በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነቢይቷ ዲቦራ


“ነቢይቷ ዲቦራ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢይቷ ዲቦራ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

መሣፍንት 4–5

ነቢይቷ ዲቦራ

እስራኤል በጌታ እንዲታመን የረዳቸ መሪ

ነቢይቷ ዲቦራ

ዲቦራ በጌታ መንፈስ የተነሳሳች ታማኝ የእስራኤላውያን መሪ የሆነች ነቢይት ነበረች። የእርሷ ህዝብ የጌታን ትእዛዛት መጠበቅ አቁመው ነበር፤ እናም ከነዓናውያን ገዟቸው። ከሃያ ዓመታት በኋላ እስራኤላውያን ጌታ እንዲረዳቸው መፀለይ ጀመሩ።

መሣፍንት 4፥1–5

ዲቦራ እየፀለየች

ጌታ ጸሎታቸውን ሰማ። ከከነዓናውያን ጋር ለመዋጋት አንድ የእስራኤላውያን ሠራዊት እንድታሰባስብ ለዲቦራ ነገራት።

መሣፍንት 4፥6

ዲቦራ ከወታደሮች ጋር እየተነጋገረች

የከነዓናውያን ሠራዊት ብዙ ወታደሮችና ሠረገሎች ነበሩት። ይህም የእስራኤላውያንን ሠራዊት አስፈራቸው፤ ዲቦራን ግን አላስፈራትም። ጌታ እንደሚረዳቸው ታውቅ ነበረ፡፡

መሣፍንት 4፥3፣ 7

ባርቅ ዲቦራን እንድትመጣ ሲጠይቃት

ባርቅ የእስራኤላውያን ሰራዊት መሪ ነበር። መዋጋት አልፈለገም ነበር። ነገር ግን ዲቦራ ከሠራዊቱ ጋር ከሄደች ጌታ ይጠብቀናል ብሎ አሰበ። ዲቦራ ለመሄድ ተስማማች። እንዲት ሴት የከነዓናውያን ሰራዊት መሪ የሆነውን ሲሣራን እንደምታሸንፍ ተነበየች።

መሣፍንት 4፥8–9።

ዲቦራ እና ሰራዊት በተራራ ጫፍ ላይ

የእስራኤል ሠራዊት በተራራ ላይ ተሰበሰበ፤ ከነዓናውያንም በሸለቆው ውስጥ ተሰበሰቡ። ዲቦራ ባርቅን ከተራራው እንዲወርድ ነገረችው። ጌታ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ቃል ገባች።

መሣፍንት 4፥12–14

ሰረገሎች በማዕበል እየተጠራረጉ

ጌታ ዝናብ ሰደደ፣ የከነዓናውያን ሰረገሎች በውሃ ውስጥ እየተጠራረጉ ተወሰዱ። ብዙ ከነዓናውያን በወንዙ ውስጥ ሰጠሙ፣ ነገር ግን ሲሳራ ሸሸ።

መሣፍንት 4፥15፣ 175፥4–5፣ 19–22

ኢያኤል ሲሣራን ወደ ድንኳን እየጋበዘች

ኢያኤል የተባለች አንዲት ሴት በአቅራቢያው በሚገኝ ድንኳን ውስጥ ትኖር ነበር። ሲሣራ ሲሮጥ አየችው እና በድንኳኗ ውስጥ እንዲደበቅ ነገረችው። ኢያኤል የከነዓናውያን ጦር መሪ መሆኑን ታውቅ ነበር እናም ብዙ ሰዎችን እንዳይጎዳ ገደለችው።

መሣፍንት 4፥15–21

ዲቦራ ሰላማዊ ከተማን እየተመለከተች

የዲቦራ ትንቢት እውን ሆነ። ሲሣራ በጀግና ሴት ተሸነፈ። እስራኤላውያንን ጌታ እንዴት እንዳዳናቸው እንዲያስታውሱ ለመርዳት ዲቦራ አንድ መዝሙር ዘመረች። እስራኤላውያን ትእዛዛቱን ጠበቁ እናም ለ40 ዓመታት በሰላም ኖሩ፡፡

መሣፍንት 5፥1፤ 24–27፤ 31