ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ህዳር 14–20 (እ.አ.አ)። አሞጽ፤ አብድዩ፦ “እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ”


“ህዳር 14–20 (እ.አ.አ)። አሞጽ፤ አብድዩ፦ ‘እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ፣‘” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [(2021) እ.አ.አ]

“ህዳር 14–20 (እ.አ.አ)። አሞጽ፤ አብድዩ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ፊት በጨለማ ክፍል ውስጥ በበሩ ሻማዎች ፈክቶ

የሕይወት እንጀራ፣ በክሪስ ያንግ

ህዳር 14–20 (እ.አ.አ)

አሞጽአብድዩ

“እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ”

መንፈስ ቅዱስ ለእርሶ ብቻ በታሰቡ የእግዚአብሔር ቃላት ውስጥ ባሉ መልዕክቶች አዕምሮዎትን እና ልቦትን ሊከፍት ይችላል። በዚህ ሳምንት ጌታ ምን እንዲማሩ የሚፈልግ ሆኖ ይሰማዎታል?

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

እግዚአብሔር ለሁሉም ህዝቦች “በረከት” እንዲሆኑ የአብርሐምን ዘር የቃልኪዳን ህዝቦቹ አድርጎ መረጠ ( ኦሪት ዘፍጥረት 12፥2–3ይመልከቱ)። ነገር ግን በምትኩ፣ በአሞጽ አገልግሎት ጊዜ ብዙዎቹ የቃልኪዳን ህዝቦች የአምልኮ ተግባራቸውን ባዶ እና ትርጉም የለሽ በማድረግ ድሆችን እየጨቆኑ እና ነብያቶችን ችላ እያሉ ነበር ( አሞጽ 2፥6–16ይመልከቱ)። በእርግጥ በዙሪያቸው ያሉት አገራትም ጭምር በታላቅ ሃጢያቶች ጥፋተኝነት ውስጥ ነበሩ ( አሞጽ12፥1–5ይመልከቱ)፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሰዎች ያ ፈፅሞ ማስተባበያ አልነበረም ( አሞጽ 3፥2ይመልከቱ)። ስለዚህ እግዚአብሔር ለእስራኤል መንግስት ንስሃን እንዲሰብክ ከይሁዳ አሞጽ የሚባልን እረኛ ላከ። ከዛ በኋላ የይሁዳ መንግስት ቢፈርስም እንኳን እግዚአብሔር ህዝቦቹን እንደሚሰበስብ እና እንደገና እንደሚባርክ በነብዩ አብድዩ አማካኝነት አወጀ። የቃልኪዳን ህዝቦቹ ከእግዚአብሔር ተለዩ፣ ነገር ግን ለዘላለም እንደማይጣሉ ሁለቱም ነብያት መሰከሩ። እግዚአብሔር ሚስጥሩን ለአገልጋዮቹ ለነብያት ሲገልፅ፣ ( አሞጽ 3፥7ይመልከቱ)፣ ከእርሱ ጋር የገባነውን ቃልኪዳኖች ለመጠበቅ አሁንም እኛን ለመርዳት እንደሚፈልግ ምልክት አድርገን ልንወስደው እንችላለን።

ስለአሞጽ እና ስለአብድዩ መጽሐፎች የበለጠ መረጃ ለማገኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “አሞጽ” እና “አብድዩ” የሚሉትን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

አሞጽ 3፥1–87፥10–15

እግዚአብሔር እውነትን በነብያቶቹ አማካኝነት ይገልፃል።

አሞጽ 3፥3–6፣ ውስጥ ነብዩ አሞጽ ብዙ የመንስኤ እና የውጤት ምሳሌዎችን አቀረበ፦አንበሳ የሚነጥቀውን ነገር ስለሚያገኝ፣ አንበሳ ያጓራል፤ የወፍ ወጥመድ በመጠመዱ ምክንያት፣ ወፍ ይያዛል። (በ ቁጥር6፣ ውስጥ “ያደረገው” የሚለው ቃል በጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ውስጥ “ያወቀው” ወደሚል መቀየሩን ያስተውሉ [ አሞጽ 3፥6፣ የግርጌ ማስታወሻ]።) በ ቁጥሮች 7–8፣ ውስጥ አሞጽ ይህን አመክንዮ ለነብያቶች ተግባራዊ አደረገ። አንድን ነብይ እንዲተነብይ ምክንያት የሚሆነው ምንድን ነው? አሞጽ 7፥10–15ን ሲያነቡ ስለነብያቶች ሌላ ምን ይማራሉ? አሁንም ድረስ “እግዚአብሔር ምስጢሩን ለባሪያዎቹ ለነበያት [ስለሚገልፅ]” ለምን አመስጋኝ እንደሆኑ ያሰላስሉ (አሞጽ 3፥7)። ይህ እውነት ስለእግዚአብሔር ምን ይጠቁሞታል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥3821፥4–835፥13–14ይመልከቱ።

አሞጽ 4–5

“እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ።”

አሞጽ 4፥6–13ን ሲያነቡ እግዚአብሔር በእስራኤል ሰዎች ላይ የላከውን ፍርዶች ያስተውሉ። እነዚህ ጥቅሶች ከእነዚህ ከእያንዳንዱ ልምዶች በኋላ እግዚአብሔር ይከሰታል ብሎ ተስፋ ስላደረገው ነገር ምን ይጠቁማሉ? ( ሔለማን 12፥3ይመልከቱ)። በቅርብ ስላጋጠሞት ፈተና ያስቡ። ፈተናዎት በእግዚአብሔር ባይላክም እንኳን እርሱን ለመሻት እንዴት እድሎችን እንደሚሰጦት ያሰላስሉ።

አሞጽ 5፥4፣ 14–15ን ያንብቡ እና በፈተናዎት ወቅትም እንኳን እግዚአብሔርን በሚሹበት ሰዓት (ቁጥር15) እርሱ እንዴት “ሩህሩህ” እንደሆነ ያሰላስሉ።

የዶናልድኤል. ሀልስቶርምን፣ “Turn to the Lord፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2010 (እ.አ.አ)፣ 78–80 ይመልከቱ።

አሞጽ 8፥11–12

የእግዚአብሔር ቃል የመንፈስ ርሃብን እና ጥማትን ያረካል።

የመንፈስ ርሃብ እና ጥማት ወቅቶች ሁላችንንም ያጋጥማል፣ ነገር ግን ርሃብ እና ጥማታችንን ለማርካት የሆነ ነገርን ለመፈለግ (አሞጽ 8፥12) “ከባሕር እስከ ባሕር [መቅበዝበዝ]” አይጠበቅብንም። ያንን የመንፈስ ርሃብ ምን እንደሚያረካው እናውቃለን እናም በእግዚአብሔር ቃል በሰፊው ተባርከናል። አሞጽ 8፥11–12ን ሲያነቡ ርሃብ ለምን ያለእግዚአብሔር ቃል ከመኖር ጋር መልካም ንፅፅር እንደሆነ ያስቡ። በ ማቴዎስ 5፥6ዮሐንስ 6፥26–352ኛ ኔፊ 9፥50–5132፥3ኢኖስ 1፥4–8፣ ውስጥ ምን ተጨማሪ ሃሳቦችን ያገኛሉ?

የጀፍሪአር. ሆላንድ፣ “He Hath Filled the Hungry with Good Things፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 1997 (እ.አ.አ)፣ 64–66፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ክህደት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።

የወጣቶች ቡድን ከቤተመቅደስ ፊት ቆመው

የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራን በመስራት በጽዮን ተራራ ላይ አዳኞች መሆን እንችላለን።

አብድዩ 1፥21

“አዳኞች … በጽዮን ተራራ ላይ” የተባሉት እነማን ናቸው?

ፕሬዘደንት ጎርደንቢ. ሂንክሊ “አዳኞች በጽዮን ተራራ ላይ” ስለሚለው ሃረግ ከቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ ጋር በማያያዝ አንድ የሚያስኬድ ትርጉምን ሰጡ፦ [በቤተመቅደስ ውስጥ] በትክክል በጽዮን ተራራ ላይ አዳኞች እንሆናለን። ይህ ምን ማለት ነው? ልክ አዳኛችን ለሁሉም ሰዎች በውክልና መስዋትነት ሕይወቱን እንደሰጠ እና ይህን በማድረግ አዳኛችን ስለሆነ እኛም በውክልና የቤተመቅደስ ስራ ውስጥ ስንሳተፍ በትንሽ መልኩ አዳኞች እንሆናለን። በሞት ለተለዩ ሰዎች በእነሱ ምትክ በምድር ላይ ባሉ ሰዎች ካልተደረገ በስተቀር ሌላ ምንም መደረግ ስለማይችል እንደአዳኞች እንሆናለን” (“Closing Remarks፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር. 2004 (እ.አ.አ)፣105)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

አሞጽ 3፥7ከቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ብዙ የቅርብ መልዕክቶችን መከለስ እና እግዚአብሔር በእሱ አማካኝነት ለቤተሰቦ ምን እየገለፀ እንዳለ መወያየት ይችላሉ። ቤተክርስቲያኗን የሚመራት ነብይ መኖሩ የሚጠቅመው ለምንድን ነው ? እውነተኛ ነብይ እንደሆነ ያወቅነው እንዴት ነው? ምክሩን ለመከተል ምን እያደረግን ነው?

አሞጽ 5፥4ቤተሰብዎ በቤትዎ ውስጥ ይህን ጥቅስ የያዘ ፖስተር መስቀል ይችላሉ። እግዚአብሔርን መሻት ምን ማለት ነው? እንዴት ነው የምንሻው? ስንሻው ምን ዓይነት በረከቶችን እንቀበላለን? እግዚአብሔርን ስለመሻት ስለሚያስተምሩ ሌሎች ምንባቦች የቤተሰብ አባላት እንዲያካፍሉ እና እንዲወያዩ መጋበዝ ይችላሉ ለምሳሌ እንደ ማቴዎስ7፥7–8ኤተር 12፥41፤ እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥63

አሞጽ 8፥11–12ልጆች በዚህ ጥቅሶች ውስጥ ካሉ ሃረጎች ጋር የሚሄዱ ትወና በመፍጠር ሊደሰቱ ይችላሉ። አካላችን ሲራብ እና ሲጠማ ምን እናደርጋለን? መንፈሳችን ሲራብ እና ሲጠማ ምን እናደርጋለን? “The Great Apostasy” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪድዮ መመልከት እና የተመለሰው ወንጌል እንዴት የመንፈስ ርሃባችንን እንደሚያጠግብ መነጋገር ይችላሉ።

አብድዩ 1፥21“አዳኞች … በጽዮን ተራራ ላይ” መሆን ማለት ምን ማለት ነው? (ለአንድ የሚያስኬድ ማብራሪያ፣ የፕሬዝዳንት ጎርደንቢ. ሂንክሊን መግለጫ በ “Ideas for Personal Scripture Study” ውስጥ ይመልከቱ።) የትኞቹ ቅድመ አያቶቻችን የማዳን ስርዓቶችን ይፈልጋሉ? እነሱን ለመርዳት ምን እናደርጋለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “ኦ እግዚአብሔር ስለነብይህ እናመሰግንሃለን፣” መዝሙር፣ ቁጥር 19።

የግል ጥናትን ማሻሻል

መንፈስን ለመጋበዝ እና ትምህርትን ለመማር መዝሙርን ይጠቀሙ። መዝሙርን ማዳመጥ ወይም ማንበብ የወንጌልን መርሆዎች ለመማር ሊረዳዎት ይችላል። ለምሳሌ በሕይወት ያሉ ነብያቶች ላይ ያለን ታላቅ እምነት ለማነሳሳት “ኦ እግዚአብሔር ስለ ነብይህ እናመሰግንሃለንን” (መዝሙር፣ ቁጥር 19) ማዳመጥ ወይም ማንበብ ይችላሉ። ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 22ን ይመልከቱ።)

ሳንቶ ዶሚንጎ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ቤተመቅደስ

ሳንቶ ዶሚንጎ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ቤተመቅደስ