ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ህዳር 7–13 (እ.አ.አ)። ሆሴዕ 1–6፤ 10–14፤ ኢዮኤል፦ “በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ”


“ህዳር 7–13 (እ.አ.አ)። ሆሴዕ 1–6፤ 10–14፤ ኢዮኤል፦ ‘በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ህዳር 7–13 (እ.አ.አ)። ሆሴዕ 1–6፤ 10–14፤ ኢዮኤል፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ሙሽሪት እና ሙሽራ በቤተመቅደስ ግቢ ውስጥ

ህዳር 7–13 (እ.አ.አ)

ሆሴዕ 1–610–14ኢዮኤል

“በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ”

የሆሴዕ እና ኢዮኤል የጥናቶ አካል እንዲሆን መንፈስን ይጋብዙ። መንፈስ በልቦ እና በአዕምሮዎ የሚያነሳሳቸውን መልዕክቶች ማስታወሻ ይያዙ።

ያሳደረብዎትን ስሜት መዝግቡ

እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ቃል ኪዳን ጥልቅ እና ትርጉም ያለው ስለነበረ እግዚአብሔር ከጋብቻ ጋር አነፃፀረው። ቃል ኪዳኑ ልክ እንደ ጋብቻ ዘላለማዊ ቁርጠኝነትን፣ የጋራ ልምዶችን፣ ሕይወትን በጋራ መገንባትን፣ ልዩ ታማኝነትን እና ከሁሉም በላይ የሙሉ ልብ ፍቅርን አካቷል። እንደዚህ ዓይነት ታማኝነት ከከፍተኛ ግምቶች ጋር—እና ካለመታመን አሳዛኝ ውጤቶች ጋር መጣ። እስራኤላውያን ቃል ኪዳናቸውን ባለማክበራቸው የገጠሟቸውን የተወሰኑ ውጤቶች እግዚአብሔር በነብዩ ሆሴዕ አማካኝነት ገለፀ። ይሁን እንጁ የእርሱ መልዕክት “ታማኝ ስላልሆናችሁ ለዘላለም አልቀበላችሁም” አልነበረም። በምትኩ “መልሼ እጋብዛችኋለሁ” ነበር ( ሆሴዕ 2፥14–15ይመልከቱ)። እግዚአብሔር እንዲህ አወጀ፣ “በጽድቅና ለእኔ አጭሻለሁ” (ሆሴዕ 2፥19)። “ዓመፃቸውን እፈውሳለሁ፣ በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ” (ሆሴዕ 14፥4)። ቃል ኪዳናችንን በፍቅር እና በታማኝነት ለመኖር ስንሻ ዛሬ እርሱ የሚሰጠን ይህንኑ ተመሳሳይ መልዕክት ነው።

ኢዮኤል ተመሳሳይ መልዕክትን አካፈለ፦ “አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፣ ቁጣው የዘገየ፣ ምሕረቱም የበዛ፣ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ” (ኢዮኤል 2፥13)። “እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፣ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል” (ኢዮኤል 3፥16)። ሆሴዕን እና ኢዮኤልን ሲያነቡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለዎትን ግንኙነት ያሰላስሉ። የእርሱ ታማኝነት ለእርሱ ታማኝ ለመሆን እንዴት እንደሚያነሳሳዎት ያስቡ።

ስለሆሴዕ እና ኢዮኤል አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሆሴዕ” እና “ኢዮኤል” የሚሉትን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሆሴዕ1–314

እግዚአብሔር ሁሌ ወደ እርሱ እንድመለስ ይጋብዘኛል።

የሆሴዕ ሚስት፣ ጎሜር፣ ለእርሱ ታማኝ አልነበረችም እናም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ስለእነሱ እና ከእርሱ ጋር ስለገቡት ቃልኪዳን እንዴት እንደተሰማው ለማስተማር ወደዚህ አሳዛኝ ክስተት ጠቆመ። ሆሴዕ 1–3ን ሲያነቡ እግዚአብሔር ከቃልኪዳን ህዝቦቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዴት እንደሚመለከት ያሰላስሉ። ልክ እንደ እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ታማኝ ስላልሆኑባቸው መንገዶች እንዲሁም እርሱ እንዴት እንደረዳዎት ማሰላሰል ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ሆሴዕ 2፥14–23 እና ሆሴዕ14 ስለእግዚአብሔር ፍቅር እና ምህረት ምን ያስተምሮታል? ለእርሱ ያለዎትን ፍቅር እና ታማኝነት እንዴት ነው የሚያሳዩት?

እንዲሁም የዲተርኤፍ. ኡክዶርፍን፣ “Point of Safe Return፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2007 (እ.አ.አ)፣ 99–101 ይመልከቱ።

ምስል
አንድ ሴት በመሬት ላይ ተቀምጣ አንድ ሰው እጁን በእራሷ ላይ አድርጎ

እስራኤልን የምትወክለው ሃጥያተኛዋ ጎሜር በእግዚአብሔር ምህረት ተሰጣት። ምስል በዴብ ሚናርድ፣ ከ goodsalt.com፣ ፍቃድ የተገኘ

ሆሴዕ 6፥4–7ኢዮኤል 2፥12–13

ለእግዚአብሔር ያለ ታማኝነት በውስጥ ሊሰማ ይገባል፣ በውጪ ብቻ መገለፅ አይገባውም።

ህዝቡ የእንስሳት መስዋዕቶችን እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር አዘዞ ነበር። ነገር ግን በሆሴዕ ዘመን የነበሩ ሰዎች ያንን ህግ ቢከተሉም እንኳን ይበልጥ ጠቃሚ የነበሩትን ትዕዛዛት እየጣሱ ነበር ( ሆሴዕ 6፥4–7ይመልከቱ)። እግዚአብሔር “ከመስዋዕት ይልቅ ምህረትን፣ ከሚቃጠልም መስዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወድዳለሁና” ሲል ምን ማለት ይመስሎታል? (ሆሴዕ 6፥6)። ጽድቅ ልክ እንደ ደመና ወይም ጤዛ ነው ማለት ምን ይመስሎታል? ጽድቃችን ምን መሆን አለበት? ( ኢሳይያስ 48፥181ኛ ኔፊ 2፥9–10ይመልከቱ)።

በተጨማሪም ማቴዎስ 9፥10–1312፥1–8 ን በማንበብ በአገልግሎቱ ወቅት አዳኙ ሆሴዕ 6፥6 ን እንዴት እንደተጠቀመ ለማየት ይችላሉ። እነዚህ ምንባቦች የሆሴዕን ቃላት ለመረዳት እንዴት ረዱዎት?

ኢዮኤል 2፥12–13ን ሲያነቡ ልብስን መቅደድ የሃዘን ወይም የቁጭት መገለጫ ባህል እንደነበር ማወቅ ሊረዳ ይችላል (ለምሳሌ፣ 2ኛ ዜና መዋዕል 34፥14–21፣27ይመልከቱ)። ልባችንን መቅደድ ልብሳችንን ከመቅደድ እንዴት ነው የሚለየው?

ኢሳይያስ 1፥11–17ማቴዎስ 23፥231ኛ ዮሐንስ 3፥17–18ይመልከቱ።

ኢዮኤል2

“መንፈሴን በስጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ።”

ኢዮኤል ስለ “የጌታ ቀን” ሲተነብይ “የጨለማና የጭጋግ ቀን”፣ “ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ” (ኢዮኤል 2፥1–2፣11)ብሎ ገለፀው። እስራኤል በታሪኳ ሁሉ ብዙ ታላቅ እና አስከፊ ቀናት ገጥሟታል እንዲሁም የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝቦች ወደፊት የበለጠ ያጋጥማቸዋል። እግዚአብሔር በ ኢዮኤል 2፥12–17ውስጥ ስለሰጠው ምክር ምን አስደነቆ? እንዲሁም በ ኢዮኤል 2፥18–32ውስጥ ቃል የተገቡትን በረከቶች ያስተውሉ። በ ቁጥሮች 27–32 ውስጥ ቃል የተገቡት በረከቶች በተለይ በ ኢዮኤል2፣ በተገለፁት ቀናት ውስጥ እንዲሁም በእኛም ቀን ጨምሮ ለምን ጠቃሚ ይሆናሉ?

እግዚአብሔር “መንፈ[ሱን] በስጋ ለባሽ ላይ አፈስሳለሁ” ሲል ምን ማለት ይመስሎታል? (ኢዮኤል 2፥28)። በ ኢዮኤል 2፥28–29 ውስጥ ያሉት ትንቢቶች እየተከናወኑ ያሉት እንዴት ነው? ( የሐዋርያት ሥራ 2፥1–21የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥41ይመልከቱ።)

በፕሬዚዳንት ረስልኤም ኔልሰን የተሰጡትን እነዚህን ቃላት ሊያሰላስሉ ይችላሉ፦ “በሚመጡት ቀናት ውስጥ ያለመንፈስ ቅዱስ ምሪት፣ ጥቆማ፣ ማፅናናት እና ዘለቄታዊ ተፅዕኖ በመንፈሳዊ መትረፍ የሚቻል አይሆንም” (“Revelation for the Church, Revelation for Our Lives፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣96)። መገለጥ ለመንፈሳዊ ደህንነታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የግል መገለጥ የመቀበል ችሎታዎን እንዴት መጨመር ይችላሉ?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሆሴዕ 2፥19–20እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላለው የቃልኪዳን ግንኙነት ለመግለፅ የጋብቻ ዘይቤያዊ ንግግርን ተጠቀመ ( ቅዱሳን መጻህፍት መምሪያን፣ “ሙሽራ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ)። ጋብቻ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ቃልኪዳኖች ለምን ጥሩ ምሳሌ እንደሆነ ቤተሰቦ መወያየት ይችላሉ። ሆሴዕ 2፥19–20 እግዚአብሔር ስለእኛ እንዴት እንደሚሰማው እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? ከእርሱ ጋር ላለን ቃልኪዳኖች እንዴት ታማኝ መሆን እንችላለን?

ሆሴዕ 10፥12ልጆች ሰዓትን በመሳል እና በቀኑ በተለያዩ ሰዓታት ውስጥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉበትን መንገዶች በማቀድ ሊደሰቱ ይችላሉ።

ኢዮኤል 2፥12–13ስለ ኢዮኤል 2፥12–13፣ ለማውራት ቤተሰቦን ለመርዳት የአዳኙን ፎቶ በክፍሉ አንድ ጎን ላይ እንዲሁም ሃጢያት የሚለውን ቃል ደግሞ በተቃራኒው ማስቀመጥ ይችላሉ። የቤተሰብ አባላት ወደ ምልክቱ እንዲዞሩ እና ከዛ “በሙሉ ልባ[ችን]” ወደ አዳኙ እንድንዞር የሚረዱንን ነገሮች ሲያካፍሉ በየተራ ወደ አዳኙ እንዲዞሩ ይጋብዙ። የቤተሰብ አባላት፣ እንቅስቃሴዎችን፣ ስራን፣ ትምህርት ቤትን እና ግንኙነቶችን ጨምሮ ስለሁሉም የሕይወታቸው ገጽታዎች እንዲያስቡባቸው ያበረታቱ።

ኢዮኤል 2፥28–29መንፈስ በላያችን ላይ “[መፍሰስ]” ማለት ምን ማለት ሊሆን ይችላል? ምናልባት የሆነ ፈሳሽ በማፍሰስ እና ከጠብታ ወይም ከመንጠባጠብ ጋር በማነፃፀር ማሳየት ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “ወደ ኢየሱስ ኑ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 117።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ትምህርቱን ያስተምሩ። “ልጆች የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት እንዲማሩ ለመሰብሰብ እድሉን መቼም አይጡ። እንደዚህ ዓይነት ወቅቶች ከጠላት ሙከራዎች ጋር ሲነፃፀሩ ጥቂት ናቸው” (ሄንሪቢ. አይሪንግ፣ “The Power of Teaching Doctrine፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 1999 (እ.አ.አ)፣ 74)።

ምስል
ኢየሱስ በበር መግቢያ ላይ ቆሞ

ወደ እኔ ኑ፣ በኬሊ ፐፍ

አትም