ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 5፟–11 (እ.አ.አ)። ሐጌ፤ ዘካርያስ 1–3፤ 7–14፦ “ለእግዚአብሔር የተቀደሰ”


“ታህሳስ 5፟–11 (እ.አ.አ)። ሐጌ፤ ዘካርያስ 1–3፤ 7–14፦ ‘ለእግዚአብሔር የተቀደሰ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ታህሳስ 5፟–11 (እ.አ.አ)። ሐጌ፤ ዘካርያስ 1–3፤ 7–14፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ላኢዬ ሐዋዪ ቤተመቅደስ

ላኢዬ ሐዋዪ ቤተመቅደስ

ታህሳስ 5፟–11 (እ.አ.አ)

ሐጌዘካርያስ 1–37–14

“ለእግዚአብሔር የተቀደሰ”

ቅዱሳን መጻህፍትን ማንበብ መገለጥን ይጋብዛል። ትንቢተ ሐጌን እና ትንቢተ ዘካርያስን ሲያነቡ መንፈስ ቅዱስ ለሚገልፅልዎት መልዕክቶች ክፍት ይሁኑ።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

ከአስርተ ዓመታት ምርኮ በኋላ ነብያት ሔጌን እና ዘካርያስን ጨምሮ የእስራኤላውያን አንድ ቡድን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ተፈቅዶላቸው ነበር። በዚህ ቡድን ውስጥ የተወሰኑት ኢየሩሳሌም ከመውደሟ በፊት ምን ትመስል እንደነበር አስታወሱ። ከዚህ በፊት ቤታቸው፣ የማምለኪያ ቦታቸው እና ቤተመቅደሳቸው የነበረውን ፍርስራሽ ሲመለከቱ ምን አይነት ሰሜት ሊሰማቸው እንደሚችል ይገምቱ። ቤተመቅደሱ እንደገና የጌታን “የቀድሞ ክብር” (ሐጌ 2፥3)፣ ይመስል ይሆን ብለው ለሚገረሙ ሰዎች፣ ነብዩ ሐጌ የጌታን የማበረታቻ ቃላት እንዲህ ተናገረ፦ “እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ በርቱና ስሩ ይላል እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝኛ፣ … አትፍሩ።” “ይህንንም ቤት በክብር አሞላዋለው፣ … በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ።” (ሐጌ 2፥4–5፣ 7፣9።)

ነገር ግን ቤተመቅደሱ ብቻ አልነበረም መልሶ መገንባትን ያስፈለገው። በብዙ መንገድ የእግዚአብሔር ህዝቦች በመንፈስ ፈራርሰው ነበር። እናም ቅዱስ ህዝብን መልሶ መገንባት የቤተመቅደስን ግድግዳ ለመገንት ድንጋይን ከመጥረብ እና ከማስተካከል የበለጠ ነገርን ይወስዳል። ዛሬ ቤተመቅደሶች “ለእግዚአብሔር የተቀደሰ” የሚለውን ጽሁፍ ይዘዋል እናም አነዛ ቃላት ለህንፃ ብቻ ሳይሆን ለሕይወት አኗኗርም ተግባራዊ ይሆናሉ። እነዚህን ቃላት በ“ፈረሶች ሻኩራ ላይ” እና “በኢየሩሳሌም ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ” መቅረፅ (ዘካርያ 14፥20–21) ጠቃሚ የሚሆኑት በእያንዳንዱ ልብ ላይ ከተቀረፁ ብቻ ነው። ትክክለኛ ቅድስና የጌታን ቃላት እና ህግጋት በውስጣችን ላይ “ውጤት” እንዲኖረው፣ (ዘካርያ 1፥6) ልክ እንደ እርሱ ቅዱስ መሆን እንድንችል ኃይሉን ተፈጥሮአችንን እንዲቀይር መፍቀድን ይጠይቃል ( ዘሌዋውያን 19፥2ይመልከቱ)።

ስለሐጌ እና ዘካርያስ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሐጌ” እና “ዘካርያስ” የሚሉትን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሐጌ12፥1–9

“መንገዶትን ያስቡ።”

ኢየሩሳሌምን መልሶ ለመገንባት ብዙ የሚሰሩ ጠቃሚ ነገሮች ነበሩ። ነገር ግን እስራኤላውያን ከተመለሱ በግምት 15 ዓመታት ካለፉ በኋላ የቤተመቅደስ መልሶ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ስላልተሰጠው ጌታ አዝኖባቸው ነበር ( ሐጌ 1፥2–5ዕዝራ 4፥24ይመልከቱ)። ሐጌ12፥1–9ን ሲያነቡ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን ያስቡ፦ እስራኤላውያን ቤተመቅደሱን ስላልጨረሱ ምን ዓይነት ወጤት ገጠማቸው? ጌታ የእርሱን ቤት ገንብተው ከጨረሱ ምን ዓይነት በረከቶችን ቃል ገባላቸው? የሚያስቀድሙትን ነገር ለማሰብ እና ከጌታ ጋር የተስማማ ለማድረግ እንዲችሉ—“መንገዶትን ግምት ውስጥ ለማስገባት” ይህን እድል መውሰድ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች95፤ ትሬንስኤም. ቪንሰን፣ “True Disciples of the Savior፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር. 2019 (እ.አ.አ)፣ 9–11 ይመልከቱ።

ዘካርያ 1–37–814

ጌታ ቅዱስ ሊያደርገኝ ይችላል።

እህት ካሮልኤፍ. መክኮንኪ እንዲህ አስተማረች፣ “ቅድስና መንፈስ ቅዱስን እንደመሪያችን አድርጎ የሚያቆይን ምርጫዎች ማድረግ ነው። ቅድስና ማለት የተፈጥሮ ዝንባሌአችንን ወደ ጎን መተው እና ‘በጌታ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ቅዱስ’ መሆን ማለት ነው [ሞዛያ 3፥19]። … ለቅድስና ያለን ተስፋ በክርስቶስ፣ በምህረቱ እና በፀጋው ላይ ያተኮረ ነው” (“The Beauty of Holiness፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 9–10)። እስራኤል ቅዱስ እንድትሆን የተለመነችውን በነብዩ ዘካርያስ የተሰጡትን የጌታን ቃላት በሚያነቡ ሰዓት እነዚህን ትምህርቶች ያስታውሱ፦ ዘካርያ 1፥1–63፥1–77፥8–108፥16–17። ጌታ እስራኤልን ቅዱስ ለማድረግ እንዲያደርጉ የጠየቃቸውን ነገሮች ያስተውሉ። የበለጠ ቅዱስ እንዲሆኑ እርሱ እንዴት እየረዳዎት ነው?

ዘካርያ 2፥10–118፥1–814፥9–11፣ 20–21 ወደፊት ሁላችንም በቅድስና ከጌታ ጋር ስንኖር ሕይወት ምን እንደሚመስል ይገልፃሉ። በዘካርያስ ጊዜ ኢየሩሳሌምን ለሚገነቡት ህዝቦች እነዚህ ገለፃዎች ምን ዓይነት ትርጉም ይኖራቸዋል? ለእርሶ ምን ትርጉም አላቸው?

ምስል
የኢየሱስ የድል አገባብ ወደ ኢየሩሳሌም

“እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሁትም ሆኖ በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል” (ዘካርያ 9፥9)። የድል አገባብ፣ በሃሪ አንደርሰን

ዘካርያ 9፥9–1111፥12–1312፥1013፥6–714፥1–9

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የተገባው መሲህ ነው።

ብዙ የዘካርያስ ጽሁፎች የኢየሱስ ክርስቶስን ምድራዊ አገልግሎት እና የመጨረሻ ዳግም ምፅዓትን ይጠቁማሉ። የሚከተሉትን ከዘካርያስ የወጡ ትንቦቶች ከሌላ መጽሐፎች ተዛማጅ ምንባቦች ጋር ያነፃፅሩ።

እነዚህን ምንባቦች ሲያጠኑ ስለ አዳኙ ምን ተማሩ? እነዚህን ምንባቦች መረዳት ለእርሶ ለምን ይጠቅማል?

በቅዱሳን መጽሐፍት መመሪያ ውስጥ “መሲህ፣” (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሐጌ 1፥2-7አነዚህ ጥቅሶች ቤተሰብዎ “መንገ[ዳቸውን] [እንዲያስቡ]”ለገፋፉ ይችላሉ። ምናልባት የቤተሰብ አባላት በ ቁጥር6ውስጥ ያሉትን ሃረጎች ሊተውኑ ይችላሉ። ይህ ጥቅስ የዓለምን ነገሮች ከእግዚአብሔር ነገሮች አስበልጦ ስለማየት ምን ያስተምራል? ቤተሰብዎ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ነገሮች እርስ በእርስ ልትመካከሩ ትችላላችሁ። እንደመዝሙር “I’m Trying to Be like Jesus” (የህጻናት መዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79) መዘመር ቤተሰብዎ በተሻለ እየተገበሩ ያሉትን ነገሮች እና ማሻሻል የሚችሉበትን አካባቢዎች እንዲገመግሙ ሊረዳ ይችላል።

ሐጌ 2፥1–9እነዚህን ቁጥሮች ለማስተዋወቅ፣ ከተቃጠለ በኋላ ከውድ ሥነ ሕንፃ መልሶ የተገነባውን የፕሮቮ ከተማ ማእከል ቤተመቅደስን ታሪክ ሊያካፍሉ ይችላሉ (የ “Provo City Center Temple Completed፣” ቪዲዮ ይመልከቱ ChurchofJesusChrist.org)። ሐጌ 2፥1–9ን ሲያነቡ የቤተሰብ አባላት በሕይወታችን ውስጥ ልክ የፈረሰን ቤተመቅደስ መልሶ እንደመገንባት ስለሚመስል ነገር እንዲያስቡ ሊጠይቁ ይችላሉ። ከሃዘን ወይም ከመከራ በኋላ ጌታ እንዴት ነው መልሶ የሚገነባን?

ዘካርያስ 3፥1–7እነዚህን ጥቅሶች ሲያነቡ ለቤተሰብዎ ቆሻሻ ልብሶችን ሊያሳዩ ይችላሉ። ኢያሱ በቆሻሻ ልብስ ከመልአኩ ፊት ሲቆም እንዴት ተሰምቶት ሊሆን ይችላል? ሃጢያት እንዴት ነው እንደ ቆሻሻ ልብስ የሚወሰደው? ዘካርያስ 3፥1–7 ስለይቅርታ ምን ያስተምረናል? ከዚያም ልብሶቹን አብራችሁ በማጠብ ስለ አዳኙ የሃጢያት ክፍያ የማንፃት ኃይል ማውራት ይችላሉ።

ዘካርያስ 8፥1–8ስለዘካርያስ የኢየሩሳሌም የወደፊት ራዕይ ምን ያስደንቀናል? እዚያ በማሕበረሰባችን ውስጥ ማየት የምንፈልገውን ነገር ምን እናገኛለን? አዳኙ “በመካከ[ላችን] እንዲኖር” ለመጋበዝ እንዴት እንችላለን? (ጌሪኢ. ስቲቭንሰን፣ “Sacred Homes, Sacred Temples፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 101–3 ይመልከቱ)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “I’m Trying to Be like Jesus፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የግል ግምገማ እድሎችን ይጠቀሙ። ቅዱሳን መጽሐፍትን ሲያጠኑ ብዙውን ጊዜ ለእግዚአብሔር አባት እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ስላሎት ቆራጥነት ለማሰላሰል ይነሳሳሉ። በሚቀበሉት ስሜቶች ላይ ተግባራዊ እርምጃ ይውሰዱ።

ምስል
የፕሮቮ ቤተአምልኮ በፕሮቮ፣ ዩታ፣ ዩኤስኤ ውስጥ እንዴት በእሳት እንደወደመ እና እንዴት እንደ ፕሮቮ ከተማ ማእከል ቤተመቅደስ መልሶ እንደተገነባ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የሚያሳይ የጊዜ ሰሌዳ።

አትም