ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 12፟–18 (እ.አ.አ)። ሚልክያ፦ “ወድጃችኋለው ይላል ጌታ”


“ታህሳስ 12፟–18 (እ.አ.አ)። ሚልክያ፦ ‘ወድጃችኋለው ይላል ጌታ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ታህሳስ 12፟–18 (እ.አ.አ)። ሚልክያ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ክርስተስ ሃውልት

ታህሳስ 12፟–18 (እ.አ.አ)።

ሚልክያ

“ወድጃችኋለው ይላል ጌታ”

ሚልክያ የሚለው ስያሜ “የኔ መልዕክተኛ” ማለት ነው (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “ሚልክያ”)። የሚልክያ ለእስራኤል ያለውን መልዕክት ሲያጠኑ ለሕይወቶ ምን ዓይነት መልዕክትን ያገኛሉ? የሚልክያ ቃላት እንዴት ነው ከዘመናችን ጋር የሚዛመዱት?

ያሳደረቦትን ስሜት ይመዝግቡ

“ወድጃችኋለው፣” በነብዩ ሚልክያ አማካኝነት ጌታ ለህዝቦቹ ተናገረ። ነገር ግን ለትውልዶች በመከራ እና ምርኮኝነት የተሰቃዩ እስራኤላውያን ጌታን እንዲህ ጠየቁት፣ “በምን ወደድኸን?” (ሚልክያ 1፥2)። እስራኤላውያን ካሳለፉት መከራ በኋላ የጥንት እስራኤል ታሪክ በእርግጥ ለቃልኪዳን ህዝቦች ያለው የእግዚአብሔር የፍቅር ታሪክ እንደሆነ ተገርመው ሊሆን ይችላል።

በዚህ ዓመት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ምን እንዳነበቡ ሲያንፀባርቁ ስለእግዚአብሔር ፍቅር ምን ማረጋገጫ ያገኛሉ? ብዙ የሰው ድካም እና አመጽ ምሳሌዎችን ማየት ቀላል ነው። ነገር ግን በዛ ሁሉ ውስጥ እግዚአብሔር በፍቅር መድረሱን አላቆመም ነበር። የያዕቆብ ወንድ ልጆች ወንደማቸውን ጆሴፍን ቢበድሉም እንኳን፣ ጌታ ከረሃብ ሊያድናቸው መንገድን አዘጋጀ ( ኦሪት ዘፍጥረት 45፥4–8ይመልከቱ)። እስራኤሎች በበረሃ ሲያጉረመርሙ፣ እግዚአብሔር በመና መገባቸው ( ኦሪት ዘጸአት 16፥1–4ይመልከቱ)። እስራኤላውያን ቢተዉትም፣ ወደ ሌላ አማልክት ፊታቸውን ቢያዞሩም፣ እና ቢበታተኑም እንኳን፣ እግዚአብሔር በፍፁም ሙሉ በሙሉ አልተዋቸውም ነበር፤ ነገር ግን ንስሃ ከገቡ እንደሚሰበስባቸው እና “በታላቅ ምህረት” እንደሚያድናቸው ቃል ገባላቸው ( ኢሳይያስ 54፥7ይመልከቱ)።

በዚህ መልኩ ሲታይ፣ ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ትዕግስት፣ የሚጸና ፍቅር ታሪክ ነው። እናም ይህ ታሪክ ዛሬም ይቀጥላል። “የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣” ብሎ ሚልክያ ተነበየ (ሚልክያ 4፥2ይመልከቱ)። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ለሚመጡ ሁሉ አካላዊ እና መንፈሳዊ ፈውስን ይዞ መጥቷል። እርሱ ለጥንት እስራኤልና ለሁላችን ስላለው የእግዚአብሔር ፍቅር ታላቁ ማረጋገጫ ነው።

ስለሚልክያ መጽሐፍ የበለጠ መረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሚልክያ” የሚለውን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሚልክያ 1–4

“ወደ እኔ ተመለሱና እኔ ወደ እናንተ እመለሳለሁ።”

በሚልክያ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ቤተመቅደስን በኢየሩሳሌም እንደገና ገንብተው ነበር፤ ነገር ግን እንደ ህዝብ ከጌታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደገና መገንባት ይኖርባቸው ነበር። ሚልክያን ሲያጠኑ፣ ጌታ እስራኤላውያንን የጠየቀውን ወይም እነርሱ የጠየቁትን ጥያቄዎች ፈልጉ። ከጌታ ጋር ያሎትን ግንኙነት ለመገምገም እና ወደ እርሱ ለመቅረብ እንዲረዳ እራሶን ተመሳሳይ ጥያቄዎችን መጠየቅን ያስቡ (የተወሰኑ ምሳሌዎች ከታች ተጠቅሰዋል)።

  • ጌታ ለእኔ ያለውን ፍቅር እንዴት ተሰምቶኛል? ( ሚልክያ 1፥2ይመልከቱ)።

  • እኔ ለጌታ የማቀርበው መባ በእርግጥ እርሱን ያከብረዋልን? ( ሚልክያ 1፥6–11ይመልከቱ)።

  • በምን ዓይነት መንገዶች ነው ወደ ጌታ “መመለስ” የሚገባኝ? ( ሚልክያ 3፥7ይመልከቱ)።

  • እግዚአብሔርን በሆነ ዓይነት መንገድ እየሰረኩት ነኝን? ( ሚልክያ 3፥8–11ይመልከቱ)።

  • በአስቸጋሪ ጊዜያት ያለኝ አመለካከቴ ለጌታ ያለኝን ስሜት የሚያንፀባርቀው እንዴት ነው? ( ሚልክያ 3፥13–152፥17ይመልከቱ)።

በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻለሁ እና እቀጣለሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 97–100 ይመልከቱ።

ሚልክያ 1፥6–14

ጌታ “ንፁህ መስዋትነትን” ይጠይቃል።

የጌታ ቃላት በ ሚልክያ1 የእስራኤል ካህናት ጌታ የከለከለውን አንካሳ እና የታመሙ እንስሳትን በቤተመቅደስ ውስጥ ለመስዋትነት ያቀርቡ እንደነበር ይጠቁማል ( ዘሌዋውያን 22፥17–25ይመልከቱ)። እነዚህ መስዋእቶች ካህናቶቹ ለጌታ ስላላቸው ስሜት ምን ይጠቁማሉ? ( ሚልክያ 1፥13ይመልከቱ)። ጌታ ለምንድን ነው የተሻለ መስዋእታችንን እንድንሰጠው የሚጠይቀን? ጌታ እንዲከፍሉ የጠየቆትን መስዋእቶች ያስቡ። “ንፁህ መስዋእትን” ለእርሱ ለመስጠት ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? (ሚልክያ 1፥11፤ ደግሞም 3፥3ይመልከቱ)።

ሞሮኒ 7፥5–14ይመልከቱ።

ሚልክያ 3–4

የሚልክያ ትንቢቶች በኋለኛው ቀናት ውስጥ እየተፈፀሙ ናቸው።

አዳኙ አሜሪካን ሲጎበኝ፣ ሚልክያ 3–4 ን ለኔፋውኖች ጠቀሰላቸው ( 3ኛ ኔፊ 24–25ይመልከቱ)። በ1823 (እ.አ.አ) መልአኩ ሞሮኒ የእነዚህኑ ምዕራፎች የተወሰኑ ክፍሎች ለጆሴፍ ስሚዝ አካፈለ ( የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥36–39ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች2ይመልከቱ)። የሚልክያ ቃላት በቅዱሳን ጽሁፎች ውስጥ አብዝተው የተደገሙት ለምን ይመስሎታል? ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥9110፥13–16128፥17–18ይመልከቱ)። በእርስዎ አስተሳሰብ ከ ሚልክያ 3–4 የትኞቹ መልዕክቶች በተለይ ለቀናችን አስፈላጊ ይመስላሉ?

ሞሮኒ ሚልክያ 4፥5–6 ን ለጆሴፍ ስሚዝ ሲጠቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ከሚነበበው በትንሹ ልዩነት” ነበረው (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥36)። የሞሮኒ የተለየ ዘገባ የዚህን ትንቢት መረዳት ላይ ምን ይጨምራል? ስለኤልያስ መምጣት እና ይሄ ትንቢት ዛሬ እንዴት እየተከናወነ እንደሆነ የበለጠ ለመማር፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥13–16 ን እና የሽማግሌ ዴቪድኤ. ቤድናር፣ “The Hearts of the Children Shall Turn” መልዕክትን (ሊያሆና፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ) 24–27 ይመልከቱ)። ኤልያስ ስለመጣ አመስጋኝ የሆኑት ለምንድን ነው?

ኤልያስ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገለጽ

ኤልያስ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገለጽ የሚያሳይ በሮበርትቲ. ባሬት

ሚልክያ 3፥8–12

አስራትን መክፈል የሰማይን መስኮቶች ይከፍታል።

ሚልክያ 3፥8–12ን ሲያነቡ አስራትን በመክፈል ረገድ ያለዎትን የገዛ ልምዶትን ያስቡ። “የሰማይን መስኮት ይከፍታል” (ቁጥር10) የሚለው ሃረግ ለእርሶ ምን ማለት ነው?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሚልክያ 1፥2ቤተሰቦ በ ሚልክያ 1፥2ውስጥ የሚገኘውን—“በምን [ጌታ] ወደደን?” የሚለውን ጥያቄ እንዴት መልስ ሊሰጡ ይችላሉ? ጌታ ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያሳዩ የተወሰኑ ማስረጃዎች ምንድን ናቸው?

ሚልክያ 3፥8–12 ሚልክያ 3፥8–12ን ሲያነቡ የቤተሰብ አባላት ስለአስራት ያላቸውን ሃሳብ ወይም ስሜት እንዲያካፍሉ ይጋብዙ። አስራትን በመክፈል ምን ዓይነት አለማዊ እና መንፈሳዊ በረከቶችን አይተናል? (የዴቪድኤ. ቤድናርን፣ “Joy and Spiritual Survival፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 17–20 ይመልከቱ)። የቤተሰብ አባላት በረከቶችን ለመወከል ምስሎችን በመሳል እና ምስሎቹን በመስኮት ላይ በመስቀል ሊደሰቱ ይችላሉ።

ሚልክያ 3፥13–18የጌታ መሆን እና ከእርሱ “ጌጣጌጦች” መካከል አንዱ መሆን ለኛ ምን ማለት ነው?

ሚልክያ 4፥5–6እነዚህን ጥቅሶች ካነበቡ በኋላ ቤተሰቦ ስለሚልክያ ትንቢት አስመልክቶ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ምላሾችን ሊለዩ ይችላሉ፦ ማን? ምን? መች? የት? ለምን? (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች2ይመልከቱ)።

ልቦቻችንን እንዴት ነው ወደ አባቶቻችን የምንመልሰው? ይህን ስናደርግ እንዴት ነው የምንባረከው? “The Promised Blessings of Family History” የሚለውን ቪዲዮ ሲመለከቱ እነዚህን ጥያቄዎች ሊያሰላስሉ ይችላሉ (ChurchofJesusChrist.org)። እነዚህን በረከቶች ለመቀበል እንደቤተሰብ ምን እናደርጋለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “የቤተሰብ ታሪክ—እየተገበርኩት ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ94።

የግል ጥናትን ማሻሻል

በሚያጠኑበት ጊዜ ጥያቄዎችን ጠይቁ። ቅዱሳን መጻህፍትን ሲያጠኑ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዎ ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄዎች ያሰላስሉ እና መልሶቹን ይፈልጉ።

አንዲት ሴት ብዙ ቅድመ አያቶቿ ከኋላዋ ሆነው ነጭ መሃረብን ስታውለበልብ።

የሞርኒንግ ሆሳዕና፣ በሮዝ ዳቶክ ዳል። ሞርኒንግ የምትባል አንዲት ሴት በመንፈስ ዓለም ውስጥ ቆማ በቅድመ አያቶቿ ተከባ። ከመንፈስ ምርኮነት መዳናቸውን ስታከብር።