2022 (እ.አ.አ)
በቤተሰብ የቤት ምሽት ውስጥ መሳተፍ
ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)


የቃልኪዳን መንገዴ

በቤተሰብ የቤት ምሽት ውስጥ መሳተፍ

“ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እና እህት ሱዛን ቤድናር ሲጋቡ በተደጋጋሚ የቤተሰብ ጸሎት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የቤተሰብ የቤት ምሽት ከልጆቻቸው ያደርጉ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ አይሄዱም ነበር እናም ሽማግሌ እና እህት ቤድናር ጥረታቸው ጠቃሚ እንደሆነ ይገረሙ ነበር። በተደጋጋሚ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያጠኑበት ወቅት እንዲህ የሚል መንጫጫት ይሰማ ነበር፣ ‘እየነካኝ ነው!’ ‘እንዳያየኝ አድርጊው!’ እና ‘እማዬ፣ የእኔን አየር እየሳበ ነው!’ የቤተሰብ ጸሎት አንዳንድ ጊዜ በመሳቅ እና በመጎተንል ይረበሽ ነበር። እና በሶስት ንቁ፣ እረባሽ ወንድ ልጆች ምክንያት የቤተሰብ የቤት ምሽት ትምህርቶች ሁሌም ፀጥ ያለ አልነበረም።

“ነገር ግን ሙከራቸውን ቀጠሉ።” 1

የቤተሰብ የቤት ምሽት የቤተሰብ ትስስርን የማጠናከሪያ ጊዜ ነው። ይህን የምናደርገው ወንጌልን በጋራ በመማር፣ የእርስ በእርስ ስሜቶቻችንን በመደማመጥ በአስተሳሰቦች እና በሃሳቦች እና እንቅስቃሴዎችን አብሮ በመካፈል ነው። ብዙ ጊዜ ይህ ፕሮግራም የሚካሄደው በሰኞ ምሽት ነው።

ወንጌልን በቤት ውስጥ የመማሩ ልምምድ ከአዳም እና ከሔዋን ጀመረ (ሙሴ 6፥57ን ይመልከቱ)። ወላጆች ልጃቸውን እግዚአብሔርን እንዲወዱ እና የእርሱን መንገዶች እዲከተሉ እንዲያስተምሩ ነብያት ሲመክሩ በተከታይ ትውልዶች ሲወርድ ሲዋረድ መጣ (ዘዳግም 6፥5–7፤ ኤፌሶን 6፥4ን ይመልከቱ)።

የቤተሰብ የቤት ምሽት እርስ በእርስ ጥሩ ጊዜ የምናሳልፍበት እና በጋራ የምንጫወትበት ጊዜ ነው። በቀላል እንቅስቃሴዎች ማለትም—በጨዋታዎች፣ በአገልግሎት፣ ችሎታን በማካፈል፣ የአካባቢ ቦታዎችን በመጎብኘት—ቤተሰቦች ትስስሮችን ይፈጥራሉ እንዲሁም አንድነትን ይገነባሉ።

የቤተሰብ የቤት ምሽት ለእያንዳንዱ ሰው ነው። በቅርብ የተጋቡ ጥንዶች፣ አባቶች እና እናቶች ከልጆች ጋር፣ በትዳር ውስጥ ያልሆኑ ወላጆች ከልጆች ጋር፣ ያላገቡ ወጣቶች በቤት ምሽት ቡድን ውስጥ እና ለብቻቸው ወይም አብረው የሚኖሩ ሁሉ የቤተሰብ ቤት ምሽትን በማካሄድ መባረክ ይችላሉ።

ይህን ምክር ለሚከተሉ ሰዎች ነብያት ታላቅን እምነት በወጣቶች ልቦች ውስጥ፣ ፈተናን የመቋቋም ከፍተኛ ችሎታን እና ታላቅ ሰላምን፣ ፍቅርን እና ስምምነትን በቤት ውስጥ ጨምሮ ታላቅ በረከቶችን ቃል ገብተዋል።

በቤተሰብ የቤት ምሽት ውስጥ መሳተፍ ሁሌም አመቺ ወይም ቀላል አይደለም። ነገር ግን መሞከራችሁን ከቀጠላችሁ ልክ እንደ ሽማግሌ እና እህት ቤድናር እናንተ እና ቤተሰባችሁ ትባረካላችሁ።

ማስታወሻዎች

  1. “Be Consistent and Keep Trying”, ጓደኛ፣ ሚያዚያ 2017 (እ.አ.አ)።

አትም