2022 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዬን ታጥቄ
ጥር 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልዕክት

የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዬን ታጥቄ

ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን የመያዝ ሃላፊነትን ከልብ እንውሰደው—ከጠላት የሚጠብቅ “መንፈሳዊ መሳሪያ” ነው።

በአዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት የመጨመር አንዱ መንገድ ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን መያዝ ነው። ጠላት ከእውነት ሊያርቀን ከሚያደርገው የሙከራ ዕቅድ እንደምንጠበቅ ትልቅ የእምነት ምልክት ወይም መሳሪያ ነው።

በአጠቃላይ መመሪያዎች መጽሃፍ ውስጥ “ቤተመቅደስ ውስጥ መግባት ቅዱስ የሆነ መብት”.1 እንደሆነ ተነግሮናል። “በቤተመቅደስ አቅራቢያ ባንኖርም እንኳን”2 ብቁ ለመሆን እና ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለመያዝ መጣር አለብን። ለቃለ መጠይቃችን ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም ወደቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ ስንሄድ፣ ውስን የሆነ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ይሁን በህይወት ላሉ ለሚደረግ ስርዓቶች የሚውል ፈቃድ ወይም የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ እንደሚያስፈልገን ይወስናል።

የአስራ ሁሉቱ ሐዋርያት ጉባኤ አባል ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ እሳቸው እና ባለቤታቸው የታመሙ አማቻቸውን ለመጎብኘት ሲሄዱ የተማሩትን “ታላቅ ትምህርት” ያካፍላሉ። ሲደርሱ ኤጲስ ቆጶሱ ከአማቻቸው ቤት ወጥተው ሲሄዱ አገኟቸው። ሽማግሌ ራስባንድ የወንድ አማቻቸው ኤጲስ ቆጶሱን ለቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ እንዲያደርጋቸው እንደጋበዙት ተረዱ ምክንያቱም በራሳቸው ቃላት እንዲህ አሉ፣ “ለጌታ ብቁ ሆኜ መሄድ እፈልጋለሁ”።3

እናም ሽማግሌ ራስባንድ እንዲህ አሉ፣ “ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሄዱ”።

እኛም በቀን ተቀን ሕይወታችን ውስጥ ለጌታ ብቁ መሆን ይኖርብናል፤ በአንድ ብቁ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተቀመጡ መስፈርቶች በመኖር የሚመጡትን በረከቶች ለማጣጣም ለጌታ ብቁ መሆን ይኖርብናል። የተወሰኑት እነዚህ እሴቶች እውነተኛነትን፣ ንፅህናን፣ ታማኝነትን፣ታዛዥነትን፣ የጥበብ ቃልን መጠበቅን፣ የአስራት ህግን መጠበቅን እና የሰንበት ቀንን ማክበርን ያካትታሉ።

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ኤጲስ ቆጶስ ሳለሁ በጣም ጥሩ የአጥቢያ አባል ለሆነ ለአንድ መልካም ወንድም የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ አደረኩኝ። ሁሉም በመልካም ሁኔታ ሄደ እንዲህ የሚለው ጥያቄ ላይ እስክንደርስ ድረስ፣ “አስራትህን ትከፍላለህን?” ከዚያ መንተባተብ ጀመረ፤ ቃላት በግልፅ መውጣት አቃታቸው። አይኑን በቀጥታ ተመለከትኩኝ እና በድጋሜ እንዲህ ስል ጠየኩኝ፣ “አስራትህን ትከፍላለህ?”

ከዚያም መልሱ በዝግታ እንዲህ ሲል መጣ፣ “አብዛኛውን ጊዜ ሲከፈለኝ ብዙ የሚያስገድዱ ፍላጎቶች ስላሉኝ እና ገንዘቡ ሁሉንም ወጪ ለመሸፈን በቂ ስለማይመስል የአስራት አከፋፈሌ ወጥነት የለውም።” ይህ በጌታ እንደታዘዘው እውነተኛ እና ሙሉ አስራትን ስለመክፈል መርሆ እርሱን ለማስተማር እድል እንደነበረ አወቅኩኝ። ከዚያም ለመሄድና የሙሉ አስራት ከፋይ ለመሆን ቃል የገባውን ለመተግበር ጊዜ እንዲሰጠው ጠየቀ። የእሱን ብቁነት ለማረጋገጥ ሌላ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ስድስት ወር ወሰደ። በእርግጥ በትክክለኛው መንገድ ትንሽ እርምጃን ማድረግ ጀምሮ ነበር።

አጠቃላይ መመሪያዎች መጽሃፍ እንደሚያስተምረን “የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቆች አባሎች ምስክርነት እንዳላቸው እና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንደሚጠብቁ እንዲሁም ነብያቱን እንደሚከተሉ ለማሳየት ያስችላሉ።”4

የራሳቸውን ቡራኬ የሚቀበሉ አባሎች በመመሪያ መጽሃፉ ውስጥ ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፦

  • ቢያንስ 18 ዓመት መሆን አለባቸው፤

  • ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ተመሳሳይን መጨረስ ይኖርባቸዋል ወይም አሁን እየተማሩ ያሉ መሆን የለባቸውም፤

  • ማረጋገጫቸውን ከተቀበሉ ሙሉ አንድ ዓመት ሊሆናቸው ይገባል፤ እንዲሁም

  • አንድ ሰው ቡራኬውን ከመቀበሉ በፊት የመልከጸዴቅ ክህነትን መያዝ ይኖርበታል5

ለአንድ ዓመት ከሚሆነው ለህያዋን ስርዓቶችን ለመፈጸም ከሚውለው የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ በስተቀር የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለሁለት ዓመታት እንደሚያዝ ማስታወስ ይኖርብናል። መታወቂያው የአገልግሎት ዘመኑ ሲያበቃ እባካችሁን ለቃለ መጠይቅ እና ለእድሳት ወደ ኤጲስ ቆጶሳችሁ ወይም ወደ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንታችሁ መመለስን ሁልጊዜ አስታውሱ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ የመያዝን ሃላፊነት እንድትወስዱ አበረታታችኋለሁ – ከጠላት የሚጠብቅ “መንፈሳዊ መሳሪያ” ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳን ውስጥ በአዳኛችን እንደዚህ ተመክረናል፦

“ራሳችሁን አደራጁ፤ አስፈላጊ ነገሮችሁን ሁሉ አዘጋጁ፤ ቤትን፣ እንዲሁም የጸሎትን ቤት፣ የጾምን ቤት፣ የእምነትን ቤት፣ የእምነትን ቤት፣ የእውቀትን ቤት፣ የክብርን ቤት፣ የስርዓትን ቤት፣ የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ።”6

ያንን ምክር የመስማት ሃላፊነታችን ሳይሳካ ሲቀር እና በመንገዱ ላይ ወደ ኋላ ስንቀር፣ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያችንን የመጠቀም እድልን ኤጲስ ቆጶስ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዝዳንት ሊያነሱት እንደሚችሉ እናስታውስ። ሁሌም “ከላይ የሚመጣው እርሱ ቅዱስ እንደሆነ [እና]ስታውስ”7 እንዲሁም “በአንተ እምነት ውስጥ ካልሆኑ በስተቀር ስጦታህን ለማንም [እንዳና]ሳውቅ”8 እንደተነገረን እናስታውስ።

ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን ስንይዝ በጌታ ሰራዊት ውስጥ እንደ ጀግና ወታደሮች እንቆማለን፦ “እና ትዕዛዛትን በማክበር እነዚህን ነገሮች የሚጠብቁ እና ለማድረግ የሚያስታውሱ ቅዱሳን ሁሉ ለስጋቸው ፈውስ እና ለአጥንታቸው መጠገንን ይቀበላሉ፤ እናም ጥበብ እና ታላቅ የእውቀት ሀብቶች እንዲሁም የተሰወሩ ሀብቶችንም ያገኛሉ። እናም ይሮጣሉ አይታክቱም፣ ይሄዳሉ አይደክሙም። እና እኔ ጌታ አጥፊው መልአክ የእስራኤል ልጆችን እንዳለፋቸው እነሱን ያልፋቸው ዘንድ እና እንዳይገድላቸውም ዘንድ የተስፋ ቃል እሰጣቸዋለሁ። አሜን።”9

ፍሬድሪክ ኤም. ካምያ እንደ አካባቢ ሰባዎች በሚያዚያ 2021 (እ.አ.አ) ውስጥ ተጠሩ። ከስቴላ ካምያ ጋር ትዳራቸውን መስርተዋል፤ የስድስት ልጆች ወላጆች ናቸው። በካምፓላ፣ ዩጋንዳ ውስጥ ይኖራሉ።

ማስታወሻዎች

  1. General Handbook: Serving in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints, 26.0, ChurchofJesusChrist.org።

  2. ሮናልድ ኤ. ራስባንድ፣, “Recommended to the Lord”, ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) ይመልከቱ።

  3. ሮናልድ ኤ. ራስባንድ፣, “Recommended to the Lord”, 23።

  4. General Handbook, 26.3, ChurchofJesusChrist.org

  5. General Handbook, 26.5.1, ChurchofJesusChrist.org።

  6. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 88፥119።

  7. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 63፥64።

  8. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 6፥12።

  9. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 89፥18–21።

አትም