Scripture Stories
እስራኤላውያን በምድረበዳ ውስጥ


“እስራኤላውያን በምድረበዳ ውስጥ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“እስራኤላውያን በምድረበዳ ውስጥ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘጸአት 16

እስራኤላዊያን በምድረበዳ ውስጥ

በጌታ ላይ መደገፍን መማር

ምስል
እስራኤላውያን እያጉረመረሙ

እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ ብዙም ሳይቆይ በቂ ምግብ የለንም በማለት አጉረመረሙ። በምድረበዳ ከመራብ ይልቅ በግብፅ ባሪያ መሆን ይሻላል አሉ።

ዘጸአት 16፥1–3

ምስል
እስራኤላውያን መና እየሰበሰቡ

እርሱን እንዲያምኑ እስራኤላውያንን ለማስተማር፣ ጌታ በየቀኑ ይሰበስቡት ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ላከላቸው። እንጀራውን መና ብለው ጠሩት። ጣእሙ እንደ ማር ነበር። ጌታ በሰንበት፣ በሳምንቱ ሰባተኛው ቀን መና አልላከም ነበር። ስለዚህ በስድስተኛው ቀን፣ ለሁለት ቀናት በቂ መና እንዲሰበስቡ ነገራቸው።

ዘጸአት 16፥4–5፣ 14–31።

ምስል
እስራኤላውያን ድርጭት እየሰበሰቡ

ለተወሰነ ጊዜም፣ ጌታ እስራኤላውያን እንዲበሏቸው ድርጭትን ልኳል። ጠዋት ላይ መና ሰበሰቡ እናም በምሽት ላይ ድርጭቶችን ሰበሰቡ። ጌታ እስራኤላውያን በእርሱ መታመንን እንዲማሩ ፈልጎ ነበር። በዚህ መንገድ እነርሱን በምድረበዳ ውስጥ ተንከባከባቸው።

ዘጸአት 16፥11–13

አትም