“ነቢዩ ሔኖክ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ነቢዩ ሔኖክ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፍጥረት 5፤ ሙሴ 6–7
ነቢዩ ሔኖክ
በጌታ ያለ እምነት እንዴት አንድን ከተማ እንዳዳነ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡ ንስሐ እንዲገቡ እንዲነግራቸው ሔኖክን ጠየቀው። ሔኖክ ግን በደንብ መናገር እንደማይችል አሰበ። ህዝቡ አያደምጡኝም ብሎ ፈርቶ ነበር።
አንዳንድ ሰዎች ሔኖክ ያስተማረውን ባይወዱትም፣ ጌታ ሔኖክን ለማጠናከር እና ለመጠበቅ ቃል ገባለት።
የጌታ ተስፋ ለሔኖክ ድፍረት ሰጠው። ሔኖክ ጌታን በመታዘዝ ህዝቡን በኃይል አስተማረ። ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ንስሀ ስለመግባት፣ ስለጥምቀት፣ እና ስለመንፈስ ቅዱስ አስተማረ። አንዳንድ ሰዎች ሔኖክን አምነው ጌታን መከተል ፈለጉ።
ሔኖክ ለማጥመቅ ከእግዚአብሔር ስልጣን ነበረው። ሔኖክን ያመኑ ሰዎች በሙሉ ተጠመቁ እንዲሁም ወደ ጌታ ቀረቡ። እርስ በእርስ እንክብካቤ ይሰጣጡ ስለነበር ማንም ድሃ አልነበረም። በፍቅር እና በጽድቅ አብረው ስለኖሩ ፅዮን ተብለው ተጠሩ።
አንድ ቀን ጌታ በምድር ላይ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ለሔኖክ በራእይ አሳየው። ሔኖክ የኢየሱስ ክርስቶስን ህይወት፣ ሞት እና ትንሳኤ አየ። በመጨረሻዎቹ ቀናት ወንጌል ዳግም እንደሚመለስ ሔኖክ ተረዳ። በተጨማሪም የኢየሱስን ዳግም ምጽዓት አየ።
በመጨረሻም፣ በፅዮን ከተማ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ሔኖክን አምነው ንስሐ ገቡ። እርስ በእርስ እንክብካቤ ይሰጣጡ ስለነበር እና በሰላም ስለኖሩ፣ ጌታ ከእርሱ ጋር አብረው እንዲኖሩ ወሰዳቸው።