“ኖኅ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ኖኅ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፍጥረት 6–9፤ ሙሴ 8
ኖኅ እና ቤተሰቡ
መርከብ፣ የጥፋት ውኃ፣ እና የጌታ ቃል ኪዳኖች
ኖኅ እና ቤተሰቡ ጌታን ታዘዙ። ሁሉም ሌሎች ሰዎች በጣም ኃጢያተኞች ነበሩ። ህዝቡ ንስሃ ካልገቡ ጌታ በጥፋት ውኃ ምድርን እንደሚሸፍን ለኖኅ ነገረው።
ኖኅ ጌታ እንደወደዳቸው እንዲሁም ንስሐ እንዲገቡ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖራቸው እንደሚፈልግ ህዝብን አስተማረ። እነርሱም አላደመጡም።
ኖኅ ህዝቡ ንስሐ ባለመግባታቸው አዘነ። ጌታ የኖኅ መርከብ የተባለውን ትልቅ መርከብ እንዲሠራ ነገረው። መርከቡ በጥፋት ውኃው ወቅት የኖኅን ቤተሰብ ደህንነት ይጠብቃቸዋል።
የኖኅ ቤተሰብ ምግብ ወደ መርከቡ አመጡ። ጌታ ቢያንስ ከእያንዳንዱ እንስሳት አይነቶች ሁለት ሁለቱን ወደ ኖኅ ላከ። እንስሳቱም ወደ መርከቡ ገቡ፣ እናም ከሰባት ቀናት በኋላ ዝናቡ መጣል ጀመረ።
ልክ ጌታ እንዳስጠነቀቀውም፣ ለ40 ቀናት እና ለ40 ለሊት ዘነበ። ምድርም በጥፋት ውኃ ተሸፈነች።
የኖኅ ቤተሰብ እና በመርከቡ ውስጥ ያሉት ሁሉም እንስሳት በደህና በውኃው ላይ ተንሳፈፉ።
የጥፋት ውኃው ሲያልቅም የኖኅ መርከቡ በደረቅ መሬት ላይ አረፈች። ኖኅ እና ቤተሰቡ ጌታን ለማምለክ መሠዊያ ሠሩና ስለጠበቃቸውም አመሰገኑት። ጌታ ምድርን ዳግመኛ በጥፋት ውኃ በፍጹም እንደማያጥለቀልቅ ቃል ገባ። የገባውን ቃል ለማስታወስ ቀስተ ደመና ላከ።