በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ያዕቆብ እና ዔሳው


“ያዕቆብ እና ዔሳው፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ያዕቆብ እና ዔሳው፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 25–27

ያዕቆብ እና ዔሳው

ሁለት ወንድሞች እና አንድ ብኵርና መብት

ዔሳው እና ያዕቆብ ሲሰሩ

ይስሀቅ እና ርብቃ፣ ያዕቆብ እና ዔሳው የተባሉ መንታ ወንድ ልጆች ነበሯቸው። ዔሳው የተካነ አዳኝ ነበር። ያዕቆብ ቀለል ያለ ኑሮ ይኖር ነበር እንዲሁም ጌታንም ይከተል ነበር።

ዘፍጥረት 25፥20–28

ዔሳው እና ያዕቆብ

ዔሳው በመጀመሪያ የተወለደ ነበር። የበኩር ልጅ አብዛኛውን ጊዜ የብኵርና በረከቱን ከአባቱ ይቀበላል። የብኵርና መብት ማለትም ቤተሰቡን መምራት እንዲሁም ቤተሰቡን ለመንከባከብ የሚረዳ ተጨማሪ መሬት እና እንስሳት ማግኘት ማለት ነው። ዔሳው ግን ከቤተሰቡ የበለጠ ስለራሱ ያስብ ነበር፤ እንዲሁም ለወላጆቹ እና ለጌታ ታዛዥ አልነበረም።

ዘፍጥረት 25፥25፣ 3226፥34–35

ያዕቆብ ለዔሳው ምግብ ሲሰጠው

አንድ ቀን ዔሳው ከአደን ተመለሰ። በጣም ተርቦ ነበር እና ያዕቆብ እንዲመግበው ለመነው። ጌታ ዔሳው ብቁ ስላልነበረ ያዕቆብ የብኵርና መብት በረከቱን እንዲያገኝ ፈልጎ ነበር። ያዕቆብም የብኵርና መብቱን በጥቂት ምግብ እንዲሸጥለት ዔሳውን ጠየቀው። ዔሳውም በመስማማት የብኵርና መብቱን ለያዕቆብ ሸጠለት።

ዘፍጥረት 25፥23፣ 29–34ዕብራውያን 11፥20

ርብቃ እና ይስሀቅ

ርብቃ እና ይስሀቅ ለልጆቻቸው የሚበጀውን ፈለጉ። ዔሳው ጌታ የፈለገውን ሳይሆን እራሱ የፈለገውን በማድረግ በመቀጠሉ እነርሱ አዝነው ነበር።

ዘፍጥረት 26፥34–35

ይስሀቅ ከዔሳው ጋር ሲነጋገር

ይስሀቅ አረጀ እናም አይነ ስውር ሆነ። ከመሞቱ በፊትም፣ እንዲበላ እና እንዲደሰት ዔሳው እንስሳ እንዲያድንና እንዲያበስልለት ጠየቀው።

ዘፍጥረት 27፥1–4

ርብቃ ዔሳውን ስትመለከት

ርብቃም ይስሐቅ የብኵርና በረከትን የሚሰጥበት ጊዜ እንደ ሆነ አወቀች።

ዘፍጥረት 27፥5

ርብቃ ከያዕቆብ ጋር ስትነጋገር

ርብቃም ዔሳው ከመመለሱ በፊት ምግብ እንድታበስል ያዕቆብ ሁለት እንስሳትን እንዲያመጣ ጠየቀችው። ከዚያም ያዕቆብ በረከቱን ይቀበላል።

ዘፍጥረት 27፥6–17

ይስሀቅ ለያዕቆብ በረከት ሲሰጥ

ያዕቆብ እንደ ዔሳው አለባበስ ለብሶ ምግብን ለአባቱ አመጣ። ይስሀቅ ለያዕቆብ የበኵርና መብት በረከቱን ሰጠው። ዔሳው ሲመለስም በያዕቆብ በጣም ተናድዶ ነበር። ነገር ግን የብኵርና መብቱ ለያዕቆብ የተላለፈው የጌታን ትእዛዛት ስለጠበቀ እና ዔሳው ባለመጠበቁ ነበር።

ዘፍጥረት 27፥18–29