“ታህሳስ 19፟–25 (እ.አ.አ)። ገና፦ “እርሱን ጠብቀነዋል እናም ያድነናል፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]
“ታህሳስ 19፟–25 (እ.አ.አ)። ገና፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 19–25 (እ.አ.አ)።
የገና በዓል
“እርሱን ጠብቀነዋል እናም ያድነናል”
በዚህ የገና ወቅት ብሉይ ኪዳን አመቱን ሙሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለዎትን ምስክርነት እንዴት እንዳጠነከረ ያስቡ።
ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ
ብሉይ ኪዳን በጉጉት የመጠበቅን መንፈስ ይዟል። በዛ መልኩ፣ በትንሹ ልክ እንደ የገና ወቅት ነው። ከአዳም እና ሔዋን ጀምሮ፣ የብሉይ ኪዳን ፓትርያርኮች፣ ነብያቶች፣ ገጣሚዎች እና መልካም ቀናትን ወደፊት የተመለከቱ ሰዎች በመሲሁ የሚታደስ እና የሚያድን ተስፋ ተሞልተው ነበር። እናም እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ያንን ተስፋ ይፈልጉ ነበር—በግብፅ ወይም በባቢሎን በምርኮም ሳሉ ወይም በራሳቸው ሃጢያት ወይም አመፃ ውስጥ በነበሩ ጊዜ። በዛም ሰዓት ሁሉ ነብያት መሲህ፣ አዳኝ “ለተማረኩት ነፃነትን ለማወጅ” እንደሚመጣ አስታወሷቸው (ኢሳይያስ 61፥1)።
ያ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ሲወለድ እውን መሆን ጀመረ። ታላቁ የእስራኤል አዳኝ በበረት ተወለደ እና በግርግም ውስጥ ተኛ ( ሉቃስ 2፥7ይመልከቱ)። ነገር ግን የጥንት እስራኤላውያን አዳኝ ብቻ አልነበረም። ሃዘናችሁን ለመሸከም፣ ለበደላችሁም ለመቁሰል፣ በእርሱም ቁስል ትፈወሱ ዘንድ—ሊያድናችሁ መጣ ( ኢሳይያስ 53፥4–5ይመልከቱ)። ለዚህ ነው የገና በዓል እስከዛሬ ድረስ በጉጉት ደስታ የተሞላ የሆነው። መሲሁ ከ2000 ዓመታት በላይ በፊት መጣ እናም ስንሻው በሕይወታችን ውስጥ መምጣቱን ይቀጥላል።
ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
በቤዛዬ እደሰታለው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም ደስታን ስለሚያመጣ የገና በዓል እንደ ደስታ ወቅት ይታወቃል። ኢየሱስን እንደእግዚአብሔር ልጅ የማያመልኩ ሰዎች እራሳቸው ብዙውን ጊዜ የገና በዓል ደስታ ሊሰማቸው ይችላል። የሰማይ አባት ልጁን ስለላከው የሚሰማዎትን ደስታ ያሰላስሉ።
አዳኙ ከመወለዱ ከክፍለ ዘመናት በፊት፣ የብሉይ ኪዳን ነብያት ስለሚመጣው መሲህ ሲናገሩ ደስታ ተሰማቸው። ከሚከተሉት ምንባቦች ውስጥ የተወሰኑትን ያንብቡ፣ እና የአዳኙን ተልዕኮ ለጠበቁ ሰዎች ለምን ውድ እንደሆኑ ያስቡ፦ መዝሙረ ዳዊት 35፥9፣ ኢሳይያስ 25፥8–9፤ 44፥21–24፤ 51፥11፤ ሶፎንያስ 3፥14–20፤ ሙሴ 5፥5–11። እነዚህ ምንባቦች ለእናንተ ውድ የሆኑት ለምንድን ነው?
ደግሞም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Joy and Spiritual Survival፣ ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 81–84 ይመልከቱ።
ምልክቶች ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳስታውስ ይረዱኛል።
ብዙ ከገና በዓል ጋር የሚያያዙ ወጎች ወደ ክርስቶስ የሚጠቁሙ ምልክታዊ ትርጉሞች ሊኖራቸው ይችላል። ኮከባማ የሆኑ ጌጣጌጦች ኢየሱስ የተወለደ ምሽት የበራውን ብሩህ ኮከብ ይወክላሉ ( ማቴዎስ 2፥2ይመልከቱ)። ዘማሪዎች ለእረኞች የተገለፁትን መላዕክቶች ሊያስታውሱን ይችላሉ ( ሉቃስ 2:13–14ይመልከቱ)። በዚህ ዓመት ብሉይ ኪዳንን ባጠኑበት ጊዜ፣ የአዳኙን ብዙ ምልክቶች ተገንዝበው ይሆናል። የተወሰኑት ከታች ተዘርዝረዋል። እነዚህን ማጥናትን እና ስለእርሱ የሚያስተምሮትን ለመመዝገብ ያስቡ።
-
የነሃስ እባብ (ዘኁልቁ 21፥4–9፤ ዮሐንስ 3፥14–15)።
-
ቁጥቋጥ (ኢሳይያስ 11፥1–2፤ ኤርምያስ 23፥5፤ 33፥15)።
-
ብርሃን (መዝሙረ ዳዊት 27፥1፤ ኢሳይያስ 9፥2፤ 60፥19፤ ሚክያስ 7፥8፤ ዮሐንስ 8፥12)።
በቅዱሳንፅሁፎች ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ሌሎች ምን ምልክቶች፣ ምንባቦች እና ዘገባዎች አገኙ?
2ኛ ኔፊ 11፥4፤ ሞዛያ 3፥14–15፤ ሙሴ 6፥63፤ “የክርስቶስ ዓይነቶች ወይም ምልክቶች፣” በቅዱሳን ፅሁፎች መመሪያ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።
“ሰሙም ድንቅ መካር ተብሎ ይጠራል።”
ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ ስሞች እና ማዕረጎች ተጠርቷል። በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ ምን ዓይነት ስያሜዎችን ያገኛሉ? መዝሙረ ዳዊት 23፥1፤ 83፥18፤ ኢሳይያስ 7፥14፤ 9፥6፤ 12፥2፤ 63፥16፤ አሞጽ 4፥13፤ ዘካሪያስ 14፥16፤ ሙሴ 7፥53። ሌላ ምን ስያሜዎችን ያስባሉ? በገና መዝሙሮች ውስጥ የሚገኙትን የኢየሱስ ክርስቶስን ስያሜዎች በማዳመጥ ሊደሰቱም ይችላሉ። እያንዳንዱ ስያሜ ስለእርሱ በሚያስቡበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያሳድራል?
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
የገና በዓል ወጎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊጠቁሙ ይችላሉ።የእስራኤል ቤተሰቦች ልባቸውን እና አዕምሮአቸውን ወደ ጌታ ለማድረግ የሚረዳ እንደ ፋሲካ እና ሌሎች ድግሶች ያሉ ባህሎች ነበሯቸው ( ኦሪት ዘጸአት 12ይመልከቱ)። ቤተሰቦ በገና በዓል ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለማተኮር የሚረዱ ምን ዓይነት ባህሎች አለው? ከቤተሰቦ ታሪክ ውስጥ ምን ዓይነት ባህሎችን ያውቃሉ? መጀመር የሚፈልጉትን አንዳንድ ባህሎች እንደ ቤተሰብ መወያየትን ሊያስቡ ይችላሉ። አንዳንድ ሃሳቦች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፣ የተቸገረን ሰው ማገልገል ( ComeuntoChrist.org/light-the-worldይመልከቱ)፣ ጓደኛን የቀዳሚ አመራር የገና በዓል አምልኮን አብሮት እንዲመለከት መጋበዝ (broadcasts.ChurchofJesusChrist.org)፣ የራሶን የገና በዓል መዝሙር መፃፍ ወይም የክርስቶስን ልደት መልዕክት ለማካፈል የፈጠራ መንገድን ማግኘት።
-
“The Christ Child: A Nativity Story።”የቤተሰብ አባላት የክርስቶስን ውልደት ክብር እና ደስታ እንዲሰማቸው እንዴት መርዳት ይችላሉ? “The Christ Child: A Nativity Story” የሚለውን ቪድዮ በ (ChurchofJesusChrist.org) መመልከት ይችላሉ ወይም የሚከተሉትን ጥቅሶች በጋራ ያንብቡ ማቴዎስ 1፥18–25፤ 2፥1–12፤ ሉቃስ 1፥26–38፤ 2፥1–20። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ከቪዲዮው ወይም ከቅዱስ ፅሁፍ ዘገባው ውስጥ አንድን ሰው በመምረጥ ያ ሰው ስለአዳኙ እንዴት እንደተሰማው ማካፈል ይችላል። የቤተሰብ አባላት ስለእርሱ ያላቸውን ስሜት ማካፈልም ይችላሉ።
-
አዳኙን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማግኘት።በሚቀጥለው ዓመት የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለማጥናት ሲዘጋጁ ከቤተሰቦ ጋር በዚህ ዓመት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለእርሱ ምን እንደተማሩ መከለስን ያሰቡ። የተማሩትን ለማስታወስ እንዲረዳዎ በዚህ ግብዓት ውስጥ ያሉ ዝርዝሮች እና ግላዊ ማስታወሻዎችን መከለስ ይችላሉ። ወጣት ልጆች የ ብሉይ ኪዳን ታሪኮችን በመመልከት ወይም በዚህ ግብዓት ውስጥ ያሉ ምስሎችን በማየት ሊጠቀሙ ይችላሉ። ምን ትንቢቶች ወይም ታሪኮች ጎልተው ታዩን? ስለ አዳኙ ምን ተማርን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር “ኦ የቤተልሔም ትንሽ ከተማ፣” መዝሙር፣ ቁጥር.208።