ምዕራፍ ፲፩
የያሬዳውያን ህይወት በጦርነት፤ በፀብ እና በክፋት የተሞላ ነበር—ያሬዳውያን ንሰሃ ካልገቡ ፈፅመው እንደሚጠፉ ነቢያት ተንብየዋል—ህዝቡም የነቢያትን ቃላት አልተቀበሉም።
፩ እናም ደግሞ በቆም ዘመን ብዙ ነቢያት ተነሱ፣ እናም ያ ታላቅ ህዝብም ንሰሃ ካልገባ እናም ወደጌታ ካልተመለሱ፣ እናም ግድያቸውን እናም ክፋታቸውን ካላቆሙ እንደሚጠፉ ትንቢት ተናገሩ።
፪ እናም እንዲህ ሆነ ነቢያቱም በህዝቡ ተቀባይነትን አላገኙም ነበር፣ እናም ህዝቡም ሊገድሏቸው ስለፈለጉ የቆምን ጥበቃ ለማግኘት ወደ እርሱ ሸሹ።
፫ እናም ለቆምም ብዙ ነገሮችን ተነበዩለት፤ እናም እርሱም በቀሪው ዘመኑ ሁሉ የተባረከ ነበር።
፬ እናም በመልካም እርጅና ሁኔታ ውስጥ ኖረ፣ እናም ሺብሎምንም ወለደ፤ ሺብሎምም በእርሱ ምትክ ነገሰ። እናም የሺብሎምም ወንድም በእርሱ ላይ አመፀበት፣ እናም በምድሪቱ ሁሉ እጅግ ታላቅ የሆነ ጦርነትም ተጀመረ።
፭ እናም እንዲህ ሆነ የሺብሎም ወንድምም ስለህዝቡ መጥፋት የተነበዩት ነቢያት በሙሉ እንዲገደሉ አደረገ፤
፮ እናም በምድሪቱ ሁሉ ታላቅ መቅሰፍት ሆነ፣ ምክንያቱም ለኃጢአታቸውም ንሰሃ ካልገቡ ታላቅ እርግማን በምድሪቱ ላይ፣ እናም ደግሞ በህዝቡ ላይ እንደሚሆን፣ እናም ከዚህ በፊት በምድር ላይ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ጥፋትም በመካከላቸው እንደሚሆን፣ እናም ንሰሃ ካልገቡ አጥንቶቻቸውም በመሬት ላይ እንደተራራ እንደሚቆለሉም መስክረዋልና።
፯ እናም በክፉው ህብረታቸው የተነሳ የጌታን ድምፅ አላዳመጡም፤ ስለዚህ፣ በምድሪቱ ሁሉ ጦርነት እናም ፀብ ተጀመረ፣ እናም ደግሞ ብዙ ረሃብ እና ቸነፈር ሆነ፤ በዚህም የተነሳ ታላቅ ጥፋት ከዚህ በፊት በምድር ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሆነ፤ እናም ይህ ሁሉ የሆነው በሺብሎም ዘመን ነበር።
፰ እናም ህዝቡም ለጥፋቶቻቸው ንሰሃ መግባት ጀመሩ፤ እናም ይህንንም ባደረጉ ጊዜ ጌታ በእነርሱ ላይ ምህረት አደረገላቸው።
፱ እናም እንዲህ ሆነ ሺብሎም ተገደለ፤ እናም ሴትም ወደ ምርኮ ተወሰደ፣ እናም በዘመኑ ሁሉ በምርኮ ኖረ።
፲ እናም እንዲህ ሆነ ልጁ አሃህ መንግስቱን አገኘ፤ እናም በዘመኑ ሁሉ በህዝቡ ላይ ነገሰ። እናም እርሱም በዘመኑ ብዙ አይነት ክፋቶችን አደረገ፤ በዚያም ብዙ ደም እንዲፈስ አደረገ፤ እናም የእርሱም ዘመን ጥቂት ነበር።
፲፩ እናም ኤተም፣ የአሃህ ወገን በመሆኑም መንግስቱን አገኘ፤ እናም እርሱም ደግሞ በዘመኑ መጥፎ የሆነውን አደረገ።
፲፪ እናም እንዲህ ሆነ በኤተም ዘመን ብዙ ነቢያቶች መጡ፣ እናም በህዝቡም ላይ ትንቢትን ተናገሩ፤ አዎን፣ ለኃጢአቶቻቸው ንሰሃ ካልገቡ በስተቀር ጌታ ፈፅሞ ከምድር ላይ እንደሚያጠፋቸውም ተነበዩ።
፲፫ እናም እንዲህ ሆነ ህዝቡም ልባቸውን አጠጠሩ፤ እናም ቃላቸውንም አላዳመጡም፤ እናም ነቢያቶቹም አዘኑ እናም ከህዝቡ መካከል ወጡ።
፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ኤተም በዘመኑ ሁሉ በክፋት ፍርድን ፈፀመ፤ እናም ሞሮንን ወለደ። እናም እንዲህ ሆነ ሞሮንም በእርሱ ምትክ ነገሰ፤ ሞሮንም በጌታ ፊት መጥፎ የሆነውን አደረገ።
፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ስልጣንን እናም ጥቅምን ለማግኘት በተቋቋመው ሚስጢራዊ ሴራ የተነሳ በህዝቡ መካከል አመፅ ተነሳ፤ እናም በእነርሱም መካከል በክፋት ኃያል የሆነ ሰው ተነሳ፣ እናም እርሱም ከሞሮን ጋር ተዋጋ፣ ከዚያም የመንግስቱን ግማሽ አሸነፈ፤ እናም እርሱም ለብዙ ዓመታት ግማሹን መንግስት አስተዳደረ።
፲፮ እናም እንዲህ ሆነ ሞሮንም አሸነፈው፣ እናም መንግስቱን በድጋሚ ያዘ።
፲፯ እናም እንዲህ ሆነ ሌላም ኃያል ሰው ተነሳ፤ እርሱም የያሬድ ወንድም ወገን ነበር።
፲፰ እናም እንዲህ ሆነ እርሱም ሞሮንን በማሸነፍ መንግስቱን ያዘ፤ ስለሆነም፣ ሞሮን በተቀረው ዘመኑ በግዞት ኖረ፤ እናም እርሱም ቆሪያንቶር ወለደ።
፲፱ እናም እንዲህ ሆነ ቆሪያንቶር በዘመኑ ሁሉ በግዞት ኖረ።
፳ እናም በቆሪያንቶርም ዘመን ደግሞ ብዙ ነቢያቶች ተነሱ፣ እናም ታላቅ እናም አስገራሚ ነገሮችን ተነበዩ፣ እናም ወደ ህዝቡም ለንሰሃ ጮኹ፣ እናም ንሰሃ ካልገቡ በስተቀር ጌታ እግዚአብሔርም እነርሱን ፈፅሞ በማጥፋት ፍርዱን እንደሚፈፅም ተናገሩ፤
፳፩ እናም ጌታ እግዚአብሔር በስልጣኑ አባቶቻቸውን እንዳመጣ ሌሎች ሰዎች ምድሪቱን እንዲወርሱ እንደሚልክ ወይም እንደሚያመጣ ተናገሩ።
፳፪ እናም እነርሱም በሚስጢራዊው ህብረት እናም ክፉ በሆነው እርኩሰታቸው የነቢያቱን ቃላት በሙሉ አልተቀበሉም።
፳፫ እናም እንዲህ ሆነ ቆሪያንቶር ኤተርን ወለደ፣ እናም በዘመኑ ሁሉ በግዞት ኖሮ ሞተ።