2022 (እ.አ.አ)
ስለአሮናዊ ክህነት ይበልጥ መማር
ጥር 2022 (እ.አ.አ)


የቃል ኪዳን መንገዴ

ስለአሮናዊ ክህነት ይበልጥ መማር

ዕድሜያቸው አስራአንድ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች የእግዚአብሔርን ሥልጣን በጽድቅ በመጠቀም የሌሎችን ሕይወት በምድር እንዴት እንደሚባርኩ እወቁ።

ለምቃዲ ቤተሰብ ምንኛ አስደሳች ቀን ነው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ የቤተመቅደስ በሮች ለ14 ረዥም ወራት ተዘግተው ከቆዩ በኋላ ናላ ምቃዲ (ዕድሜዋ 11 ዓመት ነው) በመጨረሻ በሰኔ 2021 (እ.አ.አ) ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተመቅደስን የመጎብኘት ዕድል አግኝታለች።

ከዚያም በኋላ ናላ የተገኘውን ተሞክሮ ወደኋላ መለስ ብላ በመመልከት የተሞክሮውን አንዳንድ ዋና ዋና ነጥቦች ጠቅሳለች። ሰላሙን እና የህንጻውን ንጽህና ወዳዋለች። በታላቅ ወንድሟ በንታንዶ መጠመቅ መቻሏንም ወዳዋለች።

ንታንዶ (15 አመቱ ነው) የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ ስለሆነ ይህንን ቅዱስ ሥርዓት ማከናወን ችሏል። በቅርቡ በክህነት ማዕረግ ተሹሞ ነበር።

ክህነት ዕድሜያቸው 11 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ብቁ ወንዶች የተሰጠ የእግዚአብሔር ኃይል እና ስልጣን ነው። አሮናዊ ክህነት የመነሻ ወይም የዝግጅት ክህነት ነው። በአሮናዊ ክህነት የተሾሙ አዋቂ ወንዶች እና ወንዶች ልጆች ቅዱስ ቁርባንን የማሳለፍ፣ የማዘጋጀት እና የመባረክ እንዲሁም ሌሎችን የማጥመቅ ስልጣን አላቸው።

ጆሴፍ ስሚዝ ኢየሱስን ባጠመቀው በራሱ በመጥምቁ ዮሐንስ የአሮናዊ ክህነት በ1829 (እ.አ.አ) ተሰጠው። የአሮናዊ ክህነትን መቀበል እና መጠቀም ወንዶች ከፍ ያለውን ወይም የመልከ ጸዲቅ ክህነትን ለመቀበል ያዘጋጃቸዋል።

“እህቴን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማጥመቅ እድል ማግኘቴ አስደናቂ ነበር” ሲል ተናግሯል። “በቤተመቅደስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማጥመቅ በቻልኩኝ ጊዜ እናቴንም አጠመቅኳት። ቤተመቅደስን የመጠቀም ቁልፍ አለኝ እንዲሁም ቅዱስ ስርዓቶችን የመፈጸም ችሎታ አለኝ። በእውነት በእርሱ ተባርኬአለሁ እንዲሁም ጌታን በእርሱ ቤተመቅደስ ውስጥ በማገልገል የሚገኝን በረከት ተቀብያለሁ።”

የምቃዲ ቤተሰብ ተሞክሮ እንደሚያሳየው ክህነትን የሚሸከሙት ወንዶች ቢሆኑም እርሱ ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች ለመባረክ ያገለግላል።

ፕሬዝዳንት ዳልን ኤች. ኦክስ እንዲህ ብለዋል “የክህነት ሃይል ሁላችንንም ይባርከናል። የክህነት ቁልፍ ወንዶችንም ሴቶችንም ይመራል፤ እንዲሁም የክህነት ሥርዓቶች እና የክህነት ስልጣን ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል።”1

በኋላም ናላ “ወደቤተመቅደሱ ስገባ እንደተባረኩኝ ተሰማኝ፣” “በወንድሜ መጠመቅ አሪፍ ነበር።” ስትል ሃሳብ ሰጥታለች።

ለናላ ታላቅ ወንድም ለንታንዶ እንዲሁ ብዙ ነገሮችን ለመጀመሪያ ጊዜ የማድረጊያው ጊዜ ነበር። የውክልና ጥምቀቶችን በቤተመቅደስ ውስጥ ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜው ነበር። ለቤተሰቡ አባላት ይህንን ማድረግ መቻሉ ለእሱ ትርጉም ያለው ነገር ነበር።

ወንድምና እህት የሆኑት ልጆች እናት ሼፒሶ እንዲህ ብላለች “ከናላ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተመቅደስ መሳተፍ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ ንታንዶ በቤተመቅደስ የአሮናዊ ክህነቱን ለናላ ሲጠቀም ማየት እና ንታንዶ በመጠመቂያው ቦታ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሮናዊ ክህነትን ሲጠቀም ማየት ለእኔ በጣም ልዩ ነበር።

“ስለቤተመቅደሱ እና በውስጡ ስለሚሰጠው አገልግሎት መለኮታዊነት ስለመሰከረላቸው መንፈስ አመስጋኝ ነኝ። ሁለቱም በድጋሚ በቤተመቅደስ ጥምቀት ለመሳተፍ በጉጉት ሲጠይቁ ልቤ ተነካ። ሲያድጉ ይህ ተሞክሮ ለመሳተፍ የበለጠ ለማድረግ እና የጌታ ሥራ አካል እንዲሆኑ በውስጣቸው ፍላጎት እንዲቀጣጠል እንዲያደርግ ጸሎቴ ነው።”

ማስታወሻዎች

  1. ዳልን ኤች. ኦክስ, “The Keys and Authority of the Priesthood,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 እ.አ.አ።

አትም