2022 (እ.አ.አ)
ሚያዚያ 2019 (እ.አ.አ)፦ የኪንሻሳ ቤተመቅደስ ምረቃ
ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)


የዚህ ወር በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ

ሚያዚያ 2019 (እ.አ.አ)፦ የኪንሻሳ ቤተመቅደስ ምረቃ

በሚያዚያ 6 ቀን 1830 (እ.አ.አ) ወደ 40 የሚጠጉ የሴቶች እና የወንዶች ቡድን በፒተር ዊትመር፣ ቀዳማዊ ቤት ውስጥ በፋዬት ኒው ዮርክ የጌታን እውነተኛ ቤተክርስቲያን ለመመስረት ተገናኙ። ቤተክርስቲያኗም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተብላ ተጠራች እናም ትንሹ የቅዱሳን ቡድን ጆሴፍ ስሚዝን እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት እና ነቢያቸው ተቀበሉት። በሚቀጥለው ዓመትም፣ “በምድርም ለሰው የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፎችም ተሰጥተዋል፣ እናም ከዚህም ወንጌሉ እጅም፣ ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ምድርን እስከሚሞላ ድረስ እንደሚንከባለለውም ድንጋይ ወደ ምድር ዳርቻም [እንደሚገፋ]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65፥2) ለጆሴፍ ስሚዝ ተገለጠለት።

ቤተክርስቲያኗ ከተመሰረተች ከአንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ዓመታት በኋላ፣ የኪንሻሳ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ቤተመቅደስ 163ኛው በስራ ላይ ያለ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ በመሆን በሚያዚያ 14 ቀን 2019 (እ.አ.አ) ተመረቀ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የተቀደሰ አራተኛው ቤተመቅደስ እንዲሁም የመጀመሪያው የመካከለኛ አፍሪካ ክልል ቤተመቅደስ ነበር።

በሚያዚያ 1830 (እ.አ.አ) በአዲስ ተጠማቂ አባሎች ትንሽ ቡድን የጀመረችው ቤተክርስቲያን “[መንከባለሏን]” ቀጥላለች እናም በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ብቻ ወደ 700,000 የሚጠጉ አባሎችን በመያዝ መላውን ምድር በመሙላት ላይ ትገኛለች።

አትም