ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ግንቦት 2–8 (እ.አ.አ)። ዘጸአት 35–40፤ ዘሌዋውያን 1፤ 16፤ 19፥ “ቅድስና ለእግዚአብሔር”


“ግንቦት 2–8 (እ.አ.አ)። ዘጸአት 35–40፤ ዘሌዋውያን 1፤ 16፤ 19፥ ‘ቅድስና ለእግዚአብሔር፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 2–8 (እ.አ.አ)። ዘጸአት 35–40፤ ዘሌዋውያን 1፤ 16፤ 19፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

የሳዎ ፖሎ ብራዚል ቤተመቅደስ

ግንቦት 2–8 (እ.አ.አ)

ዘጸአት 35–40ዘሌዋውያን 11619

“ቅድስና ለእግዚአብሔር”

ቅዱሳት መጻሕፍትን በምታጠኑበት ጊዜ እንደ የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ለመምሰል ስለምትችሉባቸው መንገዶች ለምትቀበሏቸው መንፈሳዊ ግንዛቤዎች ትኩረት ስጡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ግብፅን ትቶ መሄድ አስፈላጊ እና ተአምራዊ ቢሆነም፣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች ያለውን ዓላማ ሙሉ በሙሉ አላከናወንም። በተስፋው ምድር ውስጥ የእነርሱ የወደፊት ብልጽግናም እንኳንየእግዚአብሔር የመጨረሻ ዓላማ አልነበረም። እነዚህ እግዚአብሔር ለህዝቡ በእውነት ወደሚፈልገው መሻገሪያዎች ብቻ ነበሩ፥ “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ” (ዘሌዋውያን 19፥2)። ለትውልድ ከምርኮ በስተቀር ምንም የማያውቁ ሆነው ሳለ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዴት ቅዱስ ለማድረግ ፈለገ? ለጌታ የቅድስና ስፍራ፣ እንዲሁም በምድረበዳ ድንኳን እንዲፈጥሩ አዘዛቸው። ድርጊቶቻቸውን እንዲመሩ እና በመጨረሻም ልባቸውን ለመለወጥ ቃል ኪዳኖችን እና ህጎችን ሰጣቸው። እናም እነዚያን ህጎች ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ሳይሳካላቸው፣ የኃጢአታቸውን ስርየት ለማሳየት የእንሰሳት መስዋእትነት እንዲያደርጉ አዘዛቸው። ይህ ሁሉ አእምሯቸውን፣ ልባቸውን፣ እና ህይወታቸውን ወደ አዳኝ እና እርሱ ወደሚሰጠው ቤዛ ለማመላከት ነበር። እርሱ ለእስራኤላውያን እና ለእኛ ወደ ቅድስና የሚመራ እውነተኛ መንገድ ነው። ሁላችንም በኃጢአት ምርኮ ውስጥ የተወሰነ ጊዜ አሳልፈናል፣ እናም ሁላችንም ወደ ንስሐ እንድንገባ፣ ማለትም ኃጢአትን ተዉ እናም “ቅዱሳን አደርጋችሁ ዘንድ ይቻለኛል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥7) ሲል ቃል የገባውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንከተል ተጋብዘናል።

ስለዘሌዋውያን አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ዘሌዋውያን” የሚለውን ይመልከቱ።

Learn More image
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዘጸአት 35–40ዘሌዋውያን 19

ጌታ እንደ እርሱ ቅዱስ እንድሆን ይፈልጋል።

ዘፀአት 25–31 ጌታ እስራኤላውያን ቅዱስ ህዝብ ይሆኑ ዘንድ የሚረዳቸው ሥነሥርዓቶች የሚሰጥበት ድንኳን የሚሠሩበትን መመሪያ ይዘግባል። ዘፀአት 35–40 እስራኤላውያን እነዚህን መመሪያዎች ለመታዘዝ ያደረጉትን ጥረት ይገልጻል። እናንተ ምዕራፎች 35–40ን ስታነቡ፣ ጌታ ሕዝቡ በድንኳኑ ውስጥ እንዲቀመጡ የጠየቃቸውን ነገሮች ፈትሹ፣ እናም እነዚህ ነገሮች ምን ሊወክሉ እንደሚችሉና በቅድስና ስለመጨመር ለእናንተ ምን እንደሚጠቁሙ አሰላስሉ። በተለይም እነዚህ ነገሮች ሀሳቦቻችሁን ወደ አዳኙ እንዴት እንደሚያዞሩ አስቡ። እንደ እነዚህ ያለ ጠረጴዛ ሊረዳችሁ ይችላል፥

ምን ነገር አገኛችሁ?

ይሄ ምንን ይወክላል?

ምን ነገር አገኛችሁ?

የቃል ኪዳኑ ታቦት (ዘጸአት 37፥1–940፥20–21)

ይሄ ምንን ይወክላል?

የእግዚአብሔር መገኘት፤ የእርሱ ቃል ኪዳኖች እና ትእዛዛት

ምን ነገር አገኛችሁ?

የዕጣን መሠዊያ (ዘጸአት 40፥26–27፤ በተጨማሪም ዘጸአት 30፥1፣ 6–8ን ይመልከቱ)

ይሄ ምንን ይወክላል?

ፀሎቶች ወደጌታ ሲያመሩ

ምን ነገር አገኛችሁ?

የሻማ መቅረዝ ወይም የአምፖል መቅረዝ (ዘጸአት 37፥17–24

ምን ነገር አገኛችሁ?

የመስዋዕት መሠዊያ (ዘጸአት 38፥1–7፤ በተጨማሪም ዘጸአት 27፥129፥10–14ን ይመልከቱ)

ምን ነገር አገኛችሁ?

መታጠቢያ ሰንና (ገንዳ) (ዘጸአት 30፥17–21)

በቤተመቅደስ ሥርዓቶች ውስጥ ከተካፈላችሁ፣ በዘፀአት 35–40 ውስጥ ስለ ድንኳኑ የተማራችሁ በዚያ ስላላችሁ ልምምዶች ምን እንድታስታውሱ ያደረጋችኋል? (በተጨማሪ “Thoughts to Keep in Mind: The Tabernacle and Sacrifice [በአዕምሮ ውስጥ ሊቆዩ የሚገቡ ሀሳቦች፥ ድንኳኑ እና መስዋዕት]” ይመልከቱ)። የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች እንደ ሰማይ አባት እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ቅዱስ እንድትሆኑ እንዴት እንደሚረዱ አስቡበት።

በእርግጥም በተቀደሱ ስፍራዎች መሆናችን ብቻ ቅዱስ አያደርገንም። ዘሌዋውያን 19 እስራኤላውያን በቅድስና እንዲጨምሩ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ህጎች እና ትእዛዛት ይገልጻል። የበለጠ ቅዱስ እንድትሆኑ የሚረዷችሁን በእነዚህ ትእዛዛት ውስጥ ምን አገኛችሁ? በእነዚህ መርሆዎች በበቂ ሁኔታ ለመኖር ምን ለማድረግ ተነሳስታችኋል?

ኬሮል ኤፍ. መኮንኪ፣ “The Beauty of Holiness [የቅደስና ውበት]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017፣ 9–12፤ “The Tabernacle [ድንኳኑ]” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “Holiness”፤ temples.ChurchofJesusChrist.org

ዘጸአት 35፥436፥7

ጌታ በፈቃደኝነት ልቤ አቅርቦቶቼን እንዳቀርብ ይጠይቃል።

ከግብፅ ከወጡ ከአመት በኋላ የእስራኤል ልጆች ከያህዌህ ጋር ያላቸው ግንኙነት የማይጣጣም ነበር ለማለት ይችላል። ሆኖም፣ ዘጸአት 35፥436፥7ን በምታነቡበት ጊዜ እስራኤላውያን ድንኳኑን ለመገንባት በተሰጠው ትእዛዝ ምን ምላሽ እንደሰጡ ልብ በሉ። ከእስራኤላውያን እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ሊረዳችሁ የሚችል ምን ትማራላችሁ?

ፕሬዘዳንት ቦኒ ኤል. ኦስካርሰን እንዳስተማሩት፥ “እያንዳንዱ አባል ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ማወቅ አለበት። እያንዳንዱ ሰው ለማበርከት አንድ አስፈላጊ ነገር አለው እናም ይህንን አስፈላጊ ሥራ አብሮ ለማንቀሳቀስ የሚረዱ ልዩ ተሰጥዖዎች እና ችሎታዎች አሉት” (“በሥራው ላይ ያሉ ወጣት ሴቶች፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 37)። እናንተ ዘጸአት 36፥1–4ን ስታነቡ፣ ጌታ በእናንተ “ያደረገውን” አስቡ። በሥራው ላይ መሳተፍ እንድትችሉ የሰማይ አባት ምን እንደሰጣችሁ ለመጠየቅ አስቡ።

የጥንት ሰዎች ድንኳኑን ለመገንባት ቁርባን ሲያቀርቡ

የእስራኤል ልጆች ለድንኳኑ “በልብ ፍቃድ” ቁርባን አቅርበዋል (ዘጸአት 35፥5)። በኮርበርት ጎዚየር የተሳለ ምስል © Lifeway Collection/licensed from goodsalt.com

ዘሌዋውያን 1፥1–916

በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ይቅር ልባል እችላለሁ።

—እንደ የእንስሳት መስዋዕቶች፣ ደምን እና ውሃን የሚመለከቱ ሥነ ሥርዓቶች እና የህይወትን ዝርዝር ጉዳዮች የሚመለከቱ ሕጎች የያዘው አብዛኛው የዘሌዋውያን መጽሐፍ ለእኛ እንግዳ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ሥነ-ሥርዓቶች እና ህጎች የተለመዱ መርሆዎችን፣ እንዲሁም ንስሀ መግባትን፣ ቅድስናን እና የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ ለማስተማር የተደረጉ ነበሩ። እናንተ እነዚህን መርሆዎች ለማግኘት ዘሌዋውያን 1፥1–916ን ስታነቡ፣ እንደ እነዚህ ያሉትን ጥያቄዎች አስቡባቸው፥ ከእነዚህ መስዋዕቶች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ኃጢአት ክፍያ መስዋእቱ ምን መማር እችላለሁ? እነዚህን መስዋእቶች ካደረጉት ጋር እኔ እንዴት እመሳሰላለሁ? በዚህ ምንጭ ውስጥ “Thoughts to Keep in Mind: The Tabernacle and Sacrifice [ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሀሳቦች፥ ድንኳኑ እና መሰዋዕቱ]” የሚለውን እና በየቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ውስጥ “መስዋዕት” (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ለመገምገም ሊያስቡ ይችላሉ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዘጸአት 36፥1–7ዘጸአት 36፥1–7 ውስጥ እስራኤላውያን ድንኳን እንዲሠሩ ለተሰጣቸው ትእዛዝ ከሰጡት ምላሽ ምን እንማራለን? እንደ ቤተሰብ፣ ጌታ በስራው እንድንሳተፍ የጋበዘንን መንገዶች ማሰብ ትችላላችሁ። የእስራኤላውያንን ምሳሌ እንዴት መከተል እንችላለን?

ዘጸአት 40እናንተ ዘፀአት 40ን አብራችሁ ስታነቡ፣ “ጌታ እንዳዘዘው” ያሉ ሀረጎችን በሰሙ ቁጥር የቤተሰብ አባላት እጃቸውን እንዲያነሱ መጋበዝ ትችላላችሁ። ለጌታ መታዘዝን በተመለከተ ከዚህ ምዕራፍ ምን እንማራለን?

ዘጸአት 40፥1–34እናንተ ዘፀአት 40 ላይ ስለ ድንኳኑ መሰብሰቢያ በምታነቡበት ጊዜ፣ ከዚህ ዝርዝር ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ሥዕል በመጠቀም የድንኳኑን የተለያዩ ክፍሎች ለመለየት በጋራ መሥራት ትችላላችሁ። ይህንን ውይይት በእኛ ዘመን የቤተመቅደስ አምልኮ ጋር ለማገናኘት፣ በጋራ “Why Latter-day Saints Build Temples [የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ለምን ቤተመቅደሶችን ይገነባሉ]” (temples.ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ለመገምገም ወይም “ቤተመቅደሶች” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪዲዮ ለማየት ትችላላችሁ።

ዘሌዋውያን 19የቤተሰብ አባላት እያንዳንዳቸው “ቅዱስ” እንዲሆኑ (ዘሌዋውያን 19፥2) እንደሚረዳቸው የሚሰማቸውን በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ማግኘት እና ለቤተሰቡ ማካፈል ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “የበለጠ ቅድስናን ስጠኝ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 131።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ። መላ ቅዱሳት መጻህፍት፣ እንዲሁም ብልይ ኪዳንን፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራሉ። ብሉይ ኪዳንን በምታነቡበት ጊዜ ምልክቶቹ፣ ህዝቦች እና ክስተቶች ስለ አዳኙ ምን ሊያስተምሯችሁ እንደሚችሉ አስቡ።

ድንኳን

የጥንቱ ድንኳን፣ በብራድሊ ክላርክ