ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ህዳር 28–ታህሳስ4 (እ.አ.አ)። ናሆም፤ ዕንባቆም፤ ሶፎንያስ፦ “መንገዱ ዘላለማዊ ነው”


“ህዳር 28–ታህሳስ4 (እ.አ.አ)። ናሆም፤ ዕንባቆም፤ ሶፎንያስ፦ ‘መንገዱ ዘላለማዊ ነው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ህዳር 28–ታህሳስ4 (እ.አ.አ)። ናሆም፤ ዕንባቆም፤ ሶፎንያስ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ክዋክብትን ወደ ላይ ሲመለከት

“መንገዱ ዘላለማዊ ነው” (ዕንባቆም 3፥6)። በመጀመሪያ ቃል ነበር፣ በኢቫ ቲሞቲ

ህዳር 28–ታህሳስ4 (እ.አ.አ)

ናሆምዕንባቆምሶፎንያስ

“መንገዱ ዘላለማዊ ነው”

ቅዱሳን መጽሐፍትን በሕይወት ዘመን ሙሉ ሊያጠኑ ይችላሉ ሆኖም አዲስ ግንዛቤዎችን በድጋሜ ያገኛሉ። ሁሉንም ነገር አሁኑኑ መረዳት እንዳለቦት አይሰማዎት። ዛሬ የሚፈልጉትን መልዕክቶች ለመገንዘብ እርዳታ ለማግኘት ይጸልዩ።

ያሳደረብዎትን ስሜት መዝግቡ

ብዙውን ጊዜ ብሉይ ኪዳንን ማንበብ ማለት ስለጥፋት የተነገሩ ትንቢቶችን ማንበብ ማለት ነው።። የእርሱ ፍርዶች በነሱ ላይ እንሆደነ ክፉዎችን ለማስጠንቀቅ ጌታ በተደጋጋሚ ነብያትን ጠራ። የናሆም፣ የዕንባቆም እና የሶፎንያስ አግልግሎቶች መልካም ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህ ነብያት በወቅቱ ጠንካራ እና ኃያል የመሰሉትን—የነነዌን፣ የባቢሎንን አንዲሁም የኢየሩሳሌምን ከተሞች ውድመት በአስፈሪ ዝርዝር ተነበዩ። ነገር ግን ያ ከሺዎች ዓመታት በፊት ነበር። ዛሬ እነዚህን ትንቢቶች ማንበብ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ምንም እንኳን እነዚያ ኩራተኞች እና ክፉ ከተሞች ቢወድሙም፣ ኩራት እና ክፋት አሁንም አለ። በዛሬው ዓለም ውስጥ አንዳንድ ጊዜ በጥንት ነብያት በተወገዙ ክፋቶች እንደተከበብን ሊሰማን ይችላል። በልቦቻችን ውስጥም እንኳን ዱካቸው ሊሰማን ይችላል። እነዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ጌታ ስለኩራት እና ክፋት እንዴት እንደሚሰማው ይገልፃሉ እንዲሁም ከእነዚህ ክፋቶች መመለስ እንደምንችል ያስተምራሉ። ምናልባት ያ የጥንት ትንቢቶችን ዛሬ የምናነብበት አንዱ ምክንያት ነው። ናሆም፣ ዕንባቆም፣ ሶፎንያስ እና ሌሎችም የጥፋት ነበያቶች ብቻ አልነበሩም—የነፃ መውጣትም ነብያት ነበሩ። የጥፋቱ መግለጫዎች ወደ ክርስቶስ ኑ እና ምህረቱን ተቀበሉ “እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ … ጽድቅንም ፈልጉ፣ ትህትናንም ፈልጉ” በሚሉ የቁጣ ግብዣዎች ይገለፃሉ (ሶፎንያስ 2፥3)። ይህ የጌታ የጥንት መንገድ ነበር፣ እንዲሁም ዛሬም የእርሱ መንገድ ነው። “መንገዱ ዘላለማዊ ነው” (ዕንባቆም 3፥6)።

ስለእነዚህ መጽሐፍት ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ናሆም፣” “ዕንባቆም፣” እና “ሶፎንያስ” የሚሉትን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ናሆም1

እግዚአብሔር ሃያል እና መሐሪ ነው።

የናሆም ተልእኮ እስራኤሎችን ስለበታተነው እና ይሁዳን በጭካኔ ስላጠቃው የእብሪተኛው የአሴሪያ ኢምፓየር ዋና ከተማ—የነነዌን ውድመት መተንበይ ነበር። ናሆም የእግዚአብሔርን ቁጣ እና አቻ የሌለው ኃይል በመግለፅ ጀመረ፣ ነገር ግን ስለእግዚአብሔር ምህረት እና መልካምነትም ተናገረ። በ ምዕራፍ1 ውስጥ እያንዳንዳቸውን እነዚህን ባህርያት—እና ሌላ ያስተዋሉትን የጌታ ባህርያት ለመገንዘብ የረዱዎትን ቁጥሮች ለመለየት ያስቡ። ስለጌታ እነዚህን እያንዳንዱን ነገሮች ማወቅ ለምን ጠቃሚ ይመስሎታል?

አንዳንዶች “እግዚአብሔር መልካም ነው” (ናሆም 1፥7) የሚለውን ትምህርት “እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል” (ናሆም 1፥2) ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር ለማስታረቅ ሊከብዳቸው ይችላል። በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ የአልማ ልጅ ኮሪአንተን “ሃጢያተኞችን በመቅጣት የእግዚአብሔርን ፍትህ [አስመልክቶ]” (አልማ 42፥1)ተመሳሳይ ጥያቄዎች ነበሩት። ስለእግዚአብሔር ምህረት እና ከእርሱ ፍትህ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ የበለጠ ለመማር አልማ ለኮሪአንተን የሰጠውን ምላሽ በ አልማ42ውስጥ ያንብቡ።

ምስል
የዓለት ምሽግ

“እግዚአብሔር መልካም ነው፣ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው” (ናሆም 1፥7)።

ዕንባቆም

የጌታን ፍቃድ እና ጊዜ ማመን እችላለሁ።

ነብያቶችም ቢሆኑ አንዳንድ ጊዜ ስለጌታ መንገዶች ጥያቄዎች አሏቸው። በይሁዳ ክፋት በተንሰራፋበት ጊዜ የኖረው ዕንባቆም ጥያቄዎችን ለጌታ በማቅረብ መዝገቡን ጀመረ ( ዕንባቆም 1፥1–4ይመልከቱ)። የዕንባቆምን ችግርች እንዴት ያጠቃልሉታል? ተመሳሳይ ስሜቶች ኖሮት ያውቃልን?

ጌታ ለዕንባቆም ጥያቄዎች ይሁዳን ለመቅጣት ከለዳውያንን (ባቢሎናውያኖችን) እንደሚልክ በመናገር መልስ ሰጠ ( ዕንባቆም 1፥5–11ይመልከቱ)። ነገር ግን ዕንባቆም ጌታ “ክፉው [ባቢሎን] የበለጠ ጻድቅ [ይሁዳ] የሆነውን ሰው እንዲገድል” ሲፈቅድ ኢፍታዊ ስለሚመስል ተቸግሮ ነበር ( ቁጥር 12–17ይመልከቱ)። በ ዕንባቆም 2፥1–4 ውስጥ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሲኖሮት ጌታን ለማመን ምን የሚያነሳሳ ነገር አገኙ?

ዕንባቆምምዕራፍ3 ለእግዚአብሔር የምስጋና እና በእርሱ ስላለ እምነት የመገለጫ ጸሎት ነው። ከ ቁጥር 17–19ውስጥ ካሉት የዕንባቆም ቃላት ያስገረሞት ምንድነው? የእነዚህ ጥቅሶች ቃና ከ ዕንባቆም 1፥1–4በምን ይለያል? ሕይወት ኢ-ፍታዊ ሲመስልም በእግዚአብሔር ታላቅ እምነትን እንዴት እንደሚያዳብሩ ያሰላስሉ።

ዕብራውያን 10፥32–3911ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–6፤ የሮበርትዲ. ሄልስ፣ “Waiting upon the Lord: Thy Will Be Doneን፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2011 (እ.አ.አ)፣ 71–74 ይመልከቱ።

ሶፎንያስ

“እናንተ የምድር ትሑታን ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ፈልጉ።”

ሶፎንያስ የይሁዳ ሰዎች በክፋታቸው ምክንያት በባቢሎኖች ሙሉ በሙሉ እንደሚጠፉ ተነበየ። “ነገርን ሁሉ ከምድር ፊት ፈጽሜ አጠፋለሁ ይላል እግዚአብሔር” (ሶፎንያስ 1፥2)። እንዲሁም ሶፎንያስ “ቀሪዎች” ይጠበቃሉ ብሎ ተናገረ (ሶፎንያስ 3፥13)። እነዚህን ትንቢቶች ሲያነቡ ይሁዳን እና ሌላ ቡድኖችን ወደ ጥፋት የመሩ አመለካከቶችን እና ባህሪዎችን ያስተውሉ—በተለይ ሶፎንያስ 1፥4–6፣122፥8፣ 10፣153፥1–4ይመልከቱ። ከዚያም እግዚአብሔር የሚጠብቃቸውን ሰዎች ባህሪዎች ይመልከቱ— ሶፎንያስ 2፥1–33፥12–13፣ 18–19ይመልከቱ። ጌታ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ለእርሶ ምን መልዕክት እንዳለው ይሰማዎታል?

ሶፎንያስ 3፥14–20 ጌታ “ጠላ[ትን] [ከጣለ]” በኋላ ጻድቃን የሚኖራቸውን ደስታ ይገልፃል (ቁጥር15)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ቃል የተገቡ ምን ዓይነት በረከቶችን አስተዋሉ? ስለእነዚህ በረከቶች ማወቅ የሚሆነው ለምንድን ነው? አነዚህን ጥቅሶች በ 3ኛ ኔፊ17 ውስጥ ከተጠቀሱት ልምዶች ጋር ሊያነፃፅሩ እና ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሕዝቦቹ እንዴት እንደተሰማው ሊያሰላስሉ ይችላሉ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ናሆም 1፥7እግዚአብሔር እንዴት ነው እንደ “መሸሸጊያ” የሆነው? ምናልባት ቤተሰብዎ በቤትዎ ውስጥ ቀላል ምሽግ ሊገነቡ እና ውስጡ ሆነው ሊወያዩ ናሆም 1፥7 ይችላሉ። ቀናችንን ምንድን ነው “የመከራ ቀን” የሚያደርገው? ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ እንዴት ነው የሚያጠነክሩን? እንዴት ነው “በእርሱ [መታመንን]” የምናሳየው?

ዕንባቆም 2፥14በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያለውን ትንቢት ለማሳካት ማገዝ የምንችለው እንዴት ነው?

ዕንባቆም 3፥17–19በዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከዕንባቆም ምሳሌ ምን እንማራለን?

ሶፎንያስ 2፥3የቤተሰብ አባላት ከብዙ ሌሎች ቃላት ጋር በአንድ ገፅ ላይ “ጽድቅ” እና “ትህትና” የሚሉትን ቃላትን የሚያገኙበትን ጨዋታ መጫወት ይችላሉ። ከዚያም አንዳቸው ባንዳቸው ላይ ስላዩት የጽድቅ እና የትህትና ምሳሌዎች መናገር ይችላሉ። ጽድቅን እና ትህትናን መፈለግ ምን ማለት ነው?

ሶፎንያስ 3፥14–20ሶፎንያስ 3፥14–20 ውስጥ “[እንድን]ዘምር፣ … በፍጹም ል[ባችን] ሐሤት አድር[ገን] ደስም [እንዲለን]” የሚያደርገንን ምን እናገኛለን? ምናልባት ቤተሰብዎ እነዚህን ጥቅሶች ሲያነቡ ወደ አዕምሮ የሚመጡን መዝሙሮች ሊዘምሩ ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “Seek the Lord Early፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣108።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ትእግስተኛ ይሁኑ። አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄዎቻችን መልሶችን በፍጥነት እንፈልጋለን፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች ጊዜን ይወስዳሉ እንዲሁም በግፊት ሊሆኑ አይችሉም። ጌታ ለዕንባቆም እንደነገረው “ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገ[ሱት]” (ዕንባቆም 2፥3)።

ምስል
ኢየሱስ ቀይ ካባ ለብሶ ከሰማይ ሲወርድ

“አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው” (ሶፎንያስ 3፥17)። ሊገዛ እና ሊነግሥ ተመልሶ ይመጣል፣ በሜሪአር. ሳወር

አትም