2022 (እ.አ.አ)
ጥር 1993 (እ.አ.አ)፦ የመጀመሪያው ቅርንጫፍ በካሜሩን
ጥር 2022 (እ.አ.አ)


ወሩ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ

ጥር 1993 (እ.አ.አ)፦ የመጀመሪያው ቅርንጫፍ በካሜሩን

ዠርቬ ጀራርድ ዛንግ በፈረንሳይ ናንት የጥርስ ቀዶ ጥገና ህክምና እያጠና በነበረበት ጊዜ የካቶሊክ እምነቱ ያልመለሳቸው ህይወትን የተመለከቱ ብዙ ጥያቄዎች እየተፈጠሩበት መጡ። ብዙ ቤተክርስቲያኖችን መመርመር ጀመረ እናም በዚህ መንገድ ላይ እያለ ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሚስዮናውያን ጋር ተገናኘ። ህዳር 11 1989 (እ.አ.አ) ተጠመቀ፤ ከጥቂት ወራት በኋላም የመልከጸዲቅ ክህነትን ተቀበለ፤ እንዲሁም በቤተክርስቲያኗ ሽማግሌ ሆኖ ተሾመ። በጥርስ ቀዶ ጥገና ህክምና ዲፕሎማውን ካገኘ በኋላ ወደካሜሩን ተመለሰ።

ጥር 10 1993 (እ.አ.አ) በካሜሩን የመጀመሪያው የቤተክርስቲያኗ ቅርንጫፍ ተደራጀ። ባስቶስ የተሰኘው ቅርንጫፍ የተቋቋመው በያውንዴ ካሜሩን ወንድም ዛንግን የቅርንጫፉ ፕሬዝዳንት በማድረግ ነበር።

በዚያው አመት መስከረም ውስጥ ቤተክርስቲያንዋ በካሜሩን ፕሬዝዳንት ህጋዊ እውቅና ተሰጣት። መንግስት እውቅና ከመስጠቱ በፊት ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎች ተጠምቀው ነበር፤ እንዲሁም ሌሎች 60 ቤተክርስቲያኗን የሚመረምሩ በእሁድ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፉ ነበር።—እህት ጁሊ ብራፍ፣ በማዕከላዊ አፍሪካ የቤተክስቲያን ታሪክ ሚስዮናዊ

አትም