በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ስለ ብሉይ ኪዳን


“ስለ ብሉይ ኪዳን፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ስለ ብሉይ ኪዳን፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ስለ ብሉይ ኪዳን

ከረጅም ጊዜ በፊት እግዚአብሔር ለልጆቹ የሰጣቸው ቃል ኪዳኖች

የቅድመ-ምድር ህይወት ምሳሌያዊ ማሳያ

የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ክፍል ብሉይ ኪዳን ነው። እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ ከረጅም ጊዜ በፊት ነበር። በእርሱ ላይ እምነት እንዲኖረን የሚረዱን ታሪኮች አሉት። በምድር ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው የሰማይ አባት ቤተሰብ አካል እንደሆነ እና እርሱም ልጆቹን እንደሚወድ ያስተምረናል።

ዘዳግም 7፥7–9ኢሳይያስ 45፥10–12

አዳም እና ሔዋን በገነት ውስጥ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ያህዌ እና ጌታ ተብሎ ተጠርቷል። እርሱም የሰማይ አባት መመሪያዎችን ይከተላል። ከአዳም እና ሔዋን ዘመን ጀምሮ፣ የሰማይ አባት ለነቢያቱ እንዲናገር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልኳል። የአንድ ነቢይ ቃላት እውነት መሆናቸውን እንድናውቅ ይረዳን ዘንድ የሰማይ አባት መንፈስ ቅዱስን ይልካል።

ዘፀአት 6፥ 2–32 ዜና 20፥20አሞጽ 3፥72 ጴጥሮስ 1፥21ሙሴ 2፥1

የአዳም ትውልድ

ጌታ ለነቢዩ አብርሃምና ለባለቤቱ ለሣራ ቤተሰቦቻቸው እንደሚበዙ እና ዓለምን ሁሉ እንደሚባርኩ ቃል ገባላቸው። የልጅ ልጃቸው ያዕቆብ አገር ለመሆን የበቃ ትልቅ ቤተሰብ ነበረው። እነርሱ የእስራኤል ቤት ወይም እስራኤላውያን ተብለው ይጠሩ ነበር። ነቢያት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመጣበትን ጊዜ በጉጉት እንዲጠብቁ አስተምረዋቸዋል።

ዘፍጥረት 15፥5–617፥1–8ዘዳግም 18፥15ኢሳያስ 7፥14

ሰዎች ቀስተ ደመናን እየተመለከቱ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ብዙ ታሪኮች ጌታ ለእስራኤላውያን የገባቸውን የተስፋ ቃላት እንዴት እንደጠበቀ ያሳያሉ።

ዘፍጥረት 9፥13–17; ኤርምያስ 11፥4–5ዕብራዊያን 11፥1–35

ሙሴ ለሰዎች በትር እያሳየ

እስራኤላውያን ነቢያትን ሲሰሙ እና ትእዛዛትን ሲጠብቁ ጌታ ረድቷቸዋል። ሳይታዘዙ በቀሩ ጊዜ ሊረዳቸው አልቻለም።

ዘዳግም 11:26–28ኢዮብ 36፥11–12

ልጆች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

እናንተ የሰማይ አባት ቤተሰብ አካል ናችሁ። የሰማይ አባት ደግ ነው እንዲሁም ይወዳችኋል። ለእናንተ እቅድ አለው። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት እንደገና ከሰማይ አባት ጋር ለመኖር መመለስ ትችላላችሁ። ልክ እስራኤላውያን ተምረው እንደነበረው እናንተም በጌታ ለማመን እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ መምረጥ ትችላላችሁ።

ዘፀአት 15፥2ዘዳግም 4፥315፥10ሙሴ 1፥39