በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኤልሳዕ ንዕማንን ፈወሰ


“ኤልሳዕ ንዕማንን ፈወሰ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ኤልሳዕ ንዕማንን ፈወሰ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

2 ነገሥት 5

ኤልሳዕ ንዕማንን ፈወሰ

እንዴት ታላቅ ተአምር ቀላል እምነትን ተከተለ

ንዕማን ታሞ በአልጋ ላይ

በሩቅ ሶርያ ውስጥ ንዕማን የሚባል ሰው ይኖር ነበር። በሶሪያ ጦር ውስጥ ታላቅ ሻምበል ነበር። ንዕማን ግን የሥጋ ደዌ የሚባል አሳማሚ የቆዳ በሽታ ነበረው።

2 ነገሥት 5፥1

እስራኤላዊቷ ብላቴና ከንዕማን ሚስት ጋር እያወራች

የንዕማን ሚስት አገልጋይ የእስራኤላዊት ብላቴና ነበረች። ብላቴናዋ በእግዚአብሔር እምነት ነበራት። ንዕማን ነቢዩ ኤልሳዕን መጎብኘት ከቻለ፣ ንዕማን ከበሽታው ይፈወሳል አለች።

2 ነገሥት 5፥2–4

ንዕማን ነቢዩ ኤልሳዕን ለማግኘት ሲጓዝ

ንዕማን ኤልሳዕን ለማግኘት ረጅም እርቀት ተጓዘ። ንዕማን በታላቅ ተአምር እንደሚድን አስቦ ነበር።

2 ነገሥት 5፥5–8

ንዕማን ከኤልሳዕ አገልጋይ ጋር እያወራ

ንዕማን ከአገልጋዮቹ፣ ከፈረሶቹ፣ እና ከሠረገሎች ጋር ወደ ኤልሳዕ ቤት መጣ። ኤልሳዕ የጌታን መመሪያ ለንዕማን እንዲሰጥ ባሪያውን ላከ። በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ለሰባት ጊዜ ከታጠበ ጌታ ንዕማንን ይፈውሰዋል።

2 ነገሥት 5፥9–10

ንዕማን በወንዝ ዳር ሆኖ ሲያማርር

ንዕማን ተቆጣ ምክንያቱም የጌታ ነቢይ እንዲመጣ እና በፍጥነት እንዲፈውሰው ፈልጎ ነበረ። የዮርዳኖስ ወንዝ በሶሪያ እንዳሉ ታላላቅ ወንዞች ጥሩ አይደለም በማለት ንዕማን ቅሬታውን ገለጸ።

2 ነገሥት 5፥11–12

አገልጋዩ ከንዕማን ጋር በወንዝ ዳር ሲያወራ

ነገር ግን የንዕማን አገልጋዮች ንዕማን ለምን እንዲህ ያለ ቀላል ሥራ እንደማይሠራ ጠየቁ። ለንዕማን ትርጉም ባይኖረውም፣ የጌታ ነቢይ ይህን እንዲያደርገው ጠይቆት ነበር።

2 ነገሥት 5፥13

ንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ተፈውሶ

ንዕማን ኩራቱን አቁሞ አገልጋዮቹን አደመጠ። በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ራሱን ለሰባት ጊዜ አጠበ። ከዚያም ኤልሳዕ እንደተናገረው ጌታ ንዕማንን ፈወሰው። ንዕማን ኤልሳዕ ነቢይ መሆኑን እና ጌታ እውን መሆኑን አወቀ።

2 ነገሥት 5፥14–15