።
ዘፍጥረት 1፥20–23፤ ሙሴ 2፥20–23፤ አብርሐም 4፥20–23
በስድስተኛው ቀን፣ በምድር ላይ እንስሳትን ፈጠረ፣ የተወሰኑት የሚራመዱ ጥቂቶቹ የሚሳቡ ነበሩ።
ዘፍጥረት 1፥24–25፤ ሙሴ 2፥24–25፤ አብርሐም 4፥24–25
የሰማይ አባት እና ጌታ በስድስተኛው ቀን ወደ ምድር ወረዱ። ወንድና ሴት በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠሩ። የሰማይ አባትም እርስ በርሳቸው እንክብካቤ እንዲሰጣጡ እና ልጆች እንዲወልዱ ነገራቸው። ወንድና ሴትም መሬቱንና እንስሳቱን እንዲንከባከቡ ሀላፊነት ተሰጣቸው።
ዘፍጥረት 1፥26–27፤ ሙሴ 2፥26–27፤ አብርሐም 4፥26–31፤ 5፥7–8
የሰማይ አባት በፈጠሩት ሁሉ ደስተኛ ነበር። በሰባተኛው ቀን ከሥራቸው ሁሉ አረፉ። ምድር ውብና በሕይወት የተሞላች ነበር።