Scripture Stories
የጌዴዎን ሰራዊት


“የጌዴዎን ሰራዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“የጌዴዎን ሰራዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

መሣፍንት 6–7

የጌዴዎን ሰራዊት

በጦር ሜዳ ላይ በጌታ መታመን

ምስል
ምድያማውያን ምግብ እየሰረቁ

የእስራኤል ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ተባረኩ። በኋላ ግን ለጌታ አለመታዘዝን መረጡ። እርሱን እንዲያስታውሱ ለመርዳት፣ ጠላቶቻቸው ምድያማውያን ምግባቸውን እና እንስሶቻቸውን እንዲወስዱ ጌታ ፈቀደ። እስራኤላውያን ተርበው ነበር፤ ስለሆነም ጌታን አስታወሱና ለእርዳታ ወደ እርሱ ጸለዩ።

መሣፍንት 6፥1–7

ምስል
መልአክ ጌዴዎንን ሲያነጋግር

ጌዴዎን ከድሃ ቤተሰብ የመጣ ሰው ነበር። እስራኤልን ነፃ ለማውጣት እርሱን ለመጥራት ጌታ መልአኩን ላከ። ጌዴዎን ጌታ የመረጠው ለምን እንደሆነ ተገረመ።

መሣፍንት 6፥11–15

ምስል
በጌዴዎን የተናደዱ ሰዎች ከፈረሰው ጣዖት አጠገብ

እስራኤላውያን የሐሰት አማልክትን የሚያመልኩባቸውን ቦታዎች እንዲያጠፋ ጌታ ለጌዴዎን ነገረው።። ጌዴዎን እንደታዘዘው ሲያደርግ ሕዝቡ ተቆጣ።

መሣፍንት 6፥25–27

ምስል
የጌዴዎን አባት እርሱን ከተቆጡ ሰዎች ሲጠብቅው

እስራኤላውያን ጌዴዎንን ለመግደል ፈለጉ። የጌዴዎን አባት ግን እንዳይጎዱት አሳመናቸው። ጌዴዎን በደህና ተጠብቆ ነበር።

መሣፍንት 6፥28–32

ምስል
ጌዴዎን እየፀለየ

ጌዴዎን እስራኤልን ነፃ ላወጣ እችላለሁ ብሎ አላሰበም። በምድያም ሰራዊት ውስጥ ከ135 ሺህ በላይ ወታደሮች ነበሩ። ጌታ ግን ለጌዴዎን ጥበብ እና ጥንካሬን ሰጠው።

መሣፍንት 6፥13–168፥10

ምስል
ወታደሮች ሰራዊቱን ትተው ሲሄዱ

ጌታ እስራኤላውያን በራሳቸው ሳይሆን በእርሱ ጥንቃሬ ማሸነፍ እንደሚችሉ እንዲያውቁ ፈልጎ ነበር። ምንም እንኳን እስራኤል 32 ሺህ ወታደሮች ብቻ የነበሩት ቢሆንም፣ ማንኛቸውንም የፈሩ ወታደሮች ወደ ቤት እንዲልክ ጌታ ጌዴዎንን ጠየቀው። 22 ሺህ ወደ ቤታቸው ከሄዱ በኋላ፣ እስራኤላውያን 10 ሺህ ወታደሮች ቀሯቸው።

መሣፍንት 7፥2–3

ምስል
ወታደሮች ውሃ እየጠጡ

ጌታ 10 ሺህ አሁንም በጣም ብዙ ወታደሮች ናቸው አለ። ጌዴዎን ሠራዊቱን ይዞ ወደ ውሃው እንዲወርድ ነገረው። በአፋቸው በቀጥታ ከውኃው የሚጠጡ ወደ ቤት ይላካሉ። ውሃውን ለመጠጣት እጃቸውን የተጠቀሙት ሊቆዩ ይችላሉ። አሁን 300 ወንዶች ብቻ ቀሩ።

መሣፍንት 7፥4–7

ምስል
የእስራኤል ወታደሮች በምድያም ሰፈር ዙሪያ መለከትና መብራት ይዘው

በስተመጨረሻ፣ እስራኤላዊያን ለመዋጋት ዝግጁ ሆኑ። ጌታ ለጌዴዎን ምድያማውያንን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል አሳየው። ጌዴዎን እነሱን ለማስፈራራት ሰራዊቱ መለከቶችን እና መብራቶችን እንዲጠቀሙ ነገራቸው። ጫጫታው እና መብራቶቹ ምድያማውያንን በጣም ግራ ስላጋቧቸው እርስ በእርሳቸው መዋጋት ጀመሩ። ከዛም ጮሁ እና ሸሹ።

መሣፍንት 7፥16–22

ምስል
ጌዴዎን ወታደሮችን እየመራ

ጌዴዎን ጌታን ስላመነ እስራኤላውያን በ300 ወታደሮች ብቻ ትልቁን የምድያማውያን ሠራዊት አሸነፉ። ጌታ የእስራኤልን ሕዝብ ነፃ አወጣ፡፡

መሣፍንት 7፥23–25

አትም