ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ልናስታውሳቸው የሚገቡ ሀሳቦች፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ታሪካዊ መጽሐፎች


“ልስታውሳቸው የሚገቡ ሀሳቦች፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ታሪካዊ መጽሐፎች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ልስታውሳቸው የሚገቡ ሀሳቦች፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ታሪካዊ መጽሐፎች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
የሀሳቦች ምልክት

ልናስታውሳቸው የሚገቡ ሀሳቦች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ታሪካዊ መጽሐፎች

ከመጽሐፈ ኢያሱ አንስቶ እስከ አስቴር በተለምዶ የብሉይ ኪዳን “ታሪካዊ መጽሐፎች” ተብለው ይጠራሉ። ይህ ግን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሌሎች መጽሐፎች ታሪካዊ ዋጋ የላቸውም ማለት አይደለም። በምትኩ፣ ታሪካዊ መጽሐፎች ተብለው የተጠሩት የፀሀፊያቸው ዋነኛ አላማዎች የእግዚአብሔርን እጅ በእስራኤል ህዝብ ታሪክ ውስጥ ማሳየት ስለነበረ ነው። አላማው ዘሌዋውያን እና ዘዳግም እንደሚያደርጉት የሙሴን ህግ መዘርዘር አልነበረም። መዝሙረ ዳዊት እና ሰቆቃው ኤርምያስ እንደሚያደርጉት ምስጋናን ወይም በግጥም መልኩ ለቅሶን ለመግለፅ አልነበረም። የ ኢሳይያስ እና የ ሕዝቅኤል መጽሐፎች እንደሚያደርጉት የነብያትን ቃላት መመዝገብም አልነበረም። ከዚያ ይልቅ ታሪካዊ መጽሐፎቹ ታሪክን ይናገራሉ።

የእይታ ጉዳይ

እንደሚጠበቀው፣ ያ ታሪክ የተነገረው ከሆነ እይታ አንፃር ነው—በእርግጥም ከሆነ አመለካከት አንፃር ነው። አበባን፣ ድንጋይን ወይም ዛፍን በአንድ ጊዜ ከአንድ አቅጣጫ በላይ ማየት እንደማይቻል ሁሉ፣ የታሪክ መዝገብ የፀሃፊውን ሰው ወይም የሰዎቸ ስብስብ እይታ ማንፀባረቁ የማይቀር ነው። ይህ እይታ የፀሃፊውን አገር ወይም የጎሳ ትስስር እንዲሁም ባህላዊ እሴቶች እና እምነቶች ያካትታል። ይህን ማወቅ የታሪካዊ መጽሐፎች ፀሃፊዎች እና ሰብሳቢዎች በተወሰኑ ዝርዝሮች ላይ እንዳተኮሩ ሌላዎቹን ደግሞ እንደቀነሱ እንድንገነዘብ ሊረዳን ይችላል።1 ሌሎች ላያደርጉት ይችሉ የነበሩትን ግምቶች አደረጉ። እናም በእነዚያ ዝርዝሮች እና ግምቶች ላይ በመመስረት ወደ ውሳኔ መጡ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉ መጽሐፎች መካከል (እና አንዳንድ ጊዜም በአንድ መጽሐፍ ውስጥ) የተለያዩ እይታዎችን መመልከት እንችላለን።2 እነዚህን እይታዎች የበለጠ ስንገነዘብ ታሪካዊ መጽሐፎችን የበለጠ መረዳት እንችላለን።

ለሁሉም የብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መጽሐፎች የጋራ የሆነ አንዱ እይታ የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝቦች የሆኑት የእስራኤል ልጆች እይታ ነው። በእግዚአብሔር ያላቸው እምነት በሕይወታቸው ውስጥ የእርሱን እጅ እንዲያዩ እና በአገራቸው ጉዳዮች ላይ የእርሱ ጣልቃ ገብነት እንዲኖር ረዳቸው። ዓለማዊ የታሪክ መጽሐፎች ነገሮችን በዚህ መልኩ የማየት ዝንባሌ ባይኖራቸውም ይህ መንፈሳዊ አመለካከት እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ለመገንባት ለሚሹ ሰዎች የብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መጽሐፎችን በጣም ጠቃሚ የሚያደርግ አካል ነው።

አውድ ለተቀረው ብሉይ ኪዳን

ታሪካዊ መጽሐፎቹ የ ዘዳግም መጽሐፍ መጨረሻ ላይ እና የእስራኤላውያን የብዙ ዓመታት የምድረበዳ ውስጥ መንከራተት ሊያበቃ ሲል ይጀምራሉ። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ የእስራኤል ልጆች ወደቃልኪዳን ምድራቸው ወደ ከነዓን ሊገቡ ተዘጋጅተው ያሳያል እናም እንዴት እንዳከናወኑት ይገልፃል። የተከተሉት መጽሐፎች፣ ከ መሣፍንት አንስቶ እስከ 2ኛ ዜና መዋዕል፣ በቃልኪዳን ምድር ውስጥ ከሰፈሩበት ጊዜ አንስቶ በአሦር እና በባቢሎን እስከመማረካቸው ድረስ እስራኤል ያሳለፈችውን ልምድ ይገልፃሉ። የ ዕዝራ እና ነህምያ መጽሐፎች ከአስርተ ዓመታት በኋላ ብዙ እስራኤላውያን ቡድኖች ዋና ከተማቸው ወደሆነችው ኢየሩሳሌም መመለሳቸው ይናገራሉ። በመጨረሻም መጽሐፈ አስቴር በፋርስ ግዛት ስር ይኖሩ ስለነበሩት እስራኤላውያን ታሪክ ይገልፃል።

እዚያ ላይ ነው የብሉይ ኪዳን የታሪክ ቅደም ተከተል የሚያቆመው። የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ጊዜ አንባቢዎች ከግማሽ በላይ የብሉይ ኪዳንን ገፆች አንብበው ሳይጨርሱ የብሉይ ኪዳንን ታሪክ አንብበው በመጨረሳቸው ይገረማሉ። ከ አስቴር፣ በኋላ ስለእስራኤላውያን ታሪክ ብዙ መረጃዎችን አናገኝም። በምትኩ፣ የሚከተሉት መጽሐፎች—በተለይ የነብያት መጽሐፎች—ታሪካዊ መጽሐፎቹ በቀረቡበት የጊዜ መስመር ውስጥ ይገኛሉ።3 ለምሳሌ፣ የነብዩ ኤርምያስ አገልግሎት የ 2ኛ ነገሥት 22–25 (እና በ 2ኛ ዜና መዋዕል 34–36ውስጥ ያለው ተመሳሳዩ ዘገባ) ክስተቶች በተመዘገቡበት ወቅት ተከናወነ። ይህን ማወቅ የታሪካዊ ትረካዎችን እና የትንቢት መጽሐፎችን በሚያነቡበት መንገድ ላይ ተፅዕኖ ሊያደርግ ይችላል።

ምስል
ያልተጨረሰ በጠረጴዛ ላይ ያለ የሚገጣጠም የቁርጥራጭ እንቆቅልሽን የያዘ እጅ

አንዳንድ የቅዱስ ጽሁፍ ምንባቦች ከቀረው የሚገጣጠም እንቆቅልሽ ጋር እንዴት እንደሚገጥም እንደማናውቀው የእንቆቅልሽ ቁራጭ አይነት ሊሆኑ ይችላሉ።

የሆነ ነገር መግጠም ሳይችል ሲቀር

ልክ እንደማንኛውም ታሪክ ብሉይ ኪዳንን ሲያነቡ፣ ለዘመናዊ ዓይኖች ባዕድ ወይም የሚረብሽ የሚመስሉ ነገሮችን ሰዎች ሲያደርጉ ወይም ሲናገሩ ሊያነቡ ይችላሉ። ይህን መጠበቅ ይኖርብናል—የብሉይ ኪዳን ፀሐፊዎች ዓለምን በተወሰነ መልኩ ከእኛ በሚለይ እይታ ተመለከቱ። አመፅ፣ ጎሳዊ ግንኙነቶች እና የሴቶች ሚና የጥንት ፀሐፊዎች ከእኛ በተለየ መልኩ ከተመለከቷቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው።

ስለዚህ በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ የሚረብሹ የሚመስሉ ምንባቦች ሲያጋጥሙን ምን ማድረግ አለብን? መጀመሪያ፣ እያንዳንዱን ምንባብ በሰፊ አውድ ማሰብ ሊረዳ ይችላል። በእግዚአብሔር የደህንነት ዕቅድ ውስጥ እንዴት ይገጥማል? ስለሰማይ አባት እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጥሮ ከሚያውቁት ጋር እንዴት ይገጥማል? በሌላ ቅዱሳን መጽሐፍት ወይም በሕያው ነብያት ትምህርቶች ውስጥ ከተገለፁ እውነታዎች ጋር እንዴት ይገጥማል? እንዲሁም ለልቦት እና ለአዕምሮዎት ሹክሹክታ ከሚያሰማው መንፈስ ጋር እንዴት ይገጥማል?

በተወሰነ መልኩ ምንባቡ ከእነዚህ ጋር በደንብ የሚገጥም ላይመስል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ምንባቡ ካገጣጠሙት የቁርጥራጭ እንቆቅልሾች ጋር የሚገጥም የማይመስል ልክ እንደ አንድ የእንቆቅልሽ ቁራጭ ሊሆን ይችላል። ቁራጩ የግድ እንዲገጥም መሞከር የተሻለ አቀራረብ አይደለም። ነገር ግን በመላ እንቆቅልሹ ላይ ተስፋ መቁረጥም የተሻለ አይደለም። በምትኩ ቁራጩን ለጊዜው ወደ ጎን መተው ይኖርቦት ይሆናል። የበለጠ ሲማሩ እና ብዙ እንቆቅልሾችን አገጣጥመው ሲጨርሱ፣ ቁራጩ እንዴት እንደሚገጥም የበለጠ ለማየት ይችሉ ይሆናል።

በሆነ እይታ ከመወሰኑም በተጨማሪ የቅዱሳን መጽሐፍት ታሪኮች ለሰው ስህተት የተጋለጡ መሆናቸውን ማስታወስ ሊረዳም ይችላል ( የእምነት አንቀፆች 1፥8ይመልከቱ)። ለምሳሌ፣ በብዙ ክፍለ ዘመናት ሂደት ውስጥ የትምህርት እና የስርዓቶች ጠቃሚ እውነታዎችን ጨምሮ “ብዙ ግልፅ እና ውድ ነገሮች [ከመጽሐፍ ቅዱስ] ተወስደው [ነበር]” (1ኛ ኔፊ 13፥28፤ እንዲሁም ቁጥሮች 29፣40ይመልከቱ)። በተመሳሳይ መልኩ የገዛ አመለካከቶቻችን ውስን መሆናቸውን አምነን ለመቀበል ፍቃደኞች መሆን አለብን፦ ሙሉ በሙሉ የማንረዳቸው ነገሮች እና መመለስ የማንችላቸው ጥያቄዎች ሁሌም ይኖራሉ።

ዕንቁዎችን ማግኘት

ነገር ግን ለአሁኑ፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎች በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙት ከውዶቹ የዘላለም እውነት ዕንቁዎች ሊያቆሙን አይገባም—አንዳንድ ጊዜ እነዚያ ዕንቁዎች በሚረብሹ ልምዶች እና ፍፁም ባልሆኑ ሰዎች በሚደረጉ ደካማ ምርጫዎች ድንጋያማ ምድር ውስጥ የተደበቁ ቢሆኑም እንኳን። ምናልባት ከእነዚህ ዕንቁዎች መካከል የበለጠ ውዶቹ ስለእግዚአብሔር ፍቅር የሚመሰክሩት ታሪኮች እና ምንባቦች ናቸው—በተለይ አዕምሯችንን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት የሚጠቁሙት። ከማንኛውም ማዕዘን ቢመለከቷቸው፣ እንደነዚህ ዓይነት ዕንቁዎች ልክ እንደ ከዚህ ቀደም ዛሬም ድረስ በብሩህ ያንፀባርቃሉ። እናም እነዚህ ዘገባዎች ስለእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝቦች በመናገራቸው ምክንያት—እነሱም የሰው ድክመቶች ያሉባቸው ወንዶች እና ሴቶች ቢሆኑም እግዚአብሔርን ስለወደዱ እና ስላገለገሉ—የእውነታ ዕንቁዎች በብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መጽሐፎች ውስጥ ተትረፈረፉ።

ማስታወሻዎች

  1. ዛሬ ያሉን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ ትረካዎች አንዳንድ ጊዜ ከገለፁት ጊዜ በኋላ ለብዙ ዓመታት እንዲሁም ክፍለ ዘመናት የሰሩ በዋናነት ስማቸው ያልተጠቀሰ የብዙ ጸሐፊዎች እና ሰብሳቢዎች ስራ ውጤቶች ናቸው። በተለያዩ ታሪካዊ ምንጮች ላይ ተመርኩዘው በዘገባቸው ውስጥ ምን መጨመር እና ምን መቀነስ እንዳለባቸው ውሳኔዎችን አደረጉ።

  2. ለምሳሌ 1–2ኛ ዜና መዋዕል1ኛ ሳሙኤል31 አንስቶ እስከ 2ኛ ነገሥት፣ መጨረሻ ድረስ ተመሳሳይ የሆነን ጊዜ ቢሸፍንም፣ 1–2ኛ ዜና መዋዕል የተለዩ ዝርዝሮች ላይ ያተኩራል እናም የተለየ አመለካከት ያቀርባል። ከ 1ኛ ሳሙኤል–2ኛ ነገሥትበተቃራኒ፣ 1–2ኛ ዜና መዋዕል በይሁዳ ደቡባዊ መንግስት ላይ ያተኩራል እናም ብዙ ጊዜ ስለዳዊት እና ሰለሞን አሉታዊ ታሪኮችን ያስወግዳል (ለምሳሌ፣ 2ኛ ሳሙኤል 10–121ኛ ዜና መዋዕል 19–20 እና 1ኛ ነገሥት 10–112ኛ ዜና መዋዕል9ጋር ያነፃፅሩ)። ኑ፣ ተከተሉኝ1እና 2ኛ ነገሥትውስጥ ያለን ዘገባ በማጥናት ላይ ያተኩራል፣ ዘገባውን ከ 1እና 2ኛ ዜና መዋዕልጋር ማነፃፀር ጥቅም ቢኖረውም እንኳን። የ 1ኛ ሳሙኤል–2ኛ ነገሥት ስራ የጀመረው የባቢሎን ኢምፓየር ይሁዳን ከመማረኩ በፊት እንደሆነ እና በባቢሎን ስደት ወቅት ስራው እንደተጠናቀቀ ማወቅ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። 1–2ኛ ዜና መዋዕል፣ የሆነው ዘገባ በሌላ መልኩ የተሰበሰበው አይሁዶች ከስደታቸው ወደኢየሩሳሌም ከተመለሱ በኋላ ነበር። ሲያነቡ፣ እነዚህ የተለያዩ ሁኔታዎች በተለያዩ ዘገባዎች ሰብሳቢዎች እይታዎች ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንዳሳደሩ ሊያስቡ ይችላሉ።

  3. በዚህ ግብዓት መጀመሪያ አካባቢ ላይ የእያንዳንዱ ነብይ አገልግሎት ከእስራኤል ታሪክ ጋር እንዴት እንደሚገጥም የጊዜ መስመር የሚያሳይ (እንዲሁም የሚወሰን) “የብሉይ ኪዳን አጠቃላይ እይታ፣” የሚል ያገኛሉ። ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን የትንቢት መጽሐፎች ከዚያ የጊዜ መስመር መጨረሻ አካባቢ ላይ እንደሚገኙ ያስተውላሉ—እሱም የእስራኤል ልጆች በጠላቶቻቸው ከመማረካቸው፣ ከመሰደዳቸው እና ከመበታተናቸው በፊት እና በኋላ ነበር።

አትም