Scripture Stories
ነቢዩ ኢሳይያስ


“ነቢዩ ኢሳይያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ኢሳይያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ኢሳይያስ 6–7፤ 953–54

ነቢዩ ኢሳይያስ

ስለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢቶች

ምስል
ኢሳይያስ በጌታ ሲጠራ

እስራኤላውያን ብዙ ጊዜ ተሸንፈው ነበር እናም ጌታ እንዲጠብቃቸው ፈለጉ። አንድ ቀን በቤተመቅደስ ውስጥ ጌታ ስለኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ህዝቡን እንዲያስተምር ኢሳይያስ የተባለን ሰው ጠራ። ኢሳይያስ ሕዝቡን ወደዳቸው እንዲሁም ክርስቶስ እንዴት ሊያድናቸው እንደሚችል አስተማራቸው።

ኢሳይያስ 6፥1–8

ምስል
ኢሳይያስ ስለኢየሱስ መወለድ ሲተነብይ

ኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝቡን ከኃጢአት ለማዳን አንድ ቀን እንደሚመጣ ኢሳይያስ አወቀ። ነገር ግን ሁሉም እርሱን እንደ አዳኛቸው አይቆጥሩትም። ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እንደማያምኑ ስላወቀ ኢሳይያስ በጣም አዘነ።

ኢሳይያስ 6፥9–137፥1453፥1–9

ምስል
ኢሳይያስ ስለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሲጽፍ

ነገር ግን ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ትንቢትም ተናግሯል። ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመለሳል እንዲሁም የምድር ሁሉ ንጉሥ ይሆናል። እንደገና ይመጣል እንዲሁም ደግነትን እና ሰላምን ለዘለአለም በማምጣት የአባቱን ዕቅድ ይፈጽማል። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛቸው እንደሆነ ሁሉም እንደሚያውቁ ኢሳይያስ ተናግሯል።

ኢሳይያስ 9፥6–754፥1–10

አትም