ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ግንቦት 16–22 (እ.አ.አ)። ዘዳግም 6–8፤ 15፤ 18፤ 29–30፤ 34፦ “እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ”


“ግንቦት 16–22 (እ.አ.አ)። ዘዳግም 6–8፤ 15፤ 18፤ 29–30፤ 34፦ ‘እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 16–22 (እ.አ.አ)። ዘዳግም 6–8፤ 15፤ 18፤ 29–30፤ 34፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ሙሴ በተራራ ላይ ቆሞ

ሙሴ በናባው ተራራ ላይ የሚያሳያ ስዕል፣ © Providence Collection/licensed from goodsalt.com

ግንቦት 16–22 (እ.አ.አ)

ዝዳግም 6–8151829–3034

“እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ”

የጌታን ቃላት ለልጆቻቸው እንዲያስተምሩ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች አዘዘ (ዘዳግም 6፥7 ይመልከቱ)። በዚህ ሳምንት ዘዳግምን ስታጠኑ፣ ከቤተሰባችሁ አባላት ጋር የተማራችሁትን ለማካፈል መንገዶችን ፈልጉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የሙሴ ምድራዊ አገልግሎት የተ ጀመረው በተራራ ላይ እግዚአብሔር በእሳት ነበልባል በተናገርው ጊዜ ነበር ፣ (ዘጸአት 3፥1–10ን ይመልከቱ)። የተጠናቀቀውም በተራራ ላይ ነበር፤ ከ40 አመታት በኋላ፣ እግዚአብሔር ለሙሴ በናባው ተራራ አናት ላይ የቃል ኪዳኗን ምድር ቀንጭቦ ባሳየው ጊዜ ( ዘዳግም 34፥1–4)። የእስራኤል ልጆች ወደዚያ የቃል ኪዳን ምድር እንዲገቡ በማዘጋጀት ሙሴ የህይወቱን ጊዜ አሳልፏል፣ እና ኦሪት ዘዳግም የመጨረሻ መመሪያዎቹን፣ ማስታወሻዎቹን፣ ማሳሰቢያዎቹን፣ እና ለእስራኤላዊያን ተማጽኖዎቹን መዝግቧል። የእርሱን ቃላት ማንበብ የሙሴ አገልግሎት ትክክለኛ አላማ—ህዝቡ ያስፈልጋቸው የነበርውን ዝግጅት—በምድረበዳ ስለመትረፍ፣ አገሮችን ድል ማድረግ፣ ወይም ማህበረሰብ መገንባት አልነበረም። እግዚአብሔርን ስለመውደድ፣ ለእርሱ ስለመታዘዝ፣ እና ለእርሱ ታማኝ ሆኖ ለመቆየት ስለመማር ነበር። ወደ ዘለአለማዊ ህይወት የቃል ኪዳን ምድር ለመግባት ሁላችንም የሚያስፈልገን ዝግጅት ያው ነው። ስለዚህ ምንም እንኳን ሙሴ በፍጹም እግሩ “ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር” (ዘጸአት 3፥8) ውስጥ ባረግጡም፣ በእምነቱ እና ታማኝነቱ ምክንያት፣ እግዚአብሔር ለሚከተሉት ሁሉ ወዳዘጋጀው የቃል ኪዳን ምድር ገባ።

ስለ ኦሪት ዘዳግም አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘዳግም” የሚለውን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዘዳግም 6፥4–78፥2–5፣ 11–1729፥18–2030፥6–10፣ 15–20

ጌታ በሙሉ ልቤ እንድወደው ይፈልጋል።

በመጨረሻ ትምህርቶቹ፣ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች በበረሃ በነበሩበት ጊዜ እንኳን እንዲህ አስታወሳቸው፣ “በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም” (ዘዳግም 2፥7)። አሁን እስራኤላዊያን “[ያልሠሯቸውንም] ከተሞች፣ እና [ያልሞሏቸውንም] ሀብትን የሞሉ ቤቶች” ወደሚገኙበት ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር እየገቡ ሳሉ፣ (ዘዳግም 6፥10–11)፣ ልባቸውን እንዳያጠጥሩ እና ጌታን ይረሳሉ ብሎ ሙሴ ሰግቶ ነበር።

የሙሴን ምክር ስታነቡ የራሳችሁን የልብ ሁኔታ አስቡ። በሚከተሉት ጥቅሶች ላይ ለማተኮር እና የሚሰማችሁን ስሜቶች ለመጻፍ ትፈልጉ ይሆናል፦

ልባችሁን ከመጠጠር ለመታደግ እና ጌታን በሙሉ ልባችሁ ለመውደድ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? በዘዳግም 6፥5–6 እና ማቴዎስ 22፥35–40 መካከል ምን አንድነት ይታያችኋል? (በተጭማሪም ዘሌዋውያን 19፥18ን ይመልከቱ)።

በተጨማሪም ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “A Yearning for Home፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 21–24ን ይመልከቱ።

ዘዳግም 6፥4–12፣ 20–25

“እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።”

ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር የሚገቡ አብዛኛው የእስራኤል ትውልዶች በግብጽ ቸነፈርን አላዩም ወይም ቀይ ባህርን አላቋረጡም። እነርሱ—እናም የወደፊት ትውልዶች—የእግዚአብሔር ህዝቦች ሆነው መቀጠል ካለባቸው የእግዚአብሔርን ተአምራት እና የእግዚአብሔርን ህግጋት ማስታወስ እንድሚያስፈልጋቸው ሙሴ ያውቅ ነበር።

ዘዳግም 6፥4–12፣ 20–25 ውስጥ ሙሴ ከሰጣቸው ምክሮች የትኛው እግዚአብሔር ስላደረገላችሁ ታላቅ ነገር ማስታወስ እንድትችሉ ረዳችሁ? የጌታ ቃል ዘወትር “በል[ባችሁ]” እንዲሆን ምን ለማድረግ ተነሳስታችኋል? (ቁጥር 6)።

እምነታችሁን እንዴት ነው ለወደፊቱ ትውልዶች የምታስተላልፉት?

በተጨማሪም ዘዳግም 11፥18–21፤ ጌሪት ደብልዩ. ጎንግ፣ “ሁልጊዜ አስታውሱት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 108–11፤ የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “Frontlets or phylacteries” ይመልከቱ።

ዘዳግም 15፥1–15

የተቸገሩትን መርዳት በጎ እጆችን እና ፍቃደኛ ልቦችን ያካትታል።

ዘዳግም 15፥1–15 ያጡ እና የተቸገሩትን ስለመርዳት ምክር ይሰጣል፣ በዛሬው ጊዜ የማንከተላቸውን የተወሰኑ ልምዶችንም ያካትታል። ነገር ግን በእነዚህ ጥቅሶች ያጡን ለምን መርዳት እንዳለብን እና እነርሱን ለመርዳት ያለን ባህሪዎቻችን እንዴት ለጌታ ትርጉም እንዳላቸው አስተውሉ። ከእነዚህ ጥቅሶች ሌሎችን ስለማገልገል ጌታ እንድትማሩ የሚፈልገው ምንድን ነው ብላችሁ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ሁለተኛው ታላቅ ትእዛዝ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 96–100 ይመልከቱ።

ዘዳግም 18፥15–19

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሙሴ የሚነሳው ነብይ ነው።

ዘዳግም 18፥15–19 ውስጥ ስላለው ትንቢት ጴጥሮስ፣ ኔፊ፣ ሞሮኒ፣ እና አዳኝም ሃሳብ ሰጥተው ነበር (የሐዋርያት ስራ 3፥20–231 ኔፊ 22፥20–21ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥403 ኔፊ 20፥23ን ይመልከቱ)። ስለአዳኝ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ትማራላችሁ? አዳኝ “እንደ” ሙሴ የሆነው እንዴት ነው? (ዘዳግም 18፥15)።

ኢየሱስ አንድን ሰው ይዞ ተንበርክኮ

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሙሴ ነቢይ ነው።

ዘዳግም 34፥5–8

ሙሴ ላይ ምን ተከሰተ?

ምንም እንኳን ዘዳግም 34፥5–8 ሙሴ መሞቱን ቢናገርም፣ የኋለኛው ቀን መረዳት እንደተለወጠ፣ ወይም ትንሳኤ ከማድረግ በፊት ህመምን ወይም ሞትን እንዳይሰቃይበት እንደተቀየረ ያብራራል (አልማ 45፥18–19፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “ሙሴ”፤ ለቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “የተቀየሩ ሰዎች፤” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgን ይመልከቱ)። ለሙሴ መለወጡ አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም በመለወጥ ተራራ ላይ ለጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐነስ የክህነት ቁልፎችን ለመስጠት አካል ያስፈልገው ነበር (ማቴዎስ 17፥1–13ን ይመልከቱ)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዘዳግም 6፥10–15እነዚህ ጥቅሶች ቤተሰባችሁ የተባረከባቸውን መንገዶች እንዲያስቡ ሊያነሳሳቸው ይችላል። “እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ” የሚለውን ምክር ልንከተል የምንችለው እንዴት ነው? (ዘዳግም 6፥12)። ስለበረከቶቻችሁ የተሰማችሁን በእርግጥ በመዝገብ ወይም በFamilySearch ልትመዘግቡ ትፈልጉ ይሆናል።

ዘዳግም 6፥13፣ 168፥3እነዚህ ጥቅሶች አዳኝን በህይወቱ አስፈላጊ ወቅት ረድተውት ነበር፤ እንዴት እንደሆነ ለማየት፣ አብራችሁ ማቴዎስ 4፥1–10ን አንብቡት። በተቸገርንባቸው ጊዜያት የትኞቹ የቅዱሳት መጻህፍት ንባቦች ረድተውናል?

ዘዳግም 7፥6–9የቤተሰባችሁ አባላት ልዩ እንደሆኑ እንዲሰማቸው የሚወዱትን ምግብ እንደማብሰል አይነት ነገር አድርጉላቸው። ከዚያም ዘዳግም 7፥6–9 አንብቡ እና የጌታ “ቅዱስ ህዝብ” (ቁጥር 6) መሆን ምን ማለት እንደሆነ የሚሰማችሁን ተወያዩበት።

ዘዳግም 29፥12–13ስለ ዘዳግም 29፥12–13 መነጋገር ቤተሰባችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ለሚፈጽሙት ወይም ሰለሚፈጸሙት ቃል ኪዳኖች እንዲወያዩ እድሉን ይሰጣል። የእግዚአብሔር ህዝብ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ቃል ኪዳኖቻችን እንዴት ነው “የ[እግዚአብሔር] ሕዝብ አድርጎ ያስነሣ[ን] ዘንድ” የሚያደርጉን? (ቁጥር 13)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “I Want to Live the Gospel፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 148።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የራሳችሁን መንፈሳዊ ግንዛቤ ፈልጉ። ይህ ዝርዝር የሚተኮርባቸው ምንባቦችን እና መርሆዎችን ይጠቁማል፣ ነገር ግን ያ የእናንተን ጥናት እንዲገድብ አታድርጉ። ስታጠኑም፣ እዚህ ያልተጠቀሰ መርህን ትማሩ ይሆናል። መማር ወዳሚያስፈልጋችሁ ነገሮች መንፈስ ቅዱስ ይምራችሁ።

ሙሴ በተራራ ላይ ቆሞ

ጌታ ምድርን ሁሉ አሳየው፣ በዋልተር ሬን