2022 (እ.አ.አ)
የመመሪያ መጽሃፉ ስለጥሪያችሁ እንዴት የበለጠ እንድትማሩ ሊረዳችሁ እንደሚችል
ጥር 2022 (እ.አ.አ)


በመመሪያ መጽሃፍ ውስጥ ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦች

የመመሪያ መጽሃፉ ስለጥሪያችሁ እንዴት የበለጠ እንድትማሩ ሊረዳችሁ እንደሚችል

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ከሚያስገኛቸው በጣም የሚያረኩ ገጽታዎች አንዱ ጥሪዎችን እና የስራ ምደባዎችን በመቀበል ለማገልገል የምታገኙት ዕድል ነው።እነዚህ ብዙ ዓይነት አገልግሎቶችን የሚያካትቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ የበጎ ፈቃደኞች የስራ ድርሻዎች ናቸው። ለምሳሌ የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪ፣ የወጣት ወንዶች አማካሪ፣ በቅርንጫፍ አመራር ውስጥ ጸሃፊ፣ የካስማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ጸሃፊ፣ የሽማግሌዎች ቡድን አማካሪ፣ የአጥቢያ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ወይም የቅርንጫፍ የታሪክ ባለሙያ ሆናችሁ ልትጠሩ ትችላላችሁ።

ጥሪያችሁን ከተቀበላችሁ፣ በክፍላችሁ አባላት ድጋፍ ከተሰጣችሁ እና የክህነትን በረከት በመቀበል በክህነት መሪዎቻችሁ ከተለያችሁ በኋላ ለማገልገል ዝግጁ ናችሁ።ነገር ግን ከእናንተ የሚጠበቀውን እንዴት ልታውቁ ትችላላችሁ እንዲሁም ጥሪያችሁን እንዴት ማጉላት ትችላላችሁ?

ጌታ እንዲህ ሲል አስተምሯል፣ “እያንዳንዱም ሰው ተግባሩን በተመደበበት ሃላፊነትም በሙሉ ትጋት መስራትን ይማር” (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107፥99 ተመልከቱ)። በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳለ መሪ የጥሪያችሁን የስራ ሀላፊነቶች ለመማር እና ለመፈጸም ይረዳችሁ ዘንድ የግል መገለጥን መሻት አለባችሁ።

ቅዱሳን ጽሁፎችን እና የኋለኛው ቀን ነቢያትን ትምህርቶች ማጥናት የስራ ሀላፊነቶቻችሁን እንድታውቁ እና እንድትፈጽሙ ይረዷችኋል። የእግዚአብሄርን ቃላት ስታጠኑ የመንፈሱ ተጽዕኖ ይበልጥ ይሰማችኋል (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 84፥85 ተመልከቱ)።

በአጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች በማጥናትም የስራ ሀላፊነታችሁን ትማራላችሁ። የመንፈስ ቅዱስን ምሪት በመሻት በተግባር ላይ ሊውሉ ስለሚገባቸው መርሆች፣ ፖሊሲዎች እና የአሠራር ሂደቶች ግንዛቤ ለመስጠት ጥቅም ላይ ከዋሉ እነዚህ መመሪያዎች መገለጥን ሊጋብዙ ይችላሉ።

አትም