2022 (እ.አ.አ)
“በእምነት እና በደስታ መኖር እና መበልጸግ እንችላለን” – የሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ የአፍሪካ ጉብኝት
ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)


Local Pages

“በእምነት እና በደስታ መኖር እና መበልጸግ እንችላለን” – የሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ የአፍሪካ ጉብኝት

ህዳር 16 ማክሰኞ ምሽት ከአፍሪካ የመጣ አንድ ወጣት የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባል ለሆኑት ለሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ አጓጊ ጥያቄ አቀረበ።

“በወረርሽኙ ወቅት ብዙ ያላገቡ ወጣት አዋቂዎች ከኅብረት እጦት የተነሳ ራሳቸውን በአእምሯዊ፣ በስሜታዊ እና በመንፈሳዊ ማሽቆልቆል ውስጥ አግኝተዋል” ሲል ተናግሯል። “በአእምሮ የጤና እክል ለሚሰቃዩ እና ድባቴ፣ ጭንቀት ወይም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ለሚሰማቸው ምን ምክር አለዎት?”

በአፍሪካ ማዕከላዊ እና በአፍሪካ ደቡባዊ አካባቢዎች ባሉ 32 ሀገራት ውስጥ ከሚገኙ በስም ያልተጠቀሱ ወጣቶች እና ወጣት አዋቂዎች ከተነሱት በርካታ ጥያቄዎች አንዱ ነበር።እርሳቸው የሰጧቸውን ምላሾችንም በቀጥታ የፌስ ቡክ ስርጭት ላይ ተከታትለዋል።

በሽማግሌ ራዝባንድ የተመራ ሲሆን በርካታ የአለም አቀፍ እና የአካባቢ የቤተክርስቲያን መሪዎችም ተሳትፈዋል።ይህም ሽማግሌ ፓትሪክ ኪሮን (የሰባዎቹ ከፍተኛ ፕሬዚዳንት) እና ባለቤታቸውን ጄኒፈርን፤ ኤጲስ ቆጶስ ኤል. ቶድ ባጅን (የኤጲስ ቆጶስ አመራር) እና ባለቤታቸውን ሎሪን፤ ሽማግሌ ክሪስቶፌል ጎልደንን (የአፍሪካ ደቡባዊ አካባቢ ፕሬዚዳንት) እና ባለቤታቸውን ዳያንን እንዲሁም የሽማግሌ ጆሴፍ ደብሊው ሲታቲ (የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ፕሬዚዳንት) ባለቤት የሆነችውን ግላዲስ ሲታቲን ያካተት ነበር።

አንድ ላይ በመሆንም ከኮቪድ-19 ክትባት አንስቶ እስከ ጾታዊ ጥቃት እና አንድ ሰው ከወደፊት የትዳር አጋሩ የትኞቹን ባህሪያት መፈለግ እንዳለበት በሚሸፍኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከልብ የመነጨ ምክር እና ምስክርነት ሰጥተዋል።

በዚህ አንድ ሰአት ያህል በፈጀው ዝግጅት ወቅት ወደ 800 የሚጠጉ አስተያየቶች ከተመልካቾች ተልከዋል።

ከኮንጎ ብራዛቪል የመጣው ኢቭሬሴ ሩሶ “ለዚህ አስደናቂ ጊዜ እና በዝግጅቱ ወቅት ለተሰማን መንፈስ እናመሰግናለን” ብሏል።

የዛምቢያ ነዋሪ የሆነችው ናታሊ ካፔማ “ይህ ስርጭት በጣም ረድቷል” ስትል ሃሳቧን ሰጥታለች።

ዝግጅቱ በሽማግሌ ራዝባንድ፣ በኪሮን እና በባለቤታቸው እንዲሁም በባጅ እና በባለቤታቸው የተደረገ የ11 ቀናት የአፍሪካ ጉብኝት አካል ነበር።

በቴክኖሎጂ በመታገዝ ጎብኚ መሪዎቹ በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ የክህነት አመራር ጉባኤዎችን እና ሌሎች ስብሰባዎችን አካሂደዋል እንዲሁም በዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪንሻሳ እና በኬንያ ናይሮቢ በተደረጉ የካስማ ኮንፈረንሶች ላይ ተሳትፈዋል።መሪዎቹ በጋቦን እና በካሜሩን እንዲያገለግሉ ከተመደቡ እንዲሁም በቅርቡ በተከሰተው አለመረጋጋት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ከተደረጉ ሚስዮናውያን ጋር በቴክኖሎጂ የታገዘ የገጽ ለገጽ ውይይት አድርገው ነበር።በአፍሪካ ደቡባዊ አካባቢ ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና አባላት ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን በቅርቡ እንደገና ወደተከፈተው በደቡብ አፍሪካ ምዕራብ ጆሃንስበርግ ወደሚገኘው ሩድፖርት የሚስዮናውያን ማሠልጠኛ ማዕከልም በድንገት ተጉዘው ነበር። በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ሽማግሌ ራዝባንድ ቅዱሳን ጥያቄዎች እንዲያቀርቡ ጋብዘው የነበረ ሲሆን ምላሽም ሰጥተዋል።

‘ጌታ በቀጥታ ስለችግሮቻችን የተናገረ ያህል ነበር’

የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ፕሬዚዳንት ሽማግሌ ጆሴፍ ደወብልዩ. ሲታቲ እንደተናገሩት በቅርቡ ለአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ እና ለአፍሪካ ደቡባዊ አካባቢ እንደተቆጣጣሪ ሃዋርያ ሆነው የተመደቡት የሽማግሌ ራዝባንድ ጉብኝት ጌታ በአፍሪካ አህጉር ለሚገኙ ቅዱሳን የደረሰ ያህል ነበር።

“አንድ የጌታ ሐዋርያ በተለይ በአፍሪካ መካከለኛው አካባቢ ቤተክርስቲያን ላይ ማተኮሩ በእርግጥ እኛ እንደመሪዎች እና እንደአባላት ስለሚያጋጥሙን ችግሮች ጌታ ራሱ እንዲናገር እንደማድረግ ነው” ብለዋል።

የአፍሪካ ደቡባዊ አካባቢ ፕሬዚዳንት ሽማግሌ ክሪስቶፍል ጎልደን የሽማግሌ ራዝባንድ ጉብኝት አስፈላጊነት የተመለከቱ አንዳንድ መልእክቶች ላይ ገለጻ አድርገዋል።

“የመጀመሪያው መርህ ፍቅርን ያካትታል” ብለዋል። ሽማግሌ ራዝባንድ ለእግዚአብሔርን እና ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅር በማዳበር አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።

እንዲሁም እርሳቸው “እንደመሪዎች ቤተክርስቲያንን እንድናጠናክር እና በዚህ በአፍሪካ ወንጌልን እንድንኖር መመሪያ ሰጥተውናል።

ከዚህም ጋር ህያው የሆነውን ነቢይ ለመከተል ግልጽ ጥሪ መጥቷል። ሽማግሌ ሲታቲ ይህ “በተለይ ብዙዎች የኮቪድ-19 ክትባት ያልተከተቡ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን እንደኢትዮጵያ፣ኡጋንዳ እና በአንዳንድ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ አካባቢዎች በመሳሰሉት ቦታዎች በተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ውጥረት እየበዛባቸው ያሉ በርካታ ቦታዎች ባሉበት ጊዜ በተለይ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

‘‘በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እምነት እና ደስታ”

ሆኖም እነዚህ ችግሮች ቢኖሩም “የትም እንኑር የት፣ በማንኛውም ሁኔታ እና በማንኛውም ጊዜ በወቅቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ውስጥም እንኳን በእምነት እና በደስታ መኖር እና መበልጸግ እንደምንችል ሐዋርያዊ ማረጋገጫ ተሰጥቶናል” ብለዋል ሽማግሌ ጎልደን።

ሽማግሌ ሲታቲ ከሐዋርያው የመጣውን “ማጽናኛ እና ማረጋገጫም” ገልጸዋል። ስሜቱን ለሌላ ሰው በትክክል መግለጽ ይከብደኛል፤ ነገር ግን ከእሱ ጋር መሆኔ የቅዱስነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል።

ወደ ዩኤስኤ ከመመለሳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ሽማግሌ ራዝባንድ አፍሪካ ውስጥ ባገኟቸው ሰዎች “በጣም እንደተደነቁ እና እንደተመሰጡ” ተናግረዋል።

“ወደአፍሪካ ስመጣ ይህ ስድስተኛ ጊዜዬ ነው እናም በሁሉም ሰው ያለማቋረጥ ተደስቻለሁ እንዲሁም ተነሳስቻለሁ” “ከእኛ ጋር አብረውን በነበሩት አመራሮች፣ ወይም አባላት፣ ወይም ሚስዮናውያንም ሆነ የተቻላቸውን ሁሉ በሚያደርጉ እና የጌታን ቤተክርስቲያን እና መንግስት በሚገነቡት በእነዚህ ድንቅ ሰዎች ተገርሚያለሁ።” ሲሉ ተናግረዋል።

አትም