2022 (እ.አ.አ)
‘ቀኑን መጠበቅ’፦ አባላት ለዲ.አር.ሲ ቤተመቅደስ እንዴት እንደተዘጋጁ
ጥር 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ ገጾች

‘ቀኑን መጠበቅ’፦ አባላት ለዲ.አር.ሲ ቤተመቅደስ እንዴት እንደተዘጋጁ

The outgoing temple president of the Kinshasa Democratic Republic of the Congo Temple looks back on the excitement and preparation of the saints as the temple opened.

የጌታ ቤት ጉልላት ጫፍ በዲ.አር.ሲ ኪንሻሳ የምሽት ሰማይ ላይ ወደ ሰማያት ይደርሳል። በደጁ ለሚያልፉ እና የተዋበውን የቤተመቅደስ ግቢ ለሚመለከቱ ሁሉ የሰላም እና የመረጋጋት ጊዜን ይፈጥራል። አባላት ቶሎ ቶሎ እንዲመጡ፣ ከጌታ ጋር ቃል ኪዳኖቻቸውን እንዲያደርጉ እና እንዲያድሱ እንዲሁም በሕይወታቸው ውስጥ የጌታ መገኘት እና ምክር እንዲሰማቸው የሚያሳስብ ነው።

ጥቅምት 1 ቀን 2011 (እ.አ.አ) ፕሬዝዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን (1927–2018) በአለም 163ኛው ቤተመቅደስ በዲ.አር.ሲ ኪንሻሳ እንደሚገነባ አስታወቁ። በወቅቱ የኪንሻሳ ሚስዮን ፕሬዝዳንት የነበሩት ፕሬዝዳንት ብሬንት ጄምሰን ይህን ትውስታ ያካፍላሉ፦

“በየስድስት ሳምንቱ ራቅ ወደሚሉት የቤተክርስቲያኗ ክፍሎች እንጓዛለን። በፑዋንት ኑዋ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ የሚፈልጉ ጥቂት አባላት እንዳሉና ሁሉም በአዳራሹ ውስጥ እንደተሰለፉ ባመለከተው የቅርንጫፍ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገልን። ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ወይም አዲስ ለማግኘት የሚጠብቁ አስራስድስት ሰዎች ነበሩ! ይኸው ዓይነት ተሞክሮ በጎበኘናቸው ቦታዎች ሁሉ ተከስቷል። ከፍተኛ የገንዘብ መስዋዕትነት በመክፈል፣ የብዙ ሰዓታት ጉዞ በማድረግ፣ እንዲሁም ፈቃድ ከማሳደስ ወይም አዲስ ከማግኘት በስተቀር ያለምንም ሌላ ምክንያት መጥተው ነበር። እነዚህ አባላት የታደሰ ፈቃድ የመያዝን አስፈላጊነት ተረድተዋል። ወንጌልን ለመኖር ምን ያህል ቁርጠኛ እንደሆኑ እና ቃል ኪዳናቸው ለእነሱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደነበረ ለጌታ እንዳሳየ ያውቁ ነበር። ወደ ቤተመቅደስ ሊገቡም ላይገቡም እንደሚችሉ ያውቁ ነበር፤ ነገር ግን እድሉ በመጣ ጊዜ ለመግባት እና ቃል ኪዳናቸውን ለማድረግ ዝግጁ ለመሆን ይፈልጋሉ። ፈቃዶቻቸው ለእነሱ እና ለጌታ አንድ አስፈላጊ ነገር ማለት ነበር።”

በኋላም በ2018 (እ.አ.አ) ፕሬዝዳንት ጄምሰን ይህንን ስሜት ቀስቃሽ ልምድ ያካፍላሉ፦

“የኪንሻሳ ቤተመቅደስ ፕሬዝዳንት እና ሜትረን ተደርገን ተጠራን። ስለዚህ በተቻለ መጠን ብዙዎች ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ዝግጁ ይሆኑ ዘንድ ለታሰበው የመግቢያ ፈቃድ ቃለመጠይቆችን የማካሄድ ዓላማ ቀደም ብለን መጣን። በቤተመቅደስ ውስጥ ሰራተኞች ሆነው ያገለግሉ ዘንድ በጎ ፈቃደኞችን ጠየቅን። ወዲያውኑ 250 ፈቃደኛ ሠራተኞች ቀረቡ፤ እያንዳንዳቸውም ትክክለኛ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ነበራቸው! ቀኑን እየጠበቁ ነበር! አብዛኞቹ በቤተመቅደስ ውስጥ የተገኙት ቡራኬዎቻቸውን ሲቀበሉ ለአንድ ጊዜ ብቻ ነበር።—አብዛኞቹ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች ነበሩ—ነገር ግን በድጋሚ ለመሳተፍ እድል አላገኙም ነበር። መደበኛው በቤተመቅደስ የመሳተፍ ቀን ደረሰ!”

ዛሬ ነሃሴ 2021 (እ.አ.አ) ጌታ አዲስ የቤተመቅደስ አመራር ከኮንጎ አባላት መርጧል፦ ኤም. ፍራንስዋ ሙኩቡ ፕሬዝዳንት፣ ካቡና ኬ. ሺሙንጉ የመጀመሪያ አማካሪ፣ ዡለ ቦፋንጋ ሁለተኛ አማካሪ። ቀኑ ደረሰ። ፕሬዝዳንት ኔልሰን እንዳሉት፣ “ቤተመቅደስን በውስጣችሁ አድርጉ እንዲሁም ራሳችሁን በቤተመቅደስ ውስጥ አድርጉ።”

አትም