ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፶፮


ምዕራፍ ፶፮

ሔለማን ከላማናውያን ጋር የነበረውን ጦርነት ሁኔታ በመዘርዘር ለሞሮኒ ደብዳቤ ላከለት—አንቲጱስ እና ሔለማን በላማናውያን ላይ ታላቅ ድል አገኙ—የሔለማን ሁለት ሺህ ብላቴና ወንድ ልጆቹ በአስደናቂ ኃይል ተዋጉ፣ እናም ማናቸውም አልተገደሉም ነበር። ቁጥር ፩ በ፷፪ ም.ዓ. ገደማ፣ ከቁጥር ፪–፲፱ በ፷፮ ም.ዓ. ገደማ፤ እናም ከቁጥር ፳–፶፯ ከ፷፭–፷፬ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ በመሣፍንቱ ሠላሳኛ ዓመት የንግስ ዘመን፣ በመጀመሪያው ወር በሁለተኛው ቀን፣ በዚያች ምድር ክፍል ያሉትን ሰዎች ሁኔታ የሚገልፅ ደብዳቤ ሞሮኒ ከሔለማን ተቀበለ።

እናም የፃፋቸው ቃላት እንዲህ የሚሉ ነበሩ፥ በጌታ እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት በመከራው ጊዜ የተወደድክ ውድ ወንድሜ፣ ሞሮኒ፣ እነሆ፣ የተወደድክ ወንድሜ፣ በዚህች ምድር ጦርነታችንን በሚመለከት በመጠኑ የምነግርህ አለኝ።

እነሆ አሞን ከኔፊ ምድር ያመጣቸው እነዚያ ሰዎች ሁለት ሺህ ወንድ ልጆች—አሁን እነዚህ የአባታችን የሌሂ ትልቅ ልጅ የላማን ዝርያዎች እንደሆኑ ታውቃለህ፤

አሁንም እነዚህን ነገሮች ሁሉ በተመለከተ ስለምታውቅ ስለወጋቸውም ሆነ ስለአለማመናቸው አልነግርህም—

ስለዚህ እነዚህ ሁለት ሺህ ወጣት ሰዎች የጦር መሳሪያዎቻቸውን እንዳነሱ እናም መሪያቸው እንድሆን መፈለጋቸውን መናገር ይበቃኛል፤ እናም እኛ ሀገራችንን ለመከላከል ወደፊት መጥተናል።

እናም አሁን ደግሞ በወንድሞቻቸው ላይ ደም ለማፍሰስ የጦር መሳሪያዎቻቸውን ላለማንሳት አባቶቻቸው የገቡትን ቃል ኪዳን በተመለከተ ታውቃለህ።

ነገር ግን በሀያ ስድስተኛው ዓመት፣ ለእነርሱ የነበረንን ስቃያችንንና መከራችንን በተመለከቱ ጊዜ፣ ቃል ኪዳናቸውን ለማፍረስ እናም እኛን ለመከላከል የጦር መሳሪያዎቻቸውን ለማንሳት ተቃርበው ነበር።

ነገር ግን በወሰዱት ቃል ኪዳን መሟላት መንስኤ በተጨማሪ እንዳንሰቃይ በመፍቀድ እግዚአብሔር ያበረታናል ብዬ በመገመቴ፣ ይህን የገቡትን መሃላ እንዲያፈርሱ አልፈቅድም።

ነገር ግን እነሆ፣ ደስታ የምናገኝበት አንድ ነገር ይህ ነው። እነሆም፣ በሀያ ስድስተኛው ዓመት፣ እኔ ሔለማን፣ የዚያች ምድር መሪ አድርገህ የሾምከውን አንቲጱስን ለመርዳት ወደ ይሁዳ ከተማ እነዚህን ሁለት ሺህ ወጣት ሰዎች በመምራት ዘመትኩ።

እናም ሁለት ሺህ ልጆቼን (ልጆች ተብሎ ለመጠራት ብቁ ነበሩና) ከአንቲጱስ ሠራዊት ጋር ቀላቀልኳቸው፣ በዚህም ኃይል አንቲጱስ እጅግ ተደስቶ ነበር፤ እነሆም፣ የእርሱ ሠራዊት በላማናውያን ተቀንሰው ነበር፣ ምክንያቱም የእነርሱ ኃይል ትልቅ ቁጥር ያለውን ህዝባችንን ገደለውብናልና፣ ለዚህ እንድናዝንም አድርጎን ነበር።

፲፩ ይሁን እንጂ በዚህ ነጥብም እራሳችንን እናፅናናለን፣ እነርሱ የሞቱት ለሀገራቸው፣ እናም ለአምላካቸው መንስኤ ነው፣ አዎን እናም እነርሱ ደስተኞች ናቸው።

፲፪ እናም ላማናውያን ደግሞ ብዙ እስረኞችን ያዙ፣ ሁሉም ዋና አዛዦች ነበሩ፣ ሌሎቹን በህይወት አላተረፉአቸውም ነበር። እናም እነርሱ በዚህን ጊዜ በኔፊ ምድር ነበሩ ብለን እንገምታለን፤ ካልተገደሉ ይህ ነበር ሁኔታው።

፲፫ እናም አሁን የጀግኖቻችንን ደም በማፍሰስ ላማናውያን ያገኙአቸው ከተሞች እነዚህ ናቸው፥

፲፬ የማንቲ ምድር፣ ወይንም የማንቲ ከተማና፣ የዚኤዝሮም ከተማ፣ እናም የቁሜኒ ከተማና፣ የአንቲፓራ ከተማ።

፲፭ እኔ በይሁዳ ከተማ ስደርስ በላማናውያን የተያዙት ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ እናም አንቲጱስና የእርሱ የሆኑት በጉልበታቸው ከተማውን ምሽግ ለማድረግ ሲደክሙ አገኘኋቸው።

፲፮ አዎን፣ እናም ከተማቸውን ለመጠበቅ ሲሉ በቀን በጀግንነት በመዋጋታቸው በምሽትም በድካም ስለሰሩ ሰውነታቸው እንዲሁም መንፈሳቸው ደክሞ ነበር፤ እናም በሁሉም ዓይነት ታላቅ ስቃይ እንደዚህ ተሰቃይተዋል።

፲፯ እናም አሁን እነርሱ በዚህች ስፍራ ለማሸነፍ ወይንም ለመሞት ቆርጠው ነበር፤ ስለዚህ ይህችን ከእኔ ጋር ያመጣኋት ትንሽ ኃይል፣ አዎን የእኔም ልጆች፣ ታላቅ ተስፋንና ብዙ ደስታን እንደሰጡአቸው በሚገባ ልትገምት ትችላለህ።

፲፰ እናም አሁን እንዲህ ሆነ ላማናውያን የአንቲጱስ በወታደሮቹ ታላቅ ብርታትን መቀበሉን በተመለከቱ ጊዜ ለውጊያ በይሁዳ ከተማም ላይ ወይንም በእኛ ላይ በድጋሚ እንዳይመጡ በአሞሮን ትዕዛዛት ተገደዱ።

፲፱ እናም በጌታ እንደዚህ ተወድደን ነበር፤ በድካማችን ላይ ምናልባት ቢመጡ በቁጥር ትንሽ በሆኑት ወታደሮቻችን ባጠፏቸው ነበር። ነገር ግን እኛ እንደዚህ ተጠብቀን ነበር።

እነርሱም የወሰዱአቸውን ከተሞች እንዲያስተዳድሩ በአሞሮን ታዘው ነበር። እናም ሀያ ስድስተኛው ዓመት እንደዚህ ተፈፀመ። እናም በሀያ ሰባተኛው ዓመት መጀመሪያ ከተማችንንና እራሳችንን ለመከላከል አዘጋጀን።

፳፩ እንግዲህ ላማናውያን ወደእኛ እንዲመጡ ፈልገን ነበር፤ ምክንያቱም በጠንካራው ምሽጋቸው ጥቃት ለማድረግ አልፈለግንም ነበርና።

፳፪ እናም እንዲህ ሆነ በስተሰሜን በኩል የሚገኙትን ሌሎች ከተሞቻችንን በምሽትም ሆነ በቀን ላማናውያን አልፈው እንዳያጠቁን እንቅስቃሴአቸውን ለመቆጣጠር በዙሪያችን ሰላዮችን አስቀምጠን ነበር።

፳፫ በከተሞቹም እነርሱን ለመቋቋም በበቂ ሁኔታ ጠንካሮች እንዳልነበሩ እናውቅ ነበርና፤ ስለዚህ እኛን የሚያልፉ ከሆነ ከጀርባቸው ለማጥቃት እናም በተመሳሳዩ ጊዜ በግንባር ከእነርሱ ጋር ከጀርባቸው ለመገናኘት ፈልገን ነበር። ልናሸንፋቸው እንችላለን ብለንም ገምተን ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፣ በዚህም ፍላጎቶቻችን ተበሳጭተን ነበር።

፳፬ በቂ ብርታት ሳይኖራቸው እንሸነፋለን ብለው በመፍራታቸው፣ ከሙሉ ወታደሮቻቸው ጋርም ይሁን ከጥቂቶች አልፈውን ለመሄድ አልደፈሩም ነበር።

፳፭ በዛራሔምላ ከተማም ላይ ቢሆን ለመዝመት አልደፈሩም ነበር፤ በኔፊሃያም ከተማ ላይ የሲዶምን ምንጭ ለማቋረጥ አልደፈሩም ነበር።

፳፮ እናም በነበራቸው ኃይል የወሰዱአቸውን ከተሞች ለመጠበቅ ወስነው ነበር።

፳፯ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ በዚህ ዓመት በሁለተኛው ወር፣ ከሁለት ሺህ ልጆቻችን አባቶች ብዙ ስንቆች መጥተውልን ነበር።

፳፰ እናም ደግሞ ከዛራሔምላ ምድር ሁለት ሺህ ሰዎች ወደ እኛ ተልከው ነበር። እናም ከአስር ሺዎቹ ሰዎች ጋርና፣ ለእነርሱ፣ እናም ደግሞ ለሚስቶቻቸውና ለልጆቻቸው ስንቅ አዘጋጅተን ነበር።

፳፱ እናም ላማናውያን ኃይላችን ቀን በቀን መጨመሩንና፣ ለድጋፋችን ስንቅ እንደደረሰን በመመልከታቸው፣ መፍራት ጀመሩ፣ እናም ስንቅና ሀይል መቀበላችንን ማቆም የሚቻላቸውም ቢሆን ተመኝተው ለጥቃት ገሰገሱ።

እንግዲህ በዚህ መንገድ ላማናውያን መጨነቅ መጀመራቸውን በምንመለከትበት ጊዜ፣ አንድን ዕቅድ በእነርሱ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ፈለግን፤ ስለዚህ አንቲጱስ ከትናንሽ ልጆቼ ጋር ወደ ጎረቤት ከተማ ልክ ወደ ጎረቤት ከተሞች ስንቅ የምንወስደው ያለ በማስመሰል እንድዘምት አዘዘኝ።

፴፩ እናም በባህሩ ዳርቻ ከከተማዋ ርቀን የሄድን በመምሰል ወደ አንቲፓራ ከተማ አጠገብ ዘምተን ነበር።

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ፣ ስንቃችንን የያዝን በመምሰል ወደዚያች ከተማ ለመጓዝ ወደፊት ዘመትን።

፴፫ እናም እንዲህ ሆነ አንቲጱስ የወታደሮቹን ክፍል በመያዝ የተቀሩትን ከተማዋን እንዲጠብቁ በማድረግ ሄደ። ነገር ግን ከጥቂት ወታደሮቼ ጋር ወደፊት እስከምሄድ እናም በአንቲፓራ ከተማ አጠገብ እስከመጣሁ ድረስ አልዘመተም ነበር።

፴፬ እናም አሁን፣ በአንቲፓራ ከተማ የላማናውያን ጠንካራ ወታደሮች ሰፍረው ነበር፤ አዎን፣ በቁጥርም እጅግ ብዙ ነበሩ።

፴፭ እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን በሰላዮቻቸው በተነገራቸው ጊዜ፣ ከወታደሮቻቸው ጋር በመሆን ወደፊት መጡና በእኛ ላይ ዘመቱ።

፴፮ እናም እንዲህ ሆነ ከፊታቸው በሰሜን በኩል ሸሸን። እናም ጠንካራ የነበሩትን የላማናውያን ሠራዊት እንደዚህ በመምራት ከእዚያ አስወጣናቸው፤

፴፯ አዎን፣ የአንቲጳስ ወታደሮች በኃይል እንዳባረሩአቸው በተመለከቱ ጊዜ፣ ወደቀኝም ሆነ ወደግራው እስከማይመለሱበት፣ ነገር ግን ጉዞአቸውን ከኋላችን እኛን በቀጥታ እየተከተሉእስከሚቀጥሉበት በብዙ ርቀትም መራናቸው፤ እናም፣ አንቲጱስ እነርሱ ላይ ከመድረሱ በፊት ዓላማቸው እኛን ለመግደል እንደነበር ገመትን፣ እናም ይህም የሆነው በህዝባችን እንዳይከበቡ ነበር።

፴፰ እናም እንግዲህ አንቲጱስ አደጋ ላይ መሆናችንን በተመለከተ ጊዜ፣ የወታደሮቹን ጉዞ አፋጠነው። ነገር ግን እነሆ፣ ምሽት ነበር፣ ስለዚህ እኛን አልደረሱብንም፣ አንቲጱስም ቢሆን አልደረሰባቸውም፤ ስለዚህ በምሽት ሰፈርን።

፴፱ እናም እንዲህ ሆነ ከመንጋቱ በፊት፣ እነሆ፣ ላማናውያን ያሳድዱን ነበር። አሁን ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት በብቃት ጠንካራ አልነበረንም፤ አዎን፣ ትንሾቹ ወንድ ልጆቼ በእጃቸው እንዲወድቁ አልፈቅድም፣ ስለዚህ ጉዞአችንን ቀጠልን፣ እናም ጉዞአችንን ወደ ምድረበዳው አደረግን።

እንግዲህ እነርሱ እንከበባለን ብለው በመፍራታቸው ወደቀኝም ሆነ ወደግራ ለመዞር አልደፈሩም ነበር፤ ያጠቁኛል ብዬ በመፍራቴ እኔም ወደቀኝም ሆነ ወደግራ አልዞርኩም፣ እናም ጥቃታቸውንም ለመቋቋም አንችልም ነበር፤ ነገር ግን እንገደላለንና እነርሱም ያመልጣሉ፤ እናም ምሽት እስከሚሆንም ድረስ ወደ ምድረበዳው ቀኑን በሙሉ ሸሸን።

፵፩ እናም በድጋሚ እንዲህ ሆነ፣ የጠዋት ፀሀይ በእኛ ላይ ስትሆን፣ ላማናውያን እኛን መቅረባቸውን ተመለከትን፣ እናም ሸሸን።

፵፪ ነገር ግን እንዲህ ሆነ፣ ከመቆማቸው በፊት በርቀት አልተከታተሉንም ነበር፣ እናም ይህ የነበረው በሰባተኛው ወር በሶስተኛው ቀን ጠዋት ነበር።

፵፫ እናም አሁን፣ አንቲጱስ እንደደረሰባቸው አናውቅም ነበር፣ ነገር ግን ለሰዎቼ እንዲህ አልኩ፥ እነሆ፣ በወጥመዳቸው እስከሚይዙን ድረስ ወደ እነርሱም እንድንመጣ ዘንድ ቆመው እንደሆነ አናውቅም፤

፵፬ ስለዚህ ልጆቼ ምን ትላላችሁ፣ እነርሱን ለመዋጋት ትሄዳላችሁን?

፵፭ እናም አሁን እንዲህ እልሃለሁ፥ የተወደድክ ወንድሜ ሞሮኒ፣ እንዲህ ያለን ታላቅ ድፍረትን በጭራሽ በኔፋውያን ሁሉ መካከል አላየሁም።

፵፮ ሁልጊዜም ልጆቼ ብዬ እንደምጠራቸው (ሁሉም ወጣቶች ናቸውና) እነርሱም እንዲህ አሉኝ፥ አባታችን፣ እነሆ አምላካችን ከእኛ ጋር ነው፤ እናም እንድንወድቅ አይፈቅድም፤ እንሂድ፤ ብቻችንን የሚተዉን ከሆነ ወንድሞቻችንን አንግድልም ነበር፤ ስለዚህ የአንቲጱስን ሠራዊት እንዳያሸንፉ ዘንድ እንሂድ።

፵፯ እንግዲህ ፈፅሞ ተዋግተውም አያውቁም፤ ይሁን እንጂ ሞትን አይፈሩም ነበር፤ እናም ከህይወታቸው የበለጠ ለአባቶቻቸው ነፃነት በይበልጥ ያስቡ ነበር፤ አዎን፣ ጥርጣሬ ከሌለባቸው እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸው በእናቶቻቸውም ተምረዋል።

፵፰ እናም እናቶቻቸው የተናገሩትን ቃላት እንዲህ ሲሉም ነገሩኝ፥ እናቶቻችንም ይህን እንደሚያውቁት ጥርጣሬ የለንም።

፵፱ እናም እንዲህ ሆነ እኛን ይከታተሉን ወደነበሩት ላማናውያን ከሁለት ሺህዎቼ ጋር ተመለስኩ። እናም አሁን እነሆ፣ የአንቲጱስ ሠራዊት ደርሰውባቸው ነበር፤ እናም አሰቃቂው ጦርነት ተጀምሮ ነበር።

የአንቲጱስ ሠራዊት በዚያች በትንሽ ጊዜ ረጅም ጉዞ ተጉዘው በመድከማቸው በላማናውያን እጅ ለመውደቅ ተቃርበው ነበር፤ እናም ከሁለት ሺህዎቼ ጋር ባልመለስ ኖሮ ያሰቡት ይሳካላቸው ነበር።

፶፩ በጉዞአቸው ፍጥነት በመድከማቸው፣ አንቲጱስ፣ እናም ብዙዎቹ የእርሱ መሪዎች በጎራዴ ወድቀው ነበር—ስለዚህ መሪዎቻቸው ስለወደቁባቸው የአንቲጱስ ሰዎች በመረበሻቸው ከላማናውያን ፊት ማፈግፈግ ጀምረው ነበር።

፶፪ እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን በረቱና፣ እነርሱን ማሳደድ ጀመሩ፤ እናም ሔለማን ከሁለት ሺህዎቹ ጋር ወደእነርሱ በመጣና በእጅ ይገድሏቸው በጀመሩ ጊዜ ላማናውያን በታላቅ ኃይል እየተከተሏቸው ነበር፣ እናም የላማናውያን ሠራዊት በሔለማን ላይ እስከሚመለሱ ድረስ ያጠቋቸው ጀመር።

፶፫ እናም የአንቲጱስ ሰዎች ላማናውያን መመለሳቸውን በተመለከቱ ጊዜ፣ ህዝባቸውን በአንድ ላይ ሰበሰቡና፣ እንደገና በላማናውያን ጀርባ ላይ መጡባቸው።

፶፬ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ እኛ የኔፊ ህዝብ፣ የአንቲጱስ ህዝብና እኔ ከሁለት ሺህዎቼ ጋር ላማናውያንን ከበብንና፣ ገደልናቸው፤ አዎን፣ የጦር መሳሪያዎቻቸውን እስከሚያስረክቡ፣ እናም ደግሞ እራሳቸውን የጦር ምርኮኛ እስከሚያደርጉ ድረስ ተገደሉ።

፶፭ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ በእኛም ሙሉ በሙሉ በምርኮ ከተያዙ በኋላ፣ እነሆ፣ ብዙ ወጣቶች ተገድለዋል ብዬ በመፍራቴ ከእኔ ጋር የተዋጉትን ወጣቶች ቆጠርኳቸው።

፶፮ እናም እነሆ፣ ለእኔ ታላቅ ደስታ የሆነው ከእነርሱ አንዲትም ነፍስ መሬት ባለመውደቋ ነበር፤ አዎን፣ በእግዚአብሔርም ጥንካሬ እንደተዋጉ ያህል ነበር፤ አዎን፣ ሰው በጭራሽ በእንደዚህ ዓይነት ታምራዊ በሆነ ጉልበት ተዋግቶ አይታወቅም ነበር፤ እናም በአስገራሚ ኃይል በላማናውያን ላይ ስለወደቁ፣ አስፈርተዋቸውም ነበር፤ በዚህም የተነሳ ላማናውያን እራሳቸውን የጦር ምርኮኛ አድርገው ሰጡ።

፶፯ እናም፣ ከላማናውያን ወታደሮች እንጠብቃቸው ዘንድ ለእስረኞቻችን ቦታ ስለሌለን፤ ስለዚህ ወደ ዛራሔምላ ምድር ላክናቸው፤ ያልሞቱትን የአንቲጱስ ሰዎችንም ከእነርሱ ጋር ልከናቸዋል፤ እናም የተቀሩትን ወስጄ ከብላቴና አሞናውያን ጋር አደባለቅሁአቸው፤ ጉዞአችንንም ወደ ይሁዳ ከተማ አደረግን።