ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ግንቦት 23–29 (እ.አ.አ)። ኢያሱ 1–8፤ 23–24፥ “ጽኑ፥ አይዞአችሁ”


“ግንቦት 23–29 (እ.አ.አ)። ኢያሱ 1–8፤ 23–24፡ ‘ጽኑ፥ አይዞአችሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 23–29 (እ.አ.አ)። ኢያሱ 1–8፤ 23–24፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ሙሴ ኢያሱን ሲሾም

ሙሴ ኢያሱን ሲሾም የሚያሳይ ስዕል፣ በዳረል ቶማስ

ግንቦት 23–29 (እ.አ.አ)

ኢያሱ 1–823–24

“ጽኑ፥ አይዞአችሁ”

መፅሐፈ ኢያሱን መስታነቡ፣ ስለ እስራኤላዊያን የምትማሩት ነገሮች እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት እንደሚጨምሩት አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በርካታ ትውልዶችን ወስዷል፣ ግን የጌታ የተስፋ ቃል ሊፈፀም ተቃርቧል፦ የእስራኤል ልጆች የተስፋውን ምድር ለመውረስ ጫፍ ላይ ነበሩ። ነገር ግን የዮርዳኖስ ወንዝ፣ የኢያሪኮ ቅጥር እና ጌታን የካዱ ክፉ ነገር ግን ሃያላን ሰዎች በመንገዳቸው እንቅፋት ነበሩ (1 ኔፊ 17፥35ን ይመልከቱ)። በዚያ ላይ የሚወዱት መሪያቸው ሙሴ አልነበረም። ሁኔታው አንዳንድ እስራኤላዊያንን ደካማነት እና ፍራቻ እንዲሰማቸው አድርጎ ይሆናል፣ ነገር ግን ጌታ “ጽኑ፥ አይዞአችሁ” አለ። ለምን እንደዚህ ሊሰማቸው ይገባል? በራሳቸው—ወይም በሙሴ ወይም በኢያሱ—ጥንካሬ አደለም፣ ነገር ግን “በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና” (ኢያሱ 1፥9)። እኛ የምናቋርጠው የራሳችን ወንዝ እና የምንጥለው ግድግዳ ሲኖረን በሕይወታችን ውስጥ አስደናቂ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፣ ምክንያቱም “እግዚአብሔር በመካከ[ላችን] ድንቅ ነገር ያደርጋልና” (ኢያሱ 3፥5)።

ስለመፅሐፈ ኢያሱ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መፅሐፈ ኢያሱ” የሚለውን ይመልከቱ።

Learn More image
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኢያሱ 1፥1–9

ለእርሱ ታማኝ ከሆንኩ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ይሆናል።

ሙሴን እንዲተካ መጠራቱ ለኢያሱ ምን ይመስል እንደነበር አስቡት። ጌታ በኢያሱ 1፥1–9 ውስጥ እርሱን ሊያበረታታው ምን እንዳለ አስተውሉ። ስለሚገጥሟችሁ አስቸጋሪ ፈተናዎች አስቡ፤ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹ ብርታትን ይሰጧችኋል?

ኢያሱ (በዕብራይስጥ ዬሁሻ ወይም ዬሹዋ) የሚለው ስም “ያህዌህ ያድናል” ማለት መሆኑ ትኩረት የሚስብ ሊሆን ይችላል። እናም በዕብራይስጥ ኢየሱስ የሚለው ስም የመጣው ከዬሹዋ ነው። ስለዚህ ስለ ኢያሱ በምታነብበት ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ወደ ተስፋው ምድር የመምራት ተልእኮው የአዳኙን ተልእኮ እንዴት እንድታስታውሱ እንድሚያደርጓችሁ አስቡበት።

በተጨማሪም አን ኤም. ዲብ፣ “ብርታት ይኑራችሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2010 (እ.አ.አ)፣ 114–16 ይመልከቱ።

ኢያሱ 2

እምነት እና ስራ ሁለቱም ለደህንነት አስፈላጊ ናቸው።

የጥንት ክርስቲያኖች ረዓብን የእምነትም ሆነ የሥራ ኃይል ምሳሌ አድርገው ይመለከቱት ነበር ( ዕብራዊያን 11፥31ያዕቆብ 2፥25ን ይመልከቱ)። እናንተ ኢያሱ 2ን ስታነቡ፣ እራሷን፣ ቤተሰቧን እና የእስራኤልን ሰላዮች በማዳን ላይ የረዓብ እምነት ምን ሚና እንዳለው አስቡ። በክርስቶስ ላይ ያላችሁ እምነት እና ስራዎቻችሁ በእናንተ እና በሌሎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ይህ ምን ያስተምራችኋል?

ረዓብ የንጉሥ ዳዊትና የኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ አያት እንደነበረች ማወቅ ያስደንቃችሁ ይሆናል (ማቴዎስ 1፥5ን ይመልከቱ)። ከዚህ ምን አይነት ትምህርቶችን ልንማር እንችላለን?

ረዓብ

ረዓብ በመስኮትዋ። ቃል ኪዳኑን በመጠበቅ፣ በኤልስፒት ያንግ።

ኢያሱ 3–4

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ካለኝ የእግዚአብሔርን “ድንቆች” ተሞክሮ ይኖረኛል።

ጌታ የሚፈልገው “ይኸውም የእግዚአብሔር እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ” ነው (ኢያሱ 4፥24)። እናንተ ኢያሱ 3–4ን ስታነቡ፣ እራሳችሁን በእስራኤላውያን ቦታ ለማድረግ ሞክሩ። ጌታ በህይወታችሁ “ድንቅን” ያደረገው እንዴት ነው? (ኢያሱ 3፥5)። እነዚያን ድንቅ ነገሮች በብዛት እንዴት ልትለማመዱ ወይም ልትገነዘቡ ትችላላችሁ? (ለምሳሌ ኢያሱ 3፥17ን ን ይመልከቱ)።

እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ከመሻገራቸው በፊት ራሳቸውን መቀደስ ለምን አስፈለጋቸው? “የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ” ብቻ ወንዙ በመከፈሉ ምን ታላቅ ትርጉም ታገኛላችሁ? (ኢያሱ 3፥13፣ 15)።

በዮርዳኖስ ወንዝ ለተከሰቱ ሌሎች ጉልህ ክስተቶች 2 ነገሥት 2፥6–155፥1–14፤ እና ማርቆስ 1፥9–11ን ይመልከቱ። እነዚህ ጥቅሶችን ስታሰላስሉ በእነዚህ ክስተቶች መካከል ምን ግንኙነቶችን ታያላችሁ?

በተጨማሪም ጀራልድ ኮሴ፣ “አሁን ይህም ለእናንተ ድንቅ ነውን?ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 98–100፤ “Exercise Faith in Christ” (ቪድዮ), ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ኢያሱ 6–8

መታዘዝ የእግዚአብሔርን ኃይል በሕይወቴ ውስጥ ያመጣል።

እነዚህ ምዕራፎች በኢያሪኮ እና በአይ መሬቶች ላይ ስለሚደረጉ ውጊያዎች ይናገራሉ። እንዚህን ስታነቡ፣ በራሳችሁ ህይወት እንዴት ፈተናን እንደምትዋጉ አስቡ (ለምሳሌ፣ ኢያሱ 7፥10–13ን ይመልከቱ)። እግዚአብሔር እንዴት ሊረዳችሁ እንደሚችል እና የእርሱን ኃይል ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ምን ትማራላችሁ? ለምሳሌ፣ ኢያሪኮን ለመውሰድ ጌታ በሰጠው መመሪያ የትኛው ያስደንቃችኋል? (ኢያሱ 6፥1–5ን ይመልከቱ)። ምናልባት በኢያሱ 7 ውስጥ ያለው መዝገብ በሕይወታችሁ ውስጥ ማስወገድ ያለባችሁን “የተረገመ ነገር” እንዳለ ለማወቅ ያነሳሳ ይሆናል (ኢያሱ 7፥13)።

ኢያሱ 23–24

“ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተጠጉ”

የቃል ኪዳኑን ምድር ለአስራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች ከከፈል በኋላ (ኢያሱ 13–21ን ይመልከቱ)፣ ኢያሱ የመጨረሻ ትምህርቱን ሰጣቸው። እነዚህን ትምህርቶች በኢያሱ 23–24 ውስጥ በምታነቡበት ጊዜ፣ የማስጠንቀቂያዎችን፣ የምክር እና የተስፋ በረከቶችን ዝርዝር መያዝ ትችላላችሁ። እስራኤላውያን ያለፉበትን ሁሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢያሱ በሕይወቱ መጨረሻ እነዚህን ነገሮች ለእነሱ ለመንገር የመረጠው ለምን ይመስላችኋል? “ወደ አምላካችሁ ተጠጉ” የሚለውን ለመተግበር ምን ያነሳሳችኋል? (ኢያሱ 23፥8)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኢያሱ 1፥8በግልም ሆነ በቤተሰባችን የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናታችንን እንዴት ማድረግ እንደምንችል ይህ ጥቅሰት ምን ይጠቁማል? ቅዱሳት መጻህፍት እንዴት “[መንገዳችንን እንዲቀና]” ያደረጉልን እና “[መከናወን]” ያመጡልን እንዴት ነው?

ኢያሱ 4፥3፣ 6–9ጌታ እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ ወንዝ በድንጋይ እንዲሠሩ የፈለገውን ካነበባችሁ በኋላ፣ ቤተሰባችሁ እግዚአብሔር ስላደረገላችሁ አንዳንድ ታላላቅ ነገሮች ለመወያየት ትችላላችሁ። ከዚያም ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ ድንጋይ ልትሰጧቸው እና ጌታ ያደረገላቸውን አንድ ነገር እንዲጽፉ ወይም እዚያ ላይ እንዲስሉ መጋበዝ ትችላላችሁ።

ኢያሱ 6፥2–5ኢያሪኮን ድል ለመንሳት ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጠውን መመሪያ በመተወን ቤተሰባችሁ ሊደሰቱ ይችላሉ። ከዚህ ታሪክ እንድንማር ጌታ ምን ይፈልግ ይሆናል?

ኢያሱ 24፥15ይህንን ጥቅስ ካነበቡ በኋላ፣ የቤተሰብ አባላት ምንም እንኳን ከባድ ቢሆንም ጌታን ለማገልገል የመረጥባቸውን ልምዶች ማካፈል ይችላሉ። አንድ ሁኔታ እስኪከሰት ድረስ ከመጠበቅ ይልቅ እርሱን ለማገልገል “ዛሬ” ምርጫውን ማድረግ ለምን አስፈላጊ ነው? “ጌታን ለማገልገል” ስንጥር የ“ቤታችንን” አባላት እንዴት መደገፍ እንችላለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “ትክክለኛውን ምረጥ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 239።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ምስክርነታችሁን በብዛት አካፍሉ። የእናንተ ስለእውነት ያላችሁ ንጹህ ምስክርነት በቤተሰባችሁ ላይ ሃይለኛ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል። ርቱዕ አነጋገር ወይም ረዥም መሆን የለበትም። ምስክርነት ቀጥታ እና ከልብ ሲሆን ነው በጣም ሃይል ያለው። (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 11ን ይመልከቱ።)

የኢያሪኮ ግምቦች ሲፈርሱ

ጌታ የኢያሪኮ ግምቦች እንዲፈርሱ አደረገ። © Providence Collection/ፈቃዱ የተገኘው ከgoodsalt.com