ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፵፮


ምዕራፍ ፵፮

አማሊቅያ ንጉስ ለመሆን አሴረ—ሞሮኒ የነፃነት አርማን አነሳ—ሕዝቡንም እምነታቸውን እንዲከላከሉ አነሳሳቸው—እውነተኛ አማኞች ክርስቲያኖች ተብለው ተጠሩ—የዮሴፍ ቅሪቶች ይጠበቃሉ—አማሊቅያ እና የተገነጠሉት ወደ ኔፊ ምድር ሸሹ—የነፃነትን ጉዳይ የማይደግፉ እንዲሞቱ ተደረገ። ከ፸፫–፸፪ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ የሔለማንንና የወንድሞቹን ቃላት መስማት ያልፈለጉት ሁሉ በወንድሞቻቸው ላይ በአንድነት ተሰባሰቡባቸው።

እናም አሁን እነሆ፣ እነርሱም እስከሚገድሉአቸው ድረስ እጅግ ተቆጥተው ነበር።

አሁን በወንድሞቻቸው ላይ ተቆጥተው የነበሩት መሪ ትልቅና ጠንካራ ሰው ነበር፤ እናም ስሙ አማሊቅያ ተብሎ ይጠራ ነበር።

እናም አማሊቅያ ንጉስ መሆንን ይፈልግ ነበር፤ እናም የተቆጡት ሰዎችም ደግሞ እርሱ ንጉሳቸው እንዲሆንላቸው ይፈልጉ ነበር፤ እናም ብዙዎቹ በምድሪቱ የበታች ዳኞች የነበሩ ናቸው፣ እነርሱም ስልጣንን ይፈልጉ ነበር።

እናም እርሱን የሚረዱትና ንጉሳቸው እንዲሆን የሚያደርጉት ከሆነ በህዝቡ ላይ ገዢ አደርጋችኋለሁ ባላቸው በአማሊቅያ ሽንገላ ተመርተው ነበር።

አዎን በቤተክርስቲያኗ ላይ ሊቀ ካህን ስለነበሩ፣ ምንም እንኳን ሔለማን እና ወንድሞቹ ቢሰብኩም፣ አዎን፣ በቤተክርስቲያኗ ላይ ታላቅ እንክብካቤን ቢያደርጉም፣ በአማሊቅያ ወደ መገንጠል ተመሩ።

እናም በቤተክርስቲያኗ የአማሊቅያን የሽንገላ ቃላት ያመኑ ብዙዎች ነበሩ፤ ስለዚህ ከቤተክርስቲያኗም እንኳን ተገነጠሉ፤ እናም ምንም እንኳን በላማናውያን ላይ ታላቅ ድል ቢያገኙም፣ እና በጌታ እጅ በዳኑበት ደስታቸው እጅግ ታላቅ ቢሆንም፣ የኔፊ ህዝብ ሁኔታም እንደዚህ እጅግ የማያስተማምን እንዲሁም አደገኛ ነበር።

ስለሆነም የሰው ልጆች ጌታ አምላካቸውን እንዴት በፍጥነት እንደሚዘነጉ፣ አዎን፣ ክፋትን ለመስራት፣ እናም በክፉ ሰዎችም ለመመራት እንዴት እንደሚፈጥኑ እንመለከታለን።

አዎን፣ እናም አንድ ኃጢአተኛ ሰው በሰው ልጆች መካከል ለታላቅ ኃጢያት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ደግሞ እንመለከታለን።

አዎን፣ አማሊቅያ የብልጠት ዕቅድ ያለው በመሆኑና፣ ብዙ የሸንጋይ ቃላት ያሉት ሰው በመሆኑ፣ የብዙ ሰዎችን ልብ ክፋት እንዲሰሩ፣ አዎን፣ እናም የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያንና፣ እግዚአብሔር የሰጣቸውን የነፃነት መሰረት፣ ወይም ለፃድቃን ሲል በምድር ገጽ ላይ እግዚአብሔር የላከውን በረከት ለማጥፋት እንደሚመራቸው እንመለከታለን።

፲፩ እናም አሁን እንዲህ ሆነ ሞሮኒ የኔፊ ሠራዊት ዋና ሻምበል የነበረው፣ ይህንን ተቃውሞ በሰማ ጊዜ በአማሊቅያ ላይ ተቆጥቶ ነበር።

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ ኮቱን ቀደደና፣ ቁራጩን ወስዶ በላዩ ላይ አምላካችንን፣ ኃይማኖታችንን፣ እናም ነፃነታችንንና፣ ሰላማችንን፣ እናም ሚስቶቻችንንና፣ ልጆቻችንን ለማስታወስ በማለት ፃፈበትና በእንጨት ጫፍ ላይ አሰረው።

፲፫ እናም የራስ ቆቡንም፣ የደረት ኪሱንም፣ ጋሻውንም አሰረ፣ እናም በወገቡ ላይ ጥሩርን ታጠቀ፤ የተቀደደው ኮቱን ያደረገበትን እንጨትንም ወሰደ (እናም የነፃነት አርማ ብሎም ጠርቶታል) እናም በመሬት ላይ ሰገደና፣ የክርስቲያኖች ቡድን ምድሪቷን የራሳቸው እስካደረጉ ድረስ፣ የነፃነት በረከት በወንድሞቹ ላይ እንዲሆን ወደ አምላኩ በኃይል ፀለየ—

፲፬ እውነተኛ የክርስቶስ አማኞች የነበሩ፣ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል የነበሩ፣ የቤተክርስቲያኗ ባልሆኑትም እንዲህ ተብለው ይጠሩ ነበርና።

፲፭ እናም የቤተክርስቲያኗ የነበሩት ታማኞች ነበሩ፣ አዎን የክርስቶስ እውነተኛ አማኞች የነበሩት በሙሉ የክርስቶስን ስም፣ ወይንም በሚመጣው ክርስቶስ በማመናቸው ክርስቲያን ተብለው የሚጠሩበትን በደስታ ለብሰው ነበር።

፲፮ እናም ስለዚህ፣ በዚህ ጊዜ፣ ሞሮኒ የክርስቲያኖች ጉዳይና የምድሪቱ ነፃነትም ይበልጥ ሞገስን እንዲያገኝ ፀለየ።

፲፯ እናም እንዲህ ሆነ ነፍሱንም ለእግዚአብሔር ባፈሰሰ ጊዜ፣ በወደመው ምድር በስተደቡብ ያሉትን ክፍሎች በሙሉ፣ አዎን፣ እናም በአጠቃላይ በምድሪቱ በሰሜን፣ በደቡብም ክፍል ያለውን በሙሉ ስም ሰጣቸው—የተመረጠች ምድርና የነፃነት መሬት በማለት ሰየመ።

፲፰ እናም እንዲህ አለ፥ በእርግጥ እኛ የክርስቶስን ስም በመልበሳችን የተጠላን በራሳችን መተላለፍን እስከምናመጣ ድረስ እንድንዋረድ እንዲሁም እንድንጠፋ እግዚአብሔር አይፈቅድም።

፲፱ እናም ሞሮኒ እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ የተቀደደውን ልብሱን ከፍ በማድረግ በተቀደደው በኩል የተፃፈውን ሰዎች ሁሉ ያዩለት ዘንድ በአየር ላይ አወዛወዘው፣ እናም ድምፁን ከፍ በማድረግም እንዲህ በማለት ጮኸ፥

እነሆ፣ ማንም ይህንን አርማ በምድሪቱ ላይ የጠበቀ በጌታ ብርታት መጥቶ ከእኔ ጋር ይሁን፣ እናም ጌታ እግዚአብሔር እንዲባርካቸው መብታቸው፣ እናም ኃይማኖታቸውን እንደሚጠብቁ ቃል ኪዳኑ ይግቡ።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ ሞሮኒ እነዚህን ቃላት ባወጀ ጊዜ፣ እነሆ፣ ሰዎቹም ልብሶቻቸውን ለምልክት በመቅደድ ወይንም ጌታ አምላካቸውን እንደማይተዉም ቃል በመግባት፣ ወይም በሌላ አነጋገር የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚተላለፉ ወይንም በመተላለፍ የሚወድቁ ከሆነ እናም የክርስቶስን ስም ለመልበስ የሚያፍሩ ከሆነ እነርሱ ልብሳቸውን እንደቀደዱ ጌታም እነርሱን ይለያቸዋል በማለት የጦር መሳሪያዎቻቸውን በወገባቸው ላይ በመታጠቅ በአንድ ላይ በመሮጥ መጡ።

፳፪ እንግዲህ የገቡት ቃል ኪዳን ይህ ነበር፣ እናም ልብሳቸውንም በሞሮኒ እግር ስር በመጣል እንዲህ አሉ፥ በመተላለፍ የምንወድቅ ከሆነ በምድሪቱ በስተሰሜን እንደነበሩት ወንድሞቻችን እንደምንጠፋ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል፤ አዎን በመተላለፍ የምንወድቅ ከሆነ ልብሶቻችንን እንዲረገጡ በእግርህ ስር እንደጣልናቸው አምላካችንም እኛን በጠላቶቻችን እግር ስር እንድንወድቅ እንዲሁ ያድርገን።

፳፫ ሞሮኒ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፥ እነሆ፣ እኛ የያዕቆብ ዘር ቅሪት ነን፣ አዎን፣ በወንድሞቹ ኮቱ የተቀዳደዱበት የዮሴፍ ዘር ቅሪት ነን፤ አዎን እናም አሁን እነሆ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመጠበቅ እናስታውስ፣ አለበለዚያ ልብሶቻችን በወንድሞቻችን ይቀደዳሉ፣ እናም ወደ ወህኒ ቤት እንጣላለን፣ ወይንም እንሸጣለን፣ ወይንም እንገደላለን።

፳፬ አዎን፣ ነፃነታችንን እንደ ዮሴፍ ቅሪት እንጠብቅ፤ አዎን ከመሞቱ በፊት የነበሩትን የያዕቆብን ቃላት እናስታውስ፣ እነሆም፣ የዮሴፍ ኮት ቅሪት ክፍል የሆኑት እንደተጠበቁና እንዳልበሰበሱም ተመለከተ። እናም እንዲህ አለ—የልጄ ልብስ ቁራጭ እንደተጠበቁ ሁሉ የልጄ ዘር ቅሪቶች በእግዚአብሔር እጅ ይጠበቃሉ፣ እናም ወደ እርሱ ይወሰዳሉ፣ የዮሴፍ ዘር ቅሪቶች ግን እንደ ልብሱ ቁራጭ ቅሪቶች ይጠፋሉ።

፳፭ እናም እነሆ፣ ይህ ነፍሴን ያሳዝናታል፤ ይሁን እንጂ ወደ እግዚአብሔር በሚወሰዱ በእርሱ የዘር ክፍል ምክንያት ነፍሴ በልጄ ትደሰታለች።

፳፮ እንግዲህ እነሆ ይህ የያዕቆብ ቋንቋ ነበር።

፳፯ እናም እንግዲህ የዮሴፍ ዘር ቅሪት የሆኑት፣ እንደልብሱ የጠፉት፣ ከእኛ የተገነጠሉ መሆናቸውንስ ማን ያውቃል? አዎን፣ እናም በክርስቶስ እምነት ፈጥነን ካልቆምን እኛም እራሳችን እንዲሁ እንሆናለን።

፳፰ እናም አሁን እንዲህ ሆነ ሞሮኒ ይህንን በተናገረ ጊዜ ወደ ፊት ሄደ፤ እናም ደግሞ ተቃውሞ ባለበት ምድር ሁሉ መልዕክተኛን ላከና፣ አማሊቅያንና የተገነጠሉት አማሊቅያውያን ተብለው በሚጠሩት ላይ ይነሱባቸው ዘንድ ነፃነታቸውን ለመጠበቅ የሚፈልጉትን ሰዎች በሙሉ በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ አደረገ።

፳፱ እናም እንዲህ ሆነ የሞሮኒ ሰዎች ከአማሊቅያውያን በቁጥር ብዙ መሆናቸውን አማሊቅያ በተመለከተ ጊዜ፣ እናም ደግሞ ህዝቡ ስላደረጓቸው ጉዳዮች ፍትህነት በተመለከተ ጥርጣሬአቸውን ተመለከተ፣ ስለዚህ ዓላማውም አይሳካልኝም ብሎ በመፍራት ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎች ወሰደና፣ ወደ ኔፊ ምድር ሸሸ።

እንግዲህ ሞሮኒም ከእንግዲህ ላማናውያን ከዚህ የበለጠ ብርታት ሊኖራቸው አይገባም ብሎ አሰበ፤ ስለዚህ የአምሊኪውያን ሰዎችን ለማቋረጥ፣ ወይም እነርሱን ለመውሰድና፣ ለመመለስ፣ እናም አማሊቅያን ለመግደል አሰበ፤ አዎን፣ ላማናውያንን በቁጣ በእነርሱ ላይ እንደሚያነሳሳና ከእነርሱ ጋር ለውጊያ እንዲመጡ እንደሚያደርግ አውቋልና፤ እናም አማሊቅያ አላማውን ለማግኘት እንዲህ እንደሚያደርግ ያውቅ ነበር።

፴፩ ስለዚህ ሞሮኒ በአንድ ላይ የሰበሰባቸውንና፣ ያስታጠቃቸውን፣ እናም ሰላምን ለመጠበቅ ቃል እንዲገቡ ያደረጋቸውን ወታደሮች መውሰድ አስፈላጊ ነው በማለት አሰበ፤ እናም እንዲህ ሆነ ወታደሮቹን ወሰደ፣ እናም በምድረበዳው ውስጥ የአማሊቅያን መንገድ ለመስበር ድንኳናቸውን በመያዝ ወደ ምድረበዳው ተንቀሳቀሱ።

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ እንደ ፍላጎቱም አደረገና፣ ወደ ምድረበዳው ዘመተ፣ እናም የአማሊቅያን ሠራዊት እርምጃ አቋረጠ።

፴፫ እናም እንዲህ ሆነ አማሊቅያ ትንሽ ቁጥር ካላቸው ሰዎች ጋር ሸሸና፣ ቀሪዎቹ በሞሮኒ እጅ ገቡ፣ እናም ወደ ዛራሔምላ ምድር ተመልሰው ተወሰዱ።

፴፬ እንግዲህ፣ ሞሮኒ በዋናው ዳኛ የተሾመ፣ እናም በህዝቡ ድምፅ የተመረጠ ሰው በመሆኑ፣ ስለዚህ በኔፋውያን ሠራዊት መካከል በእነርሱ ላይ ስልጣኑን ለመጀመርና ለመመስረትና እንደፈቃዱ ስልጣን በእነርሱ ላይ ነበረው።

፴፭ እናም እንዲህ ሆነ ነፃ መንግስት ያስተዳድሩበት ዘንድ፣ የነፃነቱን መንስኤ ለመርዳት ወደ ቃል ኪዳኑ ያልገቡትን አማሊቅያውያን እንዲገደሉ አደረገ፤ እናም የነፃነቱን ቃል ኪዳን ክደው የነበሩት ጥቂት ብቻ ነበሩ።

፴፮ እናም ደግሞ እንዲህ ሆነ፣ ሞሮኒ በኔፋውያን በተያዙ ቦታ በምድሪቱ ሁሉ ባሉት ሰገነት ላይ የነፃነት ዓርማው እንዲሰቀል አደረገ፤ እናም ሞሮኒ የነፃነት ባንዲራን በኔፋውያን መካከል እንደዚህ ተከለው።

፴፯ እናም በድጋሚ በምድራቸው ላይ ሰላምን ማግኘት ጀመሩ፣ እናም እስከ አስራ ዘጠነኛው የመሣፍንት አገዛዝ መጨረሻ መቃረቢያ ድረስ ምድሪቱ በሰላም ተዳደረች።

፴፰ እናም ሔለማንና ሊቀ ካህናቱም ደግሞ በቤተክርስቲያኗ ስርዓትን አስከበሩ፤ አዎን ለአራት ዓመታት ያህል እንኳን ሰላም በዝቶላቸው እናም በቤተክርስቲያኗም ተደስተው ነበር።

፴፱ እናም እንዲህ ሆነ በፅናት ነፍሳቸው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚድን እያመኑ የሞቱም ብዙዎች ነበሩ፤ ስለዚህ ከዓለምም የወጡት በደስታ ነበር።

እናም በዓመቱ በአንዳንድ ወቅት ውስጥም በምድሪቱ ተደጋጋሚ በነበረው ንዳድ ጥቂቶች ሞቱ—ነገር ግን ሰዎች በተፈጥሮው የአየር ፀባይ ቢገደዱም እግዚአብሔር የበሽታውን መንስኤ ለማስወገድ መልካም ተክሎችን እና ስሮችን በማዘጋጀቱ ብዙዎች በንዳዱ አልሞቱም—

፵፩ ነገር ግን ብዙዎች በእርጅናቸው ሞተዋል፤ እናም እኛ መገመት እንዳለብን ክርስቶስን በማመን የሞቱት በእርሱ ደስተኞች ናቸው።