ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፭


ምዕራፍ ፭

ኔፋውያን ንሰሃ ገቡ እናም ኃጢአቶቻቸውን ተዉ—ሞርሞን የህዝቡን ታሪክ ፃፈ እናም ዘላለማዊውን ቃል አወጀ—እስራኤል ለረጅም ጊዜ ከተበተነበት ይሰበሰባል። ፳፪–፳፮ ዓ.ም. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ ቅዱሳን ነቢያት በሙሉ የተናገሩትን ቃላት በጥቂቱም ቢሆን የተጠራጠሩ ከኔፊ ህዝብ መካከል ህያው ከሆነ ነፍስ አንድም አልነበረም፤ ምክንያቱም እነዚህ መፈፀም እንዳለባቸው ያውቃሉና።

እናም እንደነቢያቱ ቃላት በተሰጡት ብዙ ምልክቶች የተነሳ የክርስቶስ መምጣት አስፈላጊ መሆኑን ያውቁ ነበር፤ እናም በተከናወኑትም ነገሮች የተነሳ ሁሉም ነገሮች በተነገሩት መሰረት መምጣት እንዳለባቸውም ያውቁ ነበር።

ስለዚህ እነርሱም ኃጢአቶቻቸውን፣ እንዲሁም እርኩሰቶቻቸውን እንዲሁም ዝሙት መፈጸማቸውን ተዉ፣ እናም ቀንና ምሽት በሙሉ ትጋትም እግዚአብሔርን አገለገሉ።

እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ የዘራፊዎቹን እስረኞች በሙሉ በመውሰዳቸው በህይወት ያመለጠ ምንም ባልነበረበት ጊዜ፣ እስረኞቹንም ወህኒ ቤት ጣሉአቸውና፣ የእግዚእብሔር ቃልም እንዲሰበክላቸው አደረጉ፤ እናም ለኃጢአታቸው ንስሀ የገቡና ከእንግዲህ ወዲያም ላለመግደል ቃል ኪዳን የሚገቡት ሁሉ ተለቀቁ

ነገር ግን ወደ ቃል ኪዳን ያልገቡ፣ እናም በልባቸው ሚስጥራዊ ግድያውን አሁንም የቀጠሉ፣ አዎን፣ በወንድሞቻቸው ላይ ማስፈራሪያ የሚያደርጉ ተፈርዶባቸዋልና በህጉም መሰረት ተቀጥተዋል።

እናም ብዙ ክፋቶችና ብዙ ግድያዎች የተፈፀሙባቸውን ጥፋቶች፣ እናም ሚስጢራዊና እርኩስ ህብረቶችን ሁሉ እንደዚህ አቆሙ።

እናም እንደዚህ ሃያ ሁለተኛው ዓመት አለፈና፣ ደግሞ ሃያ ሦስተኛው ዓመትም፣ እናም ሃያ አራተኛውና፣ ሃያ አምስተኛው ዓመት እንደዚህ አለፉ።

በጥቂቶች ዐይን ታላቅ እንዲሁም አስደናቂ የሆኑ ብዙ ነገሮች ደረሱ፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች በሙሉ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሊፃፉ አይቻሉም፤ አዎን፣ ብዛት ባላቸው በእነዚህ ሰዎች መካከል በሃያ አምስት ዓመታት ጊዜ የተከናወኑትን አንድ መቶኛ እንኳን ይህ መጽሐፍ ሊይዘው አይችልም፤

ነገር ግን እነሆ የዚህን ህዝብ ታሪኮች በሙሉ የያዙ መዛግብቶች አሉ፤ እናም አጭር ነገር ግን እውነት የሆነው ታሪክ ግን በኔፊ ተሰጥቷል።

ስለዚህ የኔፊ ሠሌዳዎች ተብለው በሚጠሩት ሠሌዳዎች ላይ በተቀረጹት የኔፊ መዛግብት መሰረት ስለእነዚህ ነገሮች መዛግብቱን ፅፌአለሁ።

፲፩ እናም እነሆ፣ ታሪኩን በራሴ እጅ በሠራኋቸው ሠሌዳዎች ላይ እፅፋለሁ።

፲፪ እናም እነሆ፣ ስሜ ሞርሞን ይባላል፤ የተጠራሁትም አልማ በህዝቡ መካከል ቤተክርስቲያኑን አቋቁሞ በነበረበት፣ አዎን፣ ከመተላለፋቸው በኋላ በመካከላቸው የተቋቋመው የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ባቋቋመበት በሞርሞን ምድር ስም ነው።

፲፫ እነሆ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ነኝ። ዘላለማዊ ህይወትንም ያገኙ ዘንድ፣ በህዝቡ መካከል ቃሉን እንዳሰራጭ በእርሱ ተጠርቻለሁ።

፲፬ እናም ቅዱሳን የነበሩት፤ የሞቱት ፀሎት እንደእምነታቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ፣ የተከናወኑት የእነዚህ ነገሮች ታሪክ መፃፍ አስፈላጊ ሆኖ ነበር—

፲፭ አዎን ሌሂ ኢየሩሳሌምን ለቆ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን የተከናወነውን በያዘው በአነስተኛው መዝገብ እፅፋለሁ።

፲፮ ስለዚህ የእኔ ጊዜ እስከሚጀመርበት ድረስ ከእኔ በፊት በነበሩት ከተጻፉት ታሪኮች ውስጥ መዛግብቴን እፅፋለሁ፤

፲፯ እናም ከእዚያም በዐይኖቼ የተመለከትኳቸውን ነገሮች ታሪክ ፅፌአለሁ።

፲፰ እናም የፃፍኩትም ታሪክ ትክክለኛ እንዲሁም እውነተኛ መሆናቸውን አውቃለሁኝ፤ ይሁን እንጂ በቋንቋችንም ውሱንነት ምክንያት ልንፅፋቸው የማይቻሉን ብዙ ነገሮች አሉ።

፲፱ እናም አሁን ስለራሴ የምናገረውን አበቃለሁና፣ በፊቴ ስለነበሩት ነገሮች ዘገባዬን እቀጥላለሁ።

እናም እኔ ሞርሞን ነኝና፣ የሌሂ ቀጥተኛ ዘር ነኝ። አባቶቻችንን ከኢየሩሳሌም ምድር በማስወጣቱ (እናም ከምድሪቱ እንዳወጣቸው ከእርሱ ከራሱ በቀር ማንም አያውቅም) እናም ለእኔና ለህዝቤ ለነፍሳችን ደህንነት እውቀትን አብዝቶ ስለሰጠን አምላኬን እንዲሁም አዳኜ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወደስ ምክንያት አለኝ።

፳፩ በእርግጥ የያዕቆብን ቤት ባርኳል፤ እናም ለዮሴፍም ዘር መሃሪ ሆኗል።

፳፪ እናም የሌሂ ልጆችም ትዕዛዛቱን እስከጠበቁ ድረስ እንደቃሉም ባርኳቸዋልና እንዲበለፅጉ አድርጓል።

፳፫ አዎን፣ እናም በእርግጥ በድጋሚም የዮሴፍ ዘር ቅሪት የሆኑት ጌታ አምላካቸውን እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል።

፳፬ እናም ጌታ በእርግጥም ህያው እንደሆነ፣ የያዕቆብ ዘር ቅሪት የሆኑትን በሙሉ በምድር ገፅ ላይ ሁሉ የተበተኑትን ከምድር ከአራቱም ማዕዘን ይሰበስባቸዋል

፳፭ እናም ከያዕቆብ ቤትም ጋር ቃል ኪዳን እንደገባም፣ የያዕቆብ ቤት በሙሉ ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዲያውቁ፣ በራሱም ጊዜ ከያዕቆብ ቤት ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያሟላል።

፳፮ እናም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛቸውን ያውቃሉ፤ እናም ከተበተኑበት ሥፍራ ከምድር ከአራቱም ማዕዘናት ወደራሳቸው ምድር ይሰበሰባሉ፤ አዎን፣ ጌታም ህያው እንደሆነ ይህም ይሆናል። አሜን።