“ሙሴ በሲና ተራራ ላይ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ሙሴ በሲና ተራራ ላይ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘጸአት 19–20፤ 24፤ 31–34፤ ዘዳግም 4–7
ሙሴ በሲና ተራራ ላይ
ጌታን እንዲያስታውሱ ህዝቡን መርዳት
ሙሴ እና እስራኤላውያን በምድረበዳ ውስጥ ተጓዙ። ሲና ተራራ ወደሚባል ተራራ መጡ።
ሙሴ ጌታን ለማናገር ወደ ተራራው ወጣ። ጌታ ከእስራኤላውያን ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር እንደሚፈልግ ለሙሴ ነገረው።
እስራኤላውያን ወደ ሲና ተራራ ግርጌ መጡ፤ ጌታም የጢስ ደመና ተራራውን እንዲከበው አደረገ። ጌታ በደመና ውስጥ ነበር። ከእስራኤላውያን ጋር ተነጋገረ እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጣቸው። እርሱ ሲናገር ተራራው ተናወጠ።
ዘጸአት 19፥16–19፤ 20፥1–17፤ ዘዳግም 4፥12–13፣ 33፤ 5፥4–5
እስራኤላውያን ፈርተው ነበር፡፡ ጌታ የሚፈልገውን ሊነግራቸው ይችል ዘንድ ከጌታ ጋር እንዲነጋገር ሙሴን ጠየቁት።
ሙሴ የጌታን ትምህርቶች የበለጠ ለመቀበል አሮንን እና 70 እስራኤላውያን ሽማግሌዎችን ወደ ተራራው ወሰደ። ጌታ ለእነርሱ ተገለጠ።
ከዚያም ሽማግሌዎቹን ትቶ ወደ ተራራው ከፍ ብሎ እንዲወጣ ጌታ ለሙሴ ነገረው። ሙሴ የታዘዘውን አደረገ። ጌታ ህጉን እና ትእዛዛቱን በድንጋይ ጽላቶች ላይ ለመፃፍ ጣቱን ተጠቀመ። ለ40 ቀናት፣ ጌታ ለሙሴ ብዙ ነገሮችን አስተማረው።
ሙሴ በሲና ተራራ ላይ በነበረበት ወቅት የእስራኤል ሕዝብ እርሱን በመጠበቅ ደከሙ። በግብፅ ያደርጉት እንደነበረው ይሰግዱለት ዘንደ ሐውልት እንዲሠራላቸው ለአሮን ነገሩት። አሮን ወርቃቸውን ሁሉ ሰበሰበ እና የጥጃ ሐውልት ሠራ።
እስራኤላውያን የወርቅ ጥጃን አመለኩ እናም መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ከግብፅ ነፃ ያወጣቸው ጌታ ሳይሆን የወርቅ ጥጃ እንደሆነ ተናገሩ።
እስራኤላውያን ጣዖትን እያመለኩ እና እርሱን እየረሱ እንደነበር ጌታ አውቋል። ሙሴም እንዲመለስ እና ህዝቡ ንስሐ እንዲገቡ እንዲነግራቸው አዘዘው።
ሙሴ ከሲና ተራራ ወረድ እና እስራኤላውያን የወርቅ ጥጃ ሲያመልኩ አየ። በጣም ተቆጥቶ ነበር። ሕዝቡ ጌታ የጻፈውን ሕግና ትእዛዛት ለመታዘዝ ዝግጁ አልነበሩም። ሙሴ ጽላቶቹን ሰበረ እንዲሁም የወርቅ ጥጃውን አፈረሰ። ንስሐ እንዲገቡና እውነተኛ አምላካቸውን እንዲያስታውሱ እስራኤላውያንን ረዳቸው።
ሙሴ እስራኤላውያንን ይቅር እንዲላቸው እና ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳኖችን እንዲገባ ጌታን ጠየቀ። ሙሴ እንደሚመራቸውና እንደሚያስተምራቸው ቃል ገባ።
ጌታ አዲስ የድንጋይ ጽላቶችን እንዲሠራና ወደ ሲና ተራራ እንዲመለስ ሙሴን ጠየቀው። ጌታ ከእስራኤላውያን ጋር አዲስ ቃል ኪዳን ገባ እንዲሁም አሥርቱን ትእዛዛቱን ሰጣቸው።