ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ግንቦት 9–15 (እ.አ.አ)። ዘኍልቍ 11–14፤ 20–24፥ “በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ፣ … አትፍሩ”


ግንቦት 9–15 (እ.አ.አ)። ዘኍልቍ 11–14፤ 20–24፥ ‘በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ፣ … አትፍሩ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 9–15 (እ.አ.አ)። ዘኍልቍ 11–14፤ 20–24፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
በረሃ ሸለቆ

ግንቦት 9–15 (እ.አ.አ)

ዘኍልቍ 11–1420–24

“በእግዚአብሔር ላይ አታምጹ፣ … አትፍሩ”

ይህ ዝርዝር በኦሪት ዘኍልቍ ውስጥ ያሉትን ብዙ ጠቃሚ መርሆዎች ያሳያል። መንፈስ ቅዱስ እንድታዩ ለሚረዳችሁ ሌሎች ነገሮችም ክፍት ሁኑ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በእግር እንኳን ቢሆን፣ ከሲና ምድረበዳ ወደ ተስፋው ምድር ወደሆነው ከነዓን ለመጓዝ በተለምዶ 40 ዓመት አይፈጅም። ነገር ግን ያም የእስራኤል ልጆች የጂኦግራፊያዊ እርቀትን ሳይሆን የመንፈሳዊ እርቀትን ለመሸፈን ያስፈለጋቸው ረጅም ጊዜ ነው፥ ማልትም በማን እንደነበሩ እና ጌታ እንደ ቃል ኪዳን ህዝቦቹ እንዲሆኑ በፈለጋቸው መካከል ያለው እርቀት ነው።

የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋው ምድር ከመግባታቸው በፊት መማር የሚያስፈልጋቸውን ትምህርቶች ጨምሮ፣ ኦሪት ዘኍልቍ በእነዚያ 40 ዓመታት ውስጥ የተከናወኑትን አንዳንድ ነገሮች ይገልጻል። እነርሱ በጌታ ለተመረጡት አገልጋዮች ስለመታመን ተምረዋል (ዘኍልቍ 12ን ይመልከቱ)። የወደፊቱ ተስፋ የሌለው ቢመስልም እንኳ የጌታን ሃይል ስለማመን ተምረዋል (ዘኍልቍ 13–14ን ይመልከቱ)። እና እምነት ቢስ መንሆን ወይም አለመተማመን መንፈሳዊ ጉዳት እንደሚያመጣ፣ ነገር ግን ንሰሃ መግባት እና ለመዳን ወደ ክርስቶስ መመልከት እንደሚችሉ ተምረው ነበር (ዘኍልቍ 21፥4–9ን ይመልከቱ)።

ሁላችንም በአንዳንድ መልኩ እንደ እስራኤላዊያን ነን። በመንፈሳዊ ምድረበዳ ውስጥ መሆን ምን እንደሚመስል ሁላችንም እናውቃለን እና ተመሳሳይ የተማሯቸው ትምህርቶች ወደራሳችን የቃል ፥ኪዳን ምድር ለመግባት እንድንዘጋጅ ሊረዱን ይችላሉ ማለትም ከሰማይ አባታችን ጋር ለዘለአለም ለመኖር።

ስለኦሪት ዘኍልቍ አጭር ማብራሪያ በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘኍልቍ” የሚለውን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዘኍልቍ 11፥11–17፣ 24–2912

ራዕይ ለሁሉም ይገኛል፣ ግን እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን የሚመራው በነቢዩ በኩል ነው።

ዘኍልቍ 11፥11–17፣ 24–29፣ ሙሴ የሚያጋጥመውን ችግር እና እግዚአብሔር የሰጠውን ምላሽ አስተውሉ። “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ” ብሎ ሲመኝ ሙሴ ምን ማለቱ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ? (ቁጥር 29)። እነዚህን ጥቅሶች ስታሰላስሉ፣ እነዚህን የፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ቃላቶች አስቡ፥ “እግዚአብሔር በእውነቱ እናንተን ሊናገራችሁ ይፈልግ ይሆን? አዎን! … የሰማይ አባታችሁ እንድታውቁ የሚፈልገው በጣም ብዙ ነገሮች አሉ” (“ራዕይ ለቤተክርስትያኗ፣ ራዕይ ለህይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 95)።

ሆኖም፣ ሁሉም ሰው ነቢይ ሊሆን ይችላል ማለት ሁሉም እንደ ሙሴ የእግዚአብሔርን ህዝብ ይመራሉ ማለት አይደለም። በዘኍልቍ 12 ውስጥ የተመዘገበው ክስተት ይህንን ግልጽ ያደርጋል። ይህንን ምዕራፍ በምታነቡበት ጊዜ ምን ማስጠንቀቂያዎች ታገኛላችሁ? ከእነዚህ ጥቅሶች ሌሎችን ስለማገልገል ጌታ እንድትማሩ የሚፈልገው ምንድነው ብላችሁ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም 1 ኔፊ 10፥17ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥1–7፤ ዳሊን ኤች. ኦክስ፣ “ሁለትዮሽ መገናኛ መስመሮች፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 83–86ን ይመልከቱ።

ዘኍልቍ 13–14

በጌታ ላይ በማመን፣ ለወደፊቱ ተስፋ ሊኖረኝ ይችላል።

እናንተ ዘኍልቍ 13–14 ስታነቡ፣ እራሳችሁን በእስራኤላውያን ቦታ ለማድረግ ሞክሩ። “ወደ ግብፅ መመለስ” ለምን የፈለጉ ይመስላችኋል? (ዘኍልቍ 14፥3)። ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር ለመግባት ተስፋ ቆርጠው እንደነበሩት ናችሁን? ካሌብ የነበረውን ሌላ “መንፈስ” እንዴት ትገልፁታላችሁ? (ዘኍልቍ 14፥24)። ስለ ካሌብ እና ኢያሱ እምነት ምን ያስደንቃችኋል፣ እናም ምሳሌዎቻቸውን በሚገጥሟቸው ሁኔታዎች ላይ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?

በተጨማሪም Teachings of Presidents of the Church: Gordon B. Hinckley [የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፤ ጎርደን ቢ. ሂንክሊይ] [2016 (እ.አ.አ)]፣ 75–76ን ይመልከቱ።

ዘኍልቍ 21፥4–9

ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት ከተመለከትኩ፣ በመንፈስ ሊፈውሰኝ ይችላል።

ዘኍልቍ 21፥4–9 ውስጥ የተመዘገበውን ታሪክ የመጽሐፈ ሞርሞን ነቢያት ያውቁ ነበር እና መንፈሳዊ ጠቀሜታውን ተረድተው ነበር። 1 ኔፊ 17፥40–41አልማ 33፥18–22፤ እና ሔለማን 8፥13–15 ስለዚህ ታሪክ ያላችሁ መረዳት ላይ ምን ይጨምራሉ? እነዚህን ምንባቦች በምታጠናበት ጊዜ ተስፋ ስለምታደርጉት መንፈሳዊ ፈውስ አስብ። ለመፈወስ እስራኤላውያን “የናሱን እባብ [መመልከት]” (ዘኍልቍ 21፥9) ነበረባቸው። ሙሉ ለሙሉ “በእምነት የእግዚአብሔርን ልጅ [ለመመልከት]” ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል? (ሔለማን 8፥15)።

በተጨማሪም ዮሐንስ 3፥14–15ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36፤ ዴል ጂ. ረንላንድ፣ “በበረከቶች የተትረፈረፈ፣” ሊያሆና ግንቦት 2019 (እ.አ.አ.)፣ 70–73 ን ይመልከቱ።

ምስል
የነሃስ እባብ

እስራኤላውያን የናሱን እባብ በመመልከት ዳኑ።

ዘኍልቍ 22–24

ሌሎች እንዳላደርገው ሊያሳምኑኝ ቢሞክሩም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል እችላለሁ።

የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ እስራኤላውያን እየቀረቡ መሆናቸውን ባወቀ ጊዜ በረከትን እና እርግማንን በመናገር የታወቀውን ሰው በለዓምን ጠራ። ባላቅ እስራኤላውያንን በመርገም እንዲያዳክም ፈለገ። ባላቅ በለዓምን ለማሳመን እንዴት እንደሞከረ ልብ አስተውሉ ( ዘኍልቍ 22፥5–7፣15–17)፣ እናም ከእግዚአብሔር ፍላጎት በተቃራኒ እንድትሄዱ የሚገጥሟችሁን ፈተናዎች አስቡ። በዘኍልቍ 22፥18፣ 3823፥8፣ 12፣ 2624፥13 ውስጥ ያለው የበለዓም ምላሽ ምን ያስደንቃችኋል?

አሳዛኙ ነገር፣ በለዓም በመጨረሻ ለውጥረት ተሸንፎ እስራኤልን የከዳ ይመስላል (ዘኍልቍ 31፥16ይሁዳ 1፥11ን ይመልከቱ)። በሌሎች ግፊት ቢኖርም ለጌታ ታማኝ ሆናችሁ ለመቆየት እንዴት እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዘኍልቍ 11፥4–6አመለካከታችን እስራኤላውያን በዘኍልቍ 11፥4–6 ውስጥ ከገለፁት አስተሳሰብ ጋር ተመሳሳይ ነውን? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥15–21 ውስጥ ያለው ምክር እንዴት ይረዳናል?

ዘኍልቍ 12፥3ዘኍልቍ 12 ወይም በሌላ ባነበባችኋቸው የቅዱሳት መጻሐፍት ምንባቦች ውስጥ ሙሴ እንዴት ነበር “እጅግ ትሑት” እንደነበር ያሳየው? ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር በመልእክታቸው ውስጥ ስለ ትህትና የሰጡትን ማብራሪያ መገምገም ትችላላችሁ፣ “የዋህ እና ትሁት ልብ” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 30–33) ወይም በ “የዋህ፣ የዋህነት” በቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)። የበለጠ የዋህ መሆን እንድንችል ምንድን ነው የምንማረው? ያንን ስናደርግ ምን በረከቶች ሊመጡ ይችላሉ?

ዘኍልቍ 13–14ሁለት (ወይም የበለጠ) የቤተሰባችሁ አባላት ሌላ የቤታችሁ አካልን እንደ ቃል ኪዳን ምድር አስመስለው“ይሰልሉ” (ዘኍልቍ 13፥17)። ከዛም በዘኍልቍ 13፥27–33 ወይም በዘኍልቍ 14፥6–9 ላይ በመመርኮዝ ማብራሪያ ይስጡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከሁለቱ የተለያዩ ማብራሪያዎች ምን እንማራለን? እንደ ካሌብ እና ኢያሱ የበለጠ እንዴት መሆን እንችላለን?

ዘኍልቍ 21፥4–9እናንተ ዘኍልቍ 21፥4–9፣ ከ1 ኔፊ 17፥40–41አልማ 33፥18–22፤ እና ሔለማን 8፥13–15 ጋር ካነበባችሁ በኋላ፣ ቤተሰባችሁ ከወረቀት ወይም ከሸክላ እባብ ሊሰሩ እና እላዩ ላይ ወይም በወረቀት ላይ “በእምነት … የእግዚአብሔርን ልጅ [መመልከት]” (ሔለማን 8፥15) ለመቻል ጥቂት ማድረግ የሚችሉትን ይጻፉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “Jesus, the Very Thought of Thee፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 141።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቤተሰባችሁ መንፈሳዊ እራስ መቻልን እንዲያዳብሩ አግዟቸው። “መረጃን ከመስጠት ይልቅ [የቤተሰባችሁን አባላት] በቅዱሳት መጻሕፍት እና በነቢያት ቃላት ውስጥ የወንጌል እውነቶችን ለራሳቸው እንዲያገኙ እርዷቸው” (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኝ መንገድ ማስተማር]፣ 28)።

ምስል
ሙሴ እና የናሱ እባብ

ሙሴ እና የናሱ እባብ፣ በጁዲት ኤ. ሜህር

አትም